TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.44K videos
208 files
4.01K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የሰላም_ዋጋው_ውድ_ነው!!!
#የሰላም_ዋጋው_ውድ_ነው!!!
#የሰላም_ዋጋው_ውድ_ነው!!!

ይህ ተረት ተረት አይደለም!

በሩዋንዳ በ100 ቀናት ብቻ 800,000 የሩዋንዳ ዜጎች በዘር ግጭት ሳቢያ ሙተዋል!!

#ሩዋንዳ_ምሳሌ_ትሁነን!!

ዘረኝነት እና የዘረኝነት ቅስቀሳዎች ያስከተሉትን ጉዳት ለመረዳት ከጉረቤታችን ሩዋንዳ በቀላሉ ልንማር እንችላለን!!

በሁቱና ቱትሲ ዘሮች ብቻ ዘርን ማዕከል ተደርጎ ፅንፈኛ #ሚዲያዎች በሰሩት #ግደለው #አቃጥለው #አውድመው የተሰኘ ቅስቀሳ በ100 ቀናት ብቻ ለማመን በሚከብድ ሁናቴ 800,000 የሩዋንዳ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሂወታቸውን አጠዋል፡፡

እኛ ከሩዋንዳ ምን እንማር?

በሩዋንዳ የሆነው ተረት ተረት አይደለም ዛሬ ከታሪካቸው የተማሩበት ከባድ ጠባሳ እንጂ አሁን እኛ ጋር የምናየው የዘረኝነት #እብደት ሩዋንዳም ያኔ ሲጀማምራቸው የገጠማቸው ችግር ነው፡፡

ዛሬ ሀላፊነት በጎደለው መንገድ የምትተኮስ #የጥላቻ ጥይት ጥላቻውን በስሜት ለሚተኩሳት የጥፊት ሀይልም የምትዳረስ ናት፡፡

እናማ በዚህም አልን በዚያ ሩዋንዳ ምሳሌ ትሁነን!!
#ሰላም ሰላም ሰላም ሁሌም ለሰላም ቅድሚያ እንስጥ!!

#ሞገደኛው_ብዕር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በረሃብ የሰዎች ህይወት ስለማለፉ ማረጋገጫ የለንም " - አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማርያም (ዶ/ር)

የፌዴራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) " በኢትዮጵያ በረሃብ ምክንያት የሰው ህይወት አልፏል የሚል ማረጋገጫ የለንም " አሉ።

ኮሚሽነሩ ይህንን ያሉት ከፋና ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማርያም (ዶ/ር) ምን አሉ ?

- መንግስት 11 ቢሊዮን ብር መድቦ እየሰራ ነው።

- በፌዴራል የሚደረገው ድጋፍ ክልሎችና ከታች ያሉ መዋቅሮቻቸው እንዲሁም ማህበረሰቡ በሚያደርገው ድጋፍ ላይ ተጨማሪ ነው።

- አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የአህል ክምችት ቢኖረንም ትራንስፖርት ሰጪዎች በፀጥታው ምክንያት በፈለግነው ልክ ለማቅረብ አልቻልንም የሚሉት ነገር አለ። ይሄን ከሚመለከታቸው ጋር ተነጋግሮ ይስተካከላል።

- የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብ ተቀይሮ የሰውን ህይወት የሚያጠፋበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ መዋቅራዊ አደረጃጀታችን የሚፈቅል አይደለም። የቀበሌ፣ የወረዳ ፣ የዞን፣ የክልል መዋቅር አለን የሚችለውን የመደጋገፍ ስራ ይሰራል። ህይወትን የመታደግ ስራ ይሰራል። እዚህ ላይ የፌዴራልም ድጋፍ አለ።

- የድርቅ አደጋ በሚኖርበት ጊዜ የስነምግብ ሁኔታዎችን በመውሰድ ምናልባት በአካባቢው የሚፈጠሩ ወረርሽኝ እና የመሳሰሉት ነገሮች የተለያዩ ነገሮችን ፈጥረው የዜጎቻችንን በሽታን የመቋቋም አቅም አዳክመው በቀላሉ የመሸነፍ እና የመሳሳሉት ጉዳዮች ሊፈጥር ይችላል።

-ሰዎች እንደሚያነሱት ፤ አንዳንድ #ሚዲያዎች እንደሚያነሱት በእህል እጥረት  ፤ ድርቅ ወደ ረሃብ ተቀይሮ የሰውን ህይወት የሚያጠፋበት ደረጃ የራሱ የሆነ ጊዜ አለው የራሱ የሆነ ጊዜ ይወስዳል በዚህ ነው ሰው የሞተው ለማለት #ምርመራ ይፈልጋል። የሰው የሞት ምክንያት ምንድነው ? እንደምናውቀው ሰው በተለያዩ ምክንያቶች ህይወቱ ያልፋል የዛ ህይወቱ ያለፈው ሰው ምክንያቱ ምንድነው ? የሚለውን የመለየት እና የማረጋገጥ ስራ የራሱ የሆነ አካሄድና  መንገድ ይጠይቃል።

- በእኛ በኮሚሽናችን ግምገማ የተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት አለመኖር የሚፈጥራቸው ተጋላጭነት ሊኖር እንደሚችል የምንገነዘብ ቢሆንም ግን በረሃብ ምክንያት ህይወቱ ያለፈ ሰው ስለመኖሩ #ማረጋገጫ_የለንም
.
.
በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ እና አማራ ክልሎች ያሉ ከታች ያሉ መዋቅሮች በረሃብ ምክንያት ሰዎች ህይወት እንዳለፈ በተደጋጋሚ መግለፃቸው ይታወሳል።

በትግራይ ክልል የላይኛው መዋቅርም 25 ህፃናትን ጨምሮ 400 ሰዎች በረሃብ ምክንያት ህይወታቸው እንደጠፋ ማሳወቁ አይዘነጋም።

በክልል ከታች እስከላይ ማዋቅር የሚሰጡት እና ነዋሪዎች የሚገልጹት የረሃብ ሁኔታ በፌዴራል አደጋ ስጋት አመራር ቅቡልነት የለውም። ኮሚሽኑ በረሃብ ምክንያት የጠፋ ህይወት ስለመኖሩም ማረጋገጫ የለኝም ብሏል።

ከዚህ ቀደም የፌዴራል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን  " ክልሎች ትኩረት እና የተሻለ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ' ይህንን ያህል ሰዎች #ሞተውብኛል፣ ይህንን ያህል ተጎድተውብኛል ' የሚል መረጃ ያቀርባሉ " ማለቱ አየዝነጋም።

@tikvahethiopia
#EOTC

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ከዚህ ቀደም አውግዛ የለየቻቸው ግለሰቦች አሁንም በሕገወጥ እንቅስቃሴያቸው እንደገፉበት አመልክታ ግለሰቦቹን በፍርድ እንደምትጠይቅ አስታወቀች።

ግለሰቦቹን አሁንም አውግዛ ፤ ድርጊታቸውን ተቃውማለች።

የለበሱት ልብስም የቤተክርስቲያን በመሆኑ #እንዲያወልቁት እንደምታደርግ ገልጻለች።

ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያን " ሕገወጥ " ባለችው መንገድ በጵጵስና ተሹመናል ካሉት እና በኃላም በእርቅ ወደቤተክርስቲያን ሳይመለሱ ከቀሩት መካከል አባ ገብረማርያም ነጋሳን ጨምሮ 4 አባቶች ትላንት በሰጡት መግለጫ " የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ቤተክህነት መንበረ ጴጥሮስ " አቋቁመናል ብለዋል።

ይህ በ2015 ዓ/ም ተቋቁሟል ላሉት የኦሮሚያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንበር መሰየም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቋሚና ጊዜያዊ ፕሮጀክት መምሪያ ኃላፊ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ወ/ኢየሱስ ሰይፉ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫ ፤ " ግለሰቦቹ በሌላቸው ክህነት ነው መግለጫ እየሰጡ ያሉት " ብለዋል።

እነዚህን አካላት ያደረጉት ከቀኖና ውጭ ስለሆነ ዛሬም ቤተክርስቲያን አጥብቃ ታወግዛለች ሲሉ ተናግረዋል።

" ቤተክርስቲያን በሕግ በፍርድ ቤት ትጠይቃችለች ፤ በፍትህ መንፈሳዊ ከዚህ ቀደም እንዳወገዘችው አሁንም ህጌ፣ ስርዓቴ፣ ልብሴ ፣ ዶግማዬ ይከበር ትላለች " ሲሉ አክለዋል።

" ከዚህ ቀደም በፍ/ቤት ከቤተክርስቲያን እውቅና ውጭ የትም እንዳይንቀሳቀሱ ፣ አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደው ነበር ያንን ተላልፈዋል ከዚህ በኃላ በፍርድ እንጠይቃቸዋለን፤ የለበሱት ልብስም የቤተክርስቲያን ስለሆነ እናስወልቃቸዋለን፤ ህገወጥ ናቸው " ብለዋል።

" ከዚህ ባለፈ ይህ የሕገወጥ የሹመት እንቅስቃሴ ጉዳይ ከኦሮሚያ ወገን የተነሱትን ብቻ ሳይሆን ከትግራይ ወገን የተነሱትንም የሚመለከት ነው " ያሉ ሲሆን ሲመቱ ትክክለኛ አይደለም ቅዱስ ሲኖዶስም አይቀበለውም ብለዋል።

የቤተክርስቲያንን ውሳኔ ማስፈፀም የሚችል አካል ሌላ በመሆኑ እንዲያስፈፅም በትዕግስት እየጠበቅን ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ኃላፊው ፤ ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት አባቶች በቤተክርስቲያን ጥሪ ተመልሰው መጥተው ፣ ከመንግሥት ጋር በተደረግው ውይይት ፣ ወደቀድሞ ስራቸው እንዲመለሱ ተደርጎ በስራ ላይ ናቸው ብለዋል።

አራቱ እንዳልተመለሱና በሕገወጥ እንቅስቃሴ መቀጠላቸውን ገልጸው " የቤተክርስቲያንን ስም ማንሳት አይችሉም ፣ ስሟን ማጠልሸት አይችሉም " ሲሉ አሳስበዋል።

" እራሱ ህገወጥ ቡድን የ ' 5 ኪሎ ህገወጥ ' እያለ መጥራቱ ትልቅ ድፍረት ነው " ያሉት ኃላፊው ፤ " ይህን ድፍረት የሰጣቸውም ወቅትና ጊዜውን እየዋጁ መነሳታቸው ነው ብለዋል።

" #ሃይማኖት እና #ፖለቲካም ተቀላቅሎባቸዋል " ሲሉ አክለዋል።

" የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ምዕመናኖቿ ይህንን ህገወጥ ተግባር አይቀበሉትም ፤ ስለተወገዛችሁም ምዕመኑንም ከእናተ መስቀል አይባረክም " ሲሉ አሳውቀዋል።

ከዚህ ባለፈ ቤተክርስቲያኗ አውግዤ የለየኋቸውን አካላት መግለጫ ልክ እንደ ህጋዊ እያደረጉ ያቀርባሉ ያለቻቸውን #ሚዲያዎች ' ከቤተክርስቲያን ላይ እጃችሁን ፣ ሚዲያችሁን አንሱ ' ስትል አስጠንቅቃለች።

@tikvahethiopia