TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ሙስጠፋ ማን ናቸው?⬆️

አቶ ሙስጠፋ ሙሐሙድ ዑመር በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሶማሌ ክልል #ጊዜያዊ መሪ ሆነው ተመርጠዋል።

አቶ ሙስጠፋ በክልሉ በስልጣን ላይ ያለዉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አባል ባይሆኑም በጊዜያዊነት ላለፉት ሁለት ሳምንታት በሥልጣን የቆዩትን አሕመድ አብዲ መሐመድን ተክተው ለመጪዎቹ ሁለት አመታት ክልሉን ይመራሉ።

በርዕሰ-መሥተዳድርነት እንዲያገለግሉ መመረጣቸው እስከተሰማ ድረስ ከነ ቤተሰቦቻቸው ኬንያ ይኖሩ የነበሩት አቶ ሙስጠፋ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሶማሊያ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በመስራት ላይ ነበሩ።

ኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ የሕጻናት አድን ድርጅትን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ አገልግለዋል።

አቶ ሙስጠፋ የተወለዱት ከጅጅጋ 200 ኪሎ ሜትር ገደማ በምትርቀው አዋሬ የተባለች አነስተኛ ከተማ በ1964 ዓ.ም. ነው። ትምህርታቸውን በደገሐቡር እና በሐረር የመድሐኒዓለም ትምህርት ቤቶች ተከታትለዋል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪቸውን በኤኮኖሚክስ አግኝተዋል። ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በዚያው በኤኮኖሚክስ ከለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ በተልዕኮ ትምህርት አግኝተዋል።

ከዚህ ቀደም የሶማሌ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የዶክተር አብዱል መጂድ ሑሴን መምህራን ማሰልጠኛ ማዕከል ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

ከኢትዮጵያ ለምን ወጡ⬇️

አቶ ሙስጠፋ በቅርቡ ከሥልጣናቸው የተነሱት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር የክልሉን የርዕሰ-መሥተዳድርነት ሥልጣን ሲቆጣጠሩ ነው የሶማሌ ክልልን የለቀቁት።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኤኮኖሚክስ ተማሪ ሳሉ የአቶ ሙስጠፋ ጓደኛ የነበሩት አቶ ዚያድ አሕመድ የቀድሞው ርዕሰ መሥተዳድር አብዲ መሐመድ ዑመር "ያደርሱባቸው የነበረውን ችግር #ሸሽተው" ከነ ቤተሰቦቻቸው #ኬንያ ለመግባት መገደዳቸውን ያስታውሳሉ።

ከሁለት አመታት በፊት አቶ ሙስጠፋ በክልሉ መንግሥት ላይ የሚሰነዝሩትን ተቃውሞ እንዲያቆሙ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ አሻፈረኝ በማለታቸው የምኅንድስና ባለሙያ #ወንድማቸው ፋይሰል ኦማር በልዩ ፖሊስ ከደገሐቡር ከተማ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ #መገደላቸው ይነገራል። አቶ ዚያድም "ውጪ ያሉት አራማጆች በአብዲ ኢሌ ላይ ወይም በነበረው አገዛዝ ላይ ተቃውሞ ካሰሙ ወይም አንድ ነገር ካደረጉ ቤተሰቦቻቸው ይታሰራሉ ወይም ይገረፋሉ። አቶ ሙስጠፋም ወንድማቸውን ያጡት በዚህ አጋጣሚ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ዚያድ የድሮ ጓደኛቸው የሶማሌ ክልልን ለመምራት ይመረጣሉ የሚል ቅድሚያ ግምት አልነበራቸውም። "አልጠበቅኩም። እሱ የውጪ ሰው ነው። የፓርቲ አባልም አልነበረም" ይላሉ። አቶ ሙስጠፋ ከዚህ ቀደም ክልሉን ይመሩ የነበሩት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁ የለውጥ አቀንቃኝ ነበሩ። በክልሉ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚያጋልጡ የቀድሞውን አስተዳደር
የሚሞግቱ ጽሁፎች በሶማሊኛ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ሲፅፉ ቆይተዋል። በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይም የጎላ ተሳትፎ ነበራቸው።

የሶማሌ ክልል ፖለቲካን በቅርብ የሚከታተሉት አቶ ዚያድ ተመራጩ ፕሬዝዳንት በርካታ እና ውስብስብ የቤት ሥራ እንደሚጠብቃቸው አልዘነጉም። "የሕግ የበላይነት፣ ሰላም እና መረጋጋት መምጣት አለበት። ሥራ አስፈፃሚው፣ ሕግ አውጪው እና ሕግ ተርጓሚው ሪፎርም ይፈልጋል" ይላሉ አቶ ዚያድ።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ (DW Amharic)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

ሰባት የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሃይል አባላት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ #መገደላቸው ተገለፀ።

በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰላም አስከባሪ ሃይሉ ከመንግስት ሃይሎች ጋር በመተባበበር አዲኤፍ በተባለው አማጺ ቡድን ላይ በከፈቱት ጥቃት ወቅት ሰባት የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሃይል አባላት መሞታቸው ነው የተገለጸው፡፡

#የኢቦላ በሽታ ተጠቂ የሆነው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኒ ግዛትን ከአማፂ ቡድኑ ነጻ ለማድረግ በተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሃይል እና የመንግስት ወታደሮች በጋራ ዘመቻ ማድረጋቸውን የተባበሩት መንግስታት ቃል አቀባይ #ስቴቨን_ዱጃሪክ አስታውቀዋል፡፡

በዘመቻው አስር የሚሆኑ የሰላም አስከባሪ ሃይሎች መቁሰላቸውን እና አንድ ሰላም አስከባሪ መሰወሩን ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል፡፡

ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የአማፂ ቡድኑ በርካታ አባላት ተገድለዋልም ነው ያሉት፡፡

ከሞቱት የተባባሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሃይል አባላት ስድስቱ የማላዊ ተዋላጆች ሲሆኑ አንዱ ታንዛንያዊ ነው ተብሏል፡፡

በማዓድን ሃብታም የሆነው ምስራቃዊ የዲሞክራቲክ ኮንጎ አካባቢን ለመቆጣጠር አዲኤፍ የተባለ አማፂ ቡድንን ጨምሮ በርካታ ታጣቂዎች ከመንግስት ሃይል ይዋጋሉ፡፡

ምንጭ፦ አልጃዚራ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነቀምት🔝ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልልን ከኦሮሚያ በሚያዋስነው ድንበር ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት #መገደላቸው ተሰምቷል። የፖሊሶች አስክከሬን ነቀምት ከተማ ሲገባ ብዛት ያለው ህዝብ ሀዘኑንና ቁጣውን ገልጿል። በጥቃቱ የተገደሉ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት 17 እንደሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዴ.ሪ. ኮንጎ የሰው ህይወት ጠፋ‼️

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የምርጫ ውጤት ይፋ መሆንን ተከትሎ በተነሳ #ግጭት የሰው ህይወት አለፈ፡፡

በሃገሪቱ ደቡባዊ ምዕራብ በምትገኘው ኪክዊት ከተማ በተነሳ ግጭት ሁለት የፖሊስ ባልደቦችና ሁለት ንጹሃን ዜጎች #መገደላቸው ተነግሯል፡፡

ግጭቱ በሃገሪቱ የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ይፋ መሆንን ተከትሎ መነሳቱን ፖሊስ አስታውቋል።

በግጭቱ ከሞቱት በተጨማሪ 12 ዜጎች መቁሰላቸውም ነው የተገለጸው፡፡
በምርጫው ፌሊክስ ሺሴኬዲ አሸናፊ መሆናቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል።

ይሁን እንጅ የእርሳቸው ተፎካካሪ የሆኑትና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ድጋፍ አላቸው የሚባሉት ማርቲን ፋዩሉ ውጤቱን እንደማይቀበሉት ገልጸዋል። ይህን ተከትሎም ግጭት ተቀስቅሷል ነው የተባለው።

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከሁለት አመት መዘግየት በኋላ በተጠናቀቀው 2018 የመጨረሻ ቀን መካሄዱ ይታወሳል።

የምርጫው ውጤት ፀድቆ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የሚደረግ ከሆነ፥ ሃገሪቱ ነጻነቷን ከተጎናጸፈችበት የፈረንጆቹ 19 60 ወዲህ የመጀመሪያው ይሆናል።

ምንጭ፦ሲ ጂ ቲ ኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia