TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amahara በአማራ ክልል ከሚገኙ ከተሞች አንፃራዊ የሚባል ሰላም እና መረጋጋት የነበራት ባህር ዳር ዛሬ በተለያዩ አካባቢዎች በተኩስ ስትናጥ መዋሏን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ከስፍራው ዘግቧል። ምንም እንኳን ስለደረሰው ጉዳት የሚታወቅ ነገር ባይኖርም ትላንት ማታ ቦምብ የፈነዳ ሲሆን ዛሬ ቅዳሜ ከጥዋት ጀምሮ በተለይ  " ቀበሌ 14 " በሚባለው አካባቢ ላይ መንገዶች ተዘግተው ፤ የንግድና ትራንስፖርት እንቅስቃሴ…
#Amhara

በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ያለው ውጥረት አሁንም የቀጠለ ሲሆን በተለያዩ ቀጠናዎች ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ስለመኖራቸው ለማወቅ ተችሏል።

በክልሉ ባለው ግጭት እና ፍጥጫ የየብስ እና የአየር ትራንስፖርት ተስተጓጉሏል ፣ የኢንትርኔት አገለግሎት ተቋርጧል፣ አንዳንድ አካባቢዎች በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ናቸው።

" የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ " ዋና ሰብሳቢ እና የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አግልግሎት ዳይሬክትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ትላንት እሁድ በሰጡት ማብራሪያ፤ በአማራ ክልል የተጣለውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስፈጽመው ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ሕግ የማስከበር ሥራውን በማከናወን ክልሉን ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው በአጭር ጊዜ እንዲመለስ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

አቶ ተመስገን ፤ አማራ ክልል የተከሰተው በትጥቅ የታገዘው እንቅስቃሴ " የክልሉን መንግሥት በማፍረስ ወደ ፌደራል መንግሥቱ የሚዞር ግብ ያለው " ነው ብለዋል።

በክልሉ የተለያዩ ክፍሎች ሕገወጥነት ተከስቷል ያሉት ሰብሳቢው ፤ " የተደራጁ ዘራፊ ቡድኖች " ሲሉ የጠሯቸው አካላት በክልሉ ውስጥ የዞን እና የወረዳ ከተሞችን #ተቆጣጥረው የፍትሕ እና የሕዝብ ተቋማት አገልግሎት እንዳይሰጡ ከማስተጓጎል ባሻገር " በአንዳንድ አካባቢዎች ማረሚያ ቤቶችን ሰብረው ወንጀለኞችን እንዲያመልጡ እስከማድረግ የደረሰ ውንብድና ፈጽመዋል " ብለዋል።

በክልሉ ሕግ እና ሥርዓትን ለማስከበር እንዲሁም የመንግሥት እና የፓርቲ መዋቅርን የማጠናከር ሥራዎችን ለማከናወን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ክልሉን በአራት ኮማንድ ፖስቶች ማዋቀሩን አስታውቀዋል።

• የመጀመሪያው የምዕራብ አማራ ኮማንድ ፖስት ፦
- ምሥራቅ እና ምዕራብ ጎጃም
- ደብረ ማርቆስ ከተማ፣
- የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን
- ባሕር ዳር ከተማ ያሉበት ነው።

• ሁለተኛው የሰሜን ምዕራብ አማራ ኮማንድ ፖስት ፦
- ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር
- ጎንደር ከተማ
- ደብረታቦር ከተማ የሚገኙበት ነው።

• ሦስተኛው ኮማንድ ፖስት ማዕከላዊ ሸዋ ፦
-  ሰሜን ሸዋ፣
- የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን
- ደብረ ብርሃን ከተማን ያካተተ ነው።

• አራተኛ የምሥራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት ፦
- ኮምቦልቻ እና ወልዲያ ከተሞች - ሰሜን እና ደቡብ ወሎ
- ዋግ ኽምራን ያካተተ መሆኑን የዕዙ ሰብሳቢ ገልጸዋል።

አቶ ተመስገን ፤ በክልሉ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር እና የሚነሳ የትኛውንም ጥያቄ መንግሥት #በሰላም_ምላሽ_ማግኘት_አለበት ብሎ በጽኑ እንደሚያምን የገለፁ ሲሆን ሕግ እና ሥርዓት የማስከበሩ ሥራም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በአማራ ክልል ፤ ባለፉት ጥቂት ወራት ተቃውሞና ግጭቶች የነበሩ ሲሆን ከሰሞኑን ግን ግጭቶቹ ተስፋፍተው ወደ ትልልቅ ከተሞች ደርሰዋል።

ከመንግሥት ፀጥታ ኃይል ጋር ግጭት ውስጥ የገቡት የፋኖ ታጣቂዎች ፤ በተለይ " ከአማራ ልዩ ኃይል መፍረስ ጋር በተያያዘ የ #አማራ_ህዝብ እና #ክልልን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ውሳኔ ነው የተወስነው ፤ ሌሎችም የህልውና ጥያቄዎች አሉብን " በማለት ወደ ግጭት መግባታቸው ይነገራል።

@tikvahethiopia