TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኦሮሚያ #ትኩረት

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች አሁንም በቀጠለው የፀጥታ ችግር በርካቶች ህይወታቸው እያለፈ ፣ አካላቸው እየጎደለ፣ ንብረታቸው እየወደመ እንደሚገኝ ቤተሰቦቻችን ጠቁመዋል።

ባለፉት ዓመት ህዝቡ በሰላም እጦት ብዙ ቢሰቃይም መፍትሄ ሳይገኝ አሁንም እየተባባሰ በመቀጠሉ ንፁሃን ክፉኛ እየተጎዱ እና ስቃያቸውም እየተባባሰ እንደሚገኝ ነው ቤተሰቦቻችን የገለፁት።

ከጥቂት ቀን በፊት የፀጥታ ችግር ባለባቸው በወለጋ የተለያዩ አካባቢች ላይ #ንፁሃን እንዲጠበቁ ፣ የህዝቡ ስቃይ ትኩረት ባለማግኘቱ የሰሜን ክፍሉን ያህል ትንሽ እንኳን ትኩረት እንዲሰጠው እና ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈለግ ቤተሰቦቻችን ተማፅኖ ማሰማታቸው አይዘነጋም።

ከሰሞኑን በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙት ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጃርዳጋ ጃርተ ወረዳ እና በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ውስጥ በርካቶች ህይወታቸው አልፏል፣ ንብረታቸው ወድሟል ፣ #ሰላምን_ፍለጋ ሸሽተው ወደ ሌሎች አካባቢዎችም መግባታቸውን ለመስማት ችለናል።

አንድ የቤተሰባንች አባል ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ፤ " ለንፁሃን ጭፍጨፋ ፣ ለንብረት ውድመት ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ተጠናቂነት መኖር አለበት " ብሏል።

" እውነት መንግስት / አስተዳዳሪ ነኝ ፤ የህዝብንም ደህንነት አስጠብቃለሁ የሚል ካለ የትኛው አካል ለሚፈጠሩት ችግሮች ምክንያትና መንገድ እየሆነ እንዳለ ፣ ማን ግፍ እየፈፀመ እንዳለና ለዚህም ድርጊት ተባባሪ እየሆነ እንዳለ ምርመራ በማድረግ ማሳወቅ አለበት ፤ በየዕለቱ ሰዎች እየረገፉ ፣ እየተፈናቀሉ ፣ እየተራቡ እያዩ ዝም ያሉት ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ከእንቅልፋቸው ነቅተው መፍትሄ እንዲመጣ ንፁሃንን ከሞት እንዲድኑ ድምፃቸውን ማሰማት መቻል አለባቸው ። " ብሏል።

የመንግስት ዋናው ስራ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ፤ ከየትኛውም የታጠቁ አካላት የሚደርስን ጥቃት መከላከል ፣ አጥፊዎችን መቅጣት ነው ይህን ማድረግ ባይቻል እና ንፁሃን ቢጎዱ ተጠያቂነት መኖር አለበት ሲል አክሏል።

በኦሮሚያ ክልል ባለው ፀጥታ ጉዳይ ፤ በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚታዩ ችግሮች መኖራቸውን ይህም በተደጋጋሚ መገለፁን ነገር ግን እስካሁን መፍትሄ እንዳልተገኘለት ገልጿል።

" ህዝብ መንግስት አለኝ ሚለው ደህንነቱ እንዲጠበቅ እንጂ በየዕለቱ ያለበት ችግር እየተባባሰ ህይወቱን እያጣ፣ እጅግ ደክሞ ያፈራው ንብረቱ እየወደመበት እንዲቀጥል አይደለም " ያለው ይኸው የቤተሰባችን አባል ባለፉት ጊዜያት እሱን ጨምሮ ቤተሰቦቻቸው በግጭት ቀጠና ውስጥ ያሉ ወገኖች ያሳለፉት ስቃይ በቃላት የሚገለፅ እንዳልሆነ አስረድቷል።

በኦሮሚያ ውስጥ የፀጥታ ችግሮች ባለባቸው ቦታዎች ስለሚደርሰው ስቃይ ብዙ ቢነገርም መፍትሄ ሳያገኝ ዛሬም የሰዎች ህይወት እየተቀጠፈ እንደቅጠል እየረገፈ ይገኛል።

የአንድ ሀገር ዜጎች ህይወታቸው በግፍ እየረገፈ እየታየ ለችግሩ መፈጠር በተለያዩ አቅጣጫዎች የተለያዩ ምክንያቶች እየተደረደሩ ፣ ጥላቻዎችም እየተሰበኩ፣ ሁኔታዎችም #ከመሻሻል ይልቅ ክፉኛ እየተባባሱ ቀጥለዋል።

ህዝቡ ሰላም ርቆት፣ ኢኮኖሚው ደቆ፣ አርሶ እንዳይበላ ሆኖ፣ እየታፈነ ሚሊዮኖች እየተጠየቀበት ፣ መውጫ እና መግቢያ አጥቶ ፣ የሚወዳቸውን እየተነጠቀ፣ ዓመታትን በገፋበት የግጭት ቀጠናዎች መፍትሄ እንዲያገኝ ግፊት ማድረግ እንደሚገባ ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia