TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እግር ኳስ ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለአንድነት፣ ለአብሮነት፣ ለሀገር ግንባታ!

#ባህርዳር_ከነማ
#መቐለ70_እንደርታ

PHOTO : ጋንታ መቐለ 70 እንደርታ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ባህርዳር

የባህር ዳር ቲክቫህ አባላት ከለሊት 7:40 አካባቢ ሶስት ጊዜ የፍንዳታ ድምፅ እንደሰሙ ገልፀዋል።

አባላቶቻችን ከዚህ ቀደም የሰሙት አይነት ተመሳሳይ ፍንዳታ እንደሆነም ነው የገለፁት።

ፍንዳታውን ተከትሎ የተኩስ ድምፅ እንደነበርም ገልፀዋል።

ዝርዝር መረጃ በሚመለከታቸው አካላት ሲገለፅ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
* 2 የችሎት ጉዳዮች !

#አዲስ_አበባ

የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠ/ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራን በመግደል በፍ/ቤት ጥፋተኛ የተባለው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በሞት እንዲቀጣ ጠይቋል።

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዛሬ አርብ ጥያቄውን ያቀረበው የአስር አለቃ መሳፍንትን የክስ ሂደት ለሚመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። 

ዐቃቤ ህግ ዛሬ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ባለ 3 ገጽ የቅጣት አስተያየት፤ በተከሳሹ ላይ ሶስት የቅጣት ማክበጃዎችን ጠቅሷል።

የተከሳሽ ጠበቆች ፥ ተከሳሽ ከዚህ በፊት የወንጀል ሪከርድ የለበትም ብለዋል። ዐቃቤ ህግ “አንድም [የወንጀል] ሪከርድ ሳያቀርብ የሞት ፍርድ መጠየቁ ከህጉ ያፈነገጠ ነው” ሲሉ የአቃቤ ህግን የቅጣት አስተያየት ተቃውመዋል። 

ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለሰኔ 21 /2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በዝርዝር ያንብቡ : telegra.ph/Ethiopia-Insider-06-18

#ባህርዳር

ዛሬ አርብ ማለዳ የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት የዋለው ችሎት በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ እጃቸው አለበት የተባሉ 55 ተከሳሾች ላይ ብይን ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ በሻምበል መማር ጌትነት የክስ መዝገብ ስማቸው የተዘረዘሩ 55 ተከሳሾች ውስጥ 6ቱ በሌሉበት፣ 49 በተገኙበት ፍርዳቸው ሲታይ የነበረ ሲሆን ዛሬ ፍርድ ቤቱ 20ዎቹን በነጸ አሰናብቷል።

በነጻ እንዲሰናበቱ ከተበየነላቸው ተከሳሾች መካከል አቶ ዘመነ ካሴ ይገኙበታል።

በዝርዝር ያንብቡ : telegra.ph/BBC-06-18-2

መረጃዎቹ ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር እና ከቢቢሲ የተውጣቱ ናቸው።

@tikvahethiopi
ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው ..

- ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣
- የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ
- የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ
- ወልዲያ
- ሪፍትቫሊ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት እያስመረቁ ነው።

#ባህርዳር_ዩኒቨርሲቲ

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 363 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ተማሪዎቹ በመደበኛ፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሐ-ግብሮች፤ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በሶስተኛ ዲግሪ እና የስፔሻሊቲ ህክምና የሰለጠኑ ናቸው።

#አሶሳ_ዩኒቨርሲቲ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 237 ተማሪዎችን ነው በማስመረቅ ላይ የሚገኘው።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ለ8ተኛ ጊዜ ሲሆን የዛሬዎቹ ተመራቂዎች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።

#የኢትዮጵያ_ሲቪል_ሰርቪስ_ዩኒቨርሲቲ

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲም በተለያየ የትምህርት መስኮች በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሐ-ግብሮች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ ዲግሪ እና በፒ.ኤች.ዲ የተማሩ ናቸው።

ከእለቱ ተመራቂዎች ውስጥ 153 የሚሆኑት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በውጭ ግንኙነት ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሰለጠኑ እጩ ዲፕሎማቶች ናቸው።

#ወልዲያ_ዩኒቨርሲቲ

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2,537 ተማሪዎችን አስመርቋል።

#ሪፍትቫሊ_ዩኒቨርስቲ

የሪፍትቫሊ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 16, 967 ተማሪዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም አስመርቋል።

መረጃው የetv ነው።

@tikvahethiopia
#Bahirdar

በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ ማታ ማታ የሚኒቀሳቀሱ ባጃጆች ቁጥር እንዲወሰን ተደረግ።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ወንጀል እንዳይከሰት ለመቆጣጠር ያመች ዘንድ እንደሆነ ተነግሯል።

እንደሀገር ሆነ እንደ ክልል የተከሰተውን የፀጥታ ሁኔታ በተገቢ መንገድ ለመምራት በባህር ዳር በህጋዊ መንገድ ተደራጅተው የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የባጃጅ ማህበራት ከከተማ አስተዳደሩ ትራንስፖርት ጽ/ቤት፣ ከፖሊስና መሰል የህግና የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በሌሊት አገልግሎት የሚሰጡ ባጃጆች ተጠያቂነት ባለው አሰራር ታቅፈውና ለቁጥጥር እንዲያመች በቁጥር ተወስነው እንዲሰሩ መደረጉን የየማህበራቱ አስተባባሪዎች ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሰረት ከስምንት የባጃጃ ማህበራት ውስጥ በስነ-ምግባር እና ለማህበረሰቡ ቅንና ታማኝ አገልግሎት ከሚሰጡ የባጃጅ አሽከርካሪዎች መካከል 120ዎችን በመመልመልና ከምሽቱ 3፡00 እስከ ንጋት 11፡00 ድረስ በሁሉም ቀበሌዎች እየተንቀሳቀሱ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል።

ይህ ለከተማው ሰላምና፣ ለማህበረሰቡ ደህንነት ሲባል የሚደረግ በመሆኑ የተመደቡ ባጃጆች ተጠያቂነት እንዲኖራቸው የማህበራቸውን ስምና አንፀባራቂ የደንብ ልብስ እንዲጠቀሙ፣ በዚያው ሰርጎ ገቦችን በመቆጣጠር በኩል ለሚደረገው ተግባር ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ መደረጉንም ገልፀዋል፡፡

ለዚህ ከተመደቡ ውጭ ማነኛውም ባጃጅ ከ3 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ እንደሌለበትና ይህን ውሳኔ ተላልፎ የተገኘ የባጃጅ አሽከርካሪ ካለ በህግ ይጠየቃል ተብሏል።

የተመደቡት 120 ባጃጆች ያለምንም ዋጋ ጭማሪና ያለ አድሎ በሌለበት ሁኔታ እንዲሰሩ በሚሰጡት አገልግሎትም እጥረት ካለ እየተገመገመ እንደሚስተካከል ከ #ባህርዳር_ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#ባህርዳር

ነገ ባህር ዳር ከተማ የኢትዮጵያ እና የዚምባቡዌ የእግር ኳስ ፍልሚያን ታስተናግዳለች።

ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ወደጋና አቅንታ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት መሸነፏ ይታወሳል፤ የነገው ጨዋታ ሁለተኛው የማጣሪያ ጨዋታ ነው።

ይህን ጨዋታ የምታስተናድገው ደግሞ ውቢቷ ባህር ዳር ከተማ ናት።

የነገው ጨዋታ ኮሚሽነር ከኤርትራ ፤ የዳኞች ገምጋሚ ከኮትዲቫር ፤ አራቱም የጨዋታ አመራሮች ከሲሼልስ ናቸው።

በነገው ፍልሚያ ብሄራዊ ቡድናችን የተለመደውን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የሚለብስ ይሆናል።

የኢትዮጵያና የዚምባቡዌ ብሄራዊ ቡድኖች በነገው እለት የሚያደርጉት ጨዋታ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለካፍ ጥያቄ ቢያቀርብም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፍቃደኛ ባለመሆኑ ጨዋታው ያለተመልካች እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ምሽት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ሀዋሳ #ድሬዳዋ #ባህርዳር

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የማለዳ በረራ ጀመረ።

አየር መንገዱ ከሀዋሳ ፣ ከድሬዳዋ እና ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ማለዳ 1:00 የሚነሱ እለታዊ በረራዎች መጀመሩን አሳውቋል።

#EthiopianAirlines

@tikvahethiopia
#ባህርዳር_ዩኒቨርሲቲ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና ለኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ ነው።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትንና ያስተማሩትን በተግባር ለሚኖሩት፤ ሰውን በሰውነቱ ብቻ ላከበሩት ታላቁ ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ እና  ኢትዮጵያን ብሎም አፍሪካን በስፖርቱ ዓለም በማስጠራት ጀምራ ለኅብረሰተብ ፍቅርና አንድነት መጎልበት ለምትተጋው ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የዓመቱን የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ መሆኑን ዛሬ አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው የክብር ዶክትሬቱን የሚያበረክተው ነሐሴ 21 ቀን 2014 በሚያካሂደው የተማሪዎች ምረቃ ላይ ነው።

@tikvahethiopia
#ባህርዳር

ኮማንደር ዋጋዉ ታረቀኝ በጥይት ተመተው ተገደሉ።

በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ኀላፊ ኮማንደር ዋጋዉ ታረቀኝ በጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል።

እንደ #አማራ_ፖሊስ መረጃ ኮማንደር ዋጋው ፤ ፀጥታ እያስከበሩ በነበረበት ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት አካባቢ በአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ተመተው ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ባህርዳር

የአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር አስተማማኝ ሰላም እና መረጋጋት ላይ እንደምትገኝ የከተማው የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ለአሚኮ በሰጠው ቃል አሳውቋል።

ከተማዋ የተለያዩ ሁነቶችን በሰላም እያስተናገደች መሆኑን እና #ለመስቀል_በዓል እንዲሁም #ለጣና_ፎረም ዝግጅት እያደረገች መሆኑን መምሪያው ገልጿል።

መምሪያው የተለያዩ አካላት የከተማውን ሰላም በተመለከተ የሚያራግቡት ወሬ ሀሰተኛ እና መሰረተቢስ በተጨማሪም የባህር ዳርን ህዝብ የሚወክል አይደለም ብሏል።

የከተማው የፀጥታ ኃይል ከተማውን በንቃት እየጠበቀ ነው ፤ ሌት ተቀን ፓትሮል ያደርጋል፣ የኬላ ጥበቃዎችም አሉ ፣ ፍተሻም አለ የመንደር ጥበቃዎችም በተጠናከረ ሁኔታ ነው ያሉት ሲል አሳውቋል።

ትላንት ለሊት 6 ሰዓት ገደማ የባህር ዳር ፖሊስ መምኢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ዋጋው ታረቀኝ በጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

ምንድነበር የተፈጠረው ?

የባህር ዳር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አትንኩት አያለው ስለ ኮማንደር ዋጋው ታረቀኝ ህልፈት ለአሚኮ የተናገሩት ፦

" ትላንት እኔ አባይ ማዶ ነበርኩ እሱ ምክትል ኃላፊ ስለሆነ በተባበሩት አቅጣጫ ነበር።

ጥይት ተተኩሶ ሲደርስ በአጋጣሚ እዛ አካባቢ የሚጠጣ በጣም የሰከረ ሰው አግኝቷል። ማነው የተኮሰ ? ሲባል እኔ ነኝ የተኮስኩት ነው የሚለው ፤ የታጠቀ አካል ነው።

ለመታወቂያ ተባበረኝ ሲለው በጣም ሰክሮ ስለነበር በመመላለስ ላይ እያለ ጥይት ተኩሶ መታው ፤ በኃላም ሆስፒታል ከገባ በኃላ ህይወቱ አልፏል።

ከዛ በኃላ በደረሰን ጥቆማ መሰረት ሰውየውን ተከታትልነው ፤ ተከትለን ቁም ሲባል እኛ ላይ በከፈተው ተኩስ ፤ በተኩስ ልውውጥ ሰውየው እጁን አልሰጥም ብሎ ህይወቱን አጥቷል። "

@tikvahethiopia
#ባህርዳር

ትላንትና ከምሽቱ 1:40 ገደማ በባህር ዳር ከተማ በተለምዶ " አባይ ማዶ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ዳያስፖራ በሚወስደው አስፓልት መንገድ መገንጠያ ላይ በሚገኝ የምግብ እና መጠጥ መሸጫ የንግድ ተቋም ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ 3 ሰዎች ሲሞቱ 10 ሰዎች ቆስለዋል።

የቦምብ ፍንዳታው ከተፈፀመበት ቦታ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘው የአዲስ ዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ተወካይ ዶ/ር ምትኩ ተገኝ ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፥ " በትላንትናው ዕለት በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ ወደ ሆስፒታላችን  15 የሚሆኑ ታካሚዎች መጥተዋል ፤ ከዚያ ውስጥ ሶስት እንደደረሱ የሞቱ ነበሩ፣ 2 ታክመው ወደቤታቸው ሄደዋል ፤ አንደኛው ሪፈር ተፅፎለታል ወደ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ሌሎቹ ግን እዚህ በእኛ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው ፤ አጠቃላይ ዘጠኝ ናቸው። " ብለዋል።

ለሬድዮ ጣቢያው ቃላቸውን የሰጡት አንድ የአይን እማኝ ፥ " ለሁለት ሃያ ጉዳይ ነው፤ እንደፈነዳ ወጣ ከዛም ስናይ ሁለት ሰው ወድቋል ፤ ልዩ ኃይል እና ፖሊስ መጥተው አነሷቸው ፤ ከዛ ውጭ እኛንም በተኑን ወደቤት ግቡ አሉን ገባን። ቦንቡን የጣለው አካል አይታወቅም ልክ ፈነዳ እዛው አካባቢ ያለው ሰውም አላወቀውም ከየትኛው አካል ይጣል የመንግስት አካል ይጣለው ፣ ግለሰብ ይጣለው አይታወቅም። ጥዋት ስንጠይቅ ጎረቤት ያሉ ሰዎችን 4 ሰው ሞቷል ሌሎች ቁስለኛ ናቸው አሉ። የወደቁ ሰዎችን የልዩ ኃይል እና ፖሊስ አባላት ናቸው መጥተው ያነሱት ፤ ሁኔታውንም ያረጋጉት " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው አስረድተዋል።

በትላንትናው የቦምብ ፍንዳታ ህይወታቸው ያለፈው በሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ የነበሩ ወጣቶች እንደነበሩ የአይን እማኙ ገልጸዋል።

ከክልል ልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት ውሳኔ ጋር በተያያዘ በባህር ዳርም ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን ከትላንት ጀምሮ እንደ ሆስፒታል፣ ባንክ የመሰሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በቀር ሌሎች የንግድ ተቋማት ስራ ማቆማቸውን ቪኦኤ ሬድዮ ከባህር ዳር ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#ባህርዳር

የባህር ዳር ከተማ የእስልምና ምዕመናን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው የመስገጃ ቦታ ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱ ተሰማ።

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ለእስልምና እምነት ተከታዮች ለመስገጃ የሚሆን 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ መሰጠቱን ዛሬ አስታውቋል።

የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ዛሬ የኢድ አልፈጥር በዓል በባህር ዳር ስታዲየም በሚከበርበት ወቅት ነው ይህንን የምስራች ለምዕመኑ ያበሰሩት።

ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ምን አሉ ?

" ለብዙ ጊዜ ስትጠይቁት የነበረ የመስገጃ ቦታ አሁን በክልልም ፀድቆ የመጣ ስለሆነ ምናልባትም በሚቀጥለው ዓመት በደንብ ሰርታችሁት እዚህ ሳይሆን እዛው ከተፈቀደላችሁ ቦታ ላይ የምታከብሩት ይሆናል።

ክልሉ ያቀረባችሁትን ጥያቄ እኛ አፅድቀን ልከን ክልሉም ተቀብሎት 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ የኢድ አልፈጥር በዓል የምናከብርበት ቦታ ተፈቅዷል። "

ከንቲባው ይህንን ንግግራቸውን ሲያደርጉ የባህር ዳር ከተማ ሙስሊም ምእመን እጅግ በደስታ ስሜት " አላሁ አክበር ! አላሁ አክበር ! አላሁ አክበር ! " እያለ ድምፁን አሰምቷል።

@tikvahethiopia
#ባህርዳር

የአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ በጀግኖች አርበኞች ስም መንገድ ሰየመች።

82ኛው የጀግኖች አርበኞች ቀን በባሕር ዳር ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ዛሬ ተከብሯል።

በዚህም በባሕር ዳር ከተማ " ከገጠር መንገድ እሰከ ኤርፖርት " ያለው መንገድ በጀግኖች አርበኞች ስም መሰየሙን በአማራ ክልል የጀግኖች አርበኞች ማህበር አሳውቋል።

ዛሬ በነበረው ዝግጅት የአማራ ክልል የጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዜዳንት ዳኝነት አያሌው ተከታዩን መልዕክት አስተላልዋል ፦

" ለሀገር በመስዋዕትነት  ከፍለው ሀገር ያጸኑ ጀግኖችን መዘከር ይገባል።

' ጀግናን መፍጠር ጀግናን ከማክበር ይጀምራል' የሀገርን ነጻነት፣ የሀገርን ሉዓላዊነት ያጸኑ ጀግኖቻችን እንኮራባቸዋለን፣ እናከብራቸዋለን።

የዚህ ዘመን ትውልዶች ከድል ታሪኩ በመማር በመከባበር፣ በመደጋገፍ ፣በአንድነት ሀገርን ማጽናት ይገባናል።

በአንድ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ በመተባበር ሀገርን ማሻገር ይገባል። ' ሀገሩን የማያውቅ ከብዙ ሴቶች መካከል እናቱን ለይቶ የማያውቅ ሕጻን እንደማለት ነው ' እና ሀገራችን በምንና እንዴት እንደቆመች መረዳት ይገባናል።

በሚጠበቅብን ዘርፍ ሁሉ የአርበኝነት ሚናችን መወጣት ይገባል። "

#AMC

@tikvahethiopia
#ባህርዳር

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርእሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ልዑክ ባሕር ዳር ገባ።

ልዑኩ በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) እና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ እና ልዑካቸው በቆይታቸው ከርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) እና ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች ጋር  በሁለቱ ክልሎች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Credit ፦ አሚኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update #ባህርዳር

" ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን ልዩነቶቹ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በታች ናቸው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

" ልዩነቶችን በሕግ፣ በሠላም እና በመነጋገር ለመፍታት የአማራ ሕዝብ ፍላጎት አለው " - ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

ባህር ዳር የሚገኙት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ልዑካቸው ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ጋር እንዲሁም ከህብረተሰቡ ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በዚህ ውይይት ላይ አቶ ጌታቸው ረዳ " ዋጋ የማይጠይቅ የሠላም አማራጭ ሳለ በፖለቲከኞች የጠብ ርሃብ ምክንያት በርካታ ጉዳቶች ተከስተዋል " ብለዋል፡፡

" ልዩነቶች ቢኖሩ እንኳን ልዩነቶቹ ከአማራ እና ትግራይ ሕዝብ በታች ናቸው " ያሉ ሲሆን " አሁን የጦርነትን ምዕራፍ ዘግተን የሠላም አማራጮችን የምናይበት ጊዜ ነው " ብለዋል፡፡

" የሁከት እና ግርግር አጀንዳዎች የሚታያቸው ይኖራሉ፤ ነገር ግን ለሕዝብ ካሰብን እና ከሠራን ከሠላም ውጭ የተሻለ አማራጭ የለንም " ሲሉ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በበኩላቸው ፤ " ልዩነቶች ይኖራሉ  ያሉትን ልዩነቶችን ግን በሕግ፣ በሠላም እና በመነጋገር መፍታት የአማራ ሕዝብ ፍላጎት ነው ብለዋል።

" የአማራ ክልል ሕዝብ እና መንግሥት ለሠላም አማራጮች ዝግጁ ነው " ሲሉም ተደምጠዋል።

" የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ ወደ ቀደመው ሁኔታው መመለስ አለበት፣ ትራንስፖርት እና የንግድ እንቅስቃሴ መጀመር ይኖርበታል " ያሉት ዶ/ር ይልቃል " ተከባብረን እና ተደማምጠን ልዩነቶቻችን ለመፍታት መሥራት ይጠበቅብናል " ብለዋል።

የፖለቲካ አመራሩ የጀመረውን የሠላም ግንኙነት የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች በተለይ ደግሞ አዋሳኝ አካባቢ ያሉ የሁለቱም ክልል ሕዝቦች አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

Via AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ባህርዳር #ጎንደር

ባህር ዳር ከተማ ከትላንት ለሊት ጀምሮ ዝምታ ሰፍኖባት እንደምትገኝና ዛሬ የሟቾች ስርዓተ ቀብር ሲፈፀም እንደነበር ነዋሪዎቿ ተናግሩ።

ባለፉት ቀናት በከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ስትናጥ የነበረችው ባህር ዳር ከተማ ከለሊት ጀምሮ ፀጥ ብላ መዋሏን ነዋሪዎች መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፤ ዛሬ በባህር ዳር በግጭቱ የሞቱ ሰዎች ስርዓተ ቀብር ሲፈፀም መዋሉን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል።

ትላንት በቀበሌ 13 ፣ 14 እና 16 በነበረ ውጊያ በርካታ ሰዎች #መሞታቸው እና #መጎዳታቸው ተነግሯል። እነዚሁ ሟቾች ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ በተለያዩ ስፍራዎች ሲፈፀም ውሏል።

ነዋሪዎቹ በጦርነቱ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈው አብዛኞቹ ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች መሆናቸውን ገልጽዋል።

የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP) ያነጋገራቸው ሁለት ዶክተሮች በውጊያው ሰላማዊ ሰዎች ስለመገደላቸው ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ የባህር ዳር ነዋሪዎች ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ሬድዮ በሰጡት ቃል ከከተማው ማረሚያ ቤት 2 ሺህ የሚጠጉ ታራሚዎች ሲወጡ መመልከታቸውን ጠቁመዋል።

በጎንደር ዳግሞ ዛሬ ከሰሞኑን የተሻለ መረጋጋት እንዳለ ነዋሪዎች ገልጸዋል። የመንግሥት ጦር በከተማው ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን የተደረደሩ ድንጋዮችን ሲያነሱ መዋላቸውን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተጨማሪ

የባህር ዳር ፣ ጎንደርና ሸዋሮቢት ነዋሪዎች ምን አሉ ?

የባህር ዳር ፣ ጎንደር ፣ ሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች ከተማቸው በመከላከያ ሰራዊት ስር እንደሚገኝና ዛሬ ተኩስ እንዳልነበር ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

#ባህርዳር

ነዋሪ 1

" ከትለንት ከግማሽ ለሊት በኃላ መከላከያው ተቆጣጥሮታል።

ተኩስም የለም፤ መከላከያው ተቆጣጥሮታል። አንፃራዊ ሰላም አለ።

መከላከያው ነው እየተንቀሳቀሰ ያለው። ሰውም እንደ ሰሞኑን ሳይሆን መንቀሳቀስ ጀምሯል። ግን አገልግሎት መስጫ ተቋማት ዝግ ናቸው በተረፈ ቁስለኛ እየተነሳ ሃኪም ቤት እየሄደ ነው ፣ የሞተውም እየተቀበረ ነው።

ዘንዘልማ አካባቢ ብዙ ሰው ስለሞት እነሱ እየተነሱ እየተቀበሩ ነው። ከሟቾች ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ የተወሰኑ ናቸው እንጂ በቤተሰብ አማካኝነት እዛው እየተቀበረ ነው። ብዛት ያለው ሰው ደግሞ ከመኮድ ይወረወር የነበረ ከባድ ተወዋሪ መሳሪያ እሱ ነው ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው። መኖሪያ ቤት ላይ እየወደቀ፤ ህፃናቶችም ሞተዋል።

ቁጥሩን ባልገልፅም ብዙ ሰላማዊ ሰው ሞቷል፣ በተለይ ቀበሌ 14 ላይ ከፍተኛ ውጊያ ነበር፤ በጣም ብዙ ሰው ሞቷል። ዛሬ ብዛት ያለው ሰው ቀብር ነው የዋለው። ህዝቡ እየወጣ መቅበር ጀምሯል። "

ነዋሪ 2

" እኛ ኤርፖርት አካባቢ ነን። ዛሬ ሰላም ነው። ተኩስም የለም። የተረጋጋ ነው። ግን ብዙ ሰው ፍራቻ ስላለው ወደ ከተማ አይሄድም። በጣም ብዙ የሞተ ሰው ስላለ ፍራቻ አለ። ነገር ግን ከንጋት ጀምሮ ምንም ድምፅ የለም።

በአብዛኛው ሲቪልያን ነው የሚሞቱት ካለመሳሪያ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ፣ የሚታኮሱት አይደለም የሚሞቱት በብዛት። ጀሌው አለ አይደል በአጋጣሚ መንገድ ለመዝጋት የሚሄደው ነው። "

#ጎንደር

ነዋሪ 1

" ጎነደር ከትላንት ማታ ጀምሮ ማለት ይቻላል ተኩሱ ቆሟል። መከላከያው ከተማው ውስጥ ያሉትን መንገዶች የማፅዳት ስራ እየሰራ ነው ያለው። መንገዶች በድንጋይም፣ በእንጨትም ተዘጋግተው ስለነበር።

ሌሎች እንቅስቃሴዎች ገና ናቸው። የሰው እንቅስቃሴም የለም። ቤት ውሥጥ ቁጭ ብለን ነው የሰነበትን ዛሬ ሳምንታችን ነው። የሚቀጥለው ምን እንደሚሆን እየጠበቅን ነው።

በትክክል ስለደረሰው ጉዳት ይህ ነው ማለት ባልችልም፤ ሰው ግን ለሳምንት ከገበያ ከሌሎችም አገልግሎቶች ተገልሎ መቆየቱ ብዙ ሰው አላሰበውም እሮብ ማታ ድረስ ጤናማ ስራውን እየሰራ ከዚያ ምሽት በኃላ ግን መውጣት መግባት  የማይቻልበት፣ የጥይት ድምፅ የከባድ መሳሪያ ሲስተናገድ ነበር ወደ ህክምና ለመሄድም ትራንስፖርት የለም ጉዳቱ ቀላል አይሆንም። "

ነዋሪ 2

" ዛሬ ተኩስ የለም። ከተማ ውስጥ ምንም እንቅስቃሴ የለም። ከመከላከያ ውጭ የሚንቀሳቀስ የለም። ሰው ከቤት አልወጣም።

ሰላማዊ ሰዎች ብዙ ተጎድተዋል።

ህክምና ለማግኘትም አልተቻለም። ጉዳቱ ከመብዛቱ አንፃር እንዲሁም አንስቶ የሚወስድም አልተገኘም።

የሞቱ ሰዎች ትላንት አልፎ አልፎ ተቀብረዋል። ከሟች ብዛት አንፃር ያልተቀበሩ አሉ። "

በተመሳሳይ በሸዋሮቢት ከተማ ሀገር መከላከያ የገባ ሲሆን ዛሬ የተረጋጋ ሁኔታ መኖሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በግጭቱ ሳቢያ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውና መቁሰላቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ የሞቱ ሰዎች እየተለቀሙ ተቀብረዋል።

አንድ ነዋሪ እሳቸው ብቻ ባረጋገጡት 13 ንፁሃን እንደሞቱ ገልፀው ሚካኤል ቤተክርስቲያን 10 ሰው፣ ማርያም 2 ሰው፣ ሙስሊም መቃብር 1 ሰው መቀበሩን መረጃ እንዳላቸው ተናግረዋል። በየገጠሩ ያለው ገና አልታወቀም ሲሉ አክለዋል።

ትራንስፖርት አለመኖሩ፣ መንቀሳቀስም አስፈሪ ስለነበር ተጎጂዎችን ወደሆስፒታል ለመውሰድ አስቸጋሪ እንደነበር ነዋሪዎች ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#ባህርዳር

በአማራ ክልል መዲና በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ትላንት መጋቢት 29 የመግሪብ ሰላት ሰግደው ሲመለሱ የነበሩ አባት ከ3 ልጆቹ እንዲሁም አንድ ጎረቤታቸውን ጨምሮ አጠቃላይ 5 ሰዎች በተከፈተባቸው የጥይት እሩምታ መገደላቸው ተነግሯል።

ትላንትና ምሽት በግፍ የተገደሉት ፥ አቶ ሙሄ ፣ ልጃቸው አበባዉ ሙሄ ፣ ሽኩር ሙሄ ፣ ሙላት ሙሄ እና ጎረቤታቸው አቶ እንድሪስ የተባሉ ሲሆኑ ስርዓት ቀብራቸው በዛሬው ዕለት ተፈፅሟል።

እስካሁን ገዳዮች ስለመያዛቸው የተባለ ነገር የለም።

በከተማዋ ከተገደሉት ሰዎች ባሻገር ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ የሚገኘው መስጂድ ከፍተኛ የመሳሪያ ድብደባ እንደተፈፀመበት ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዛሬ የባህር ዳር ሙስሊሞች በክልሉ በሙስሊሞች ላይ አነጣጥረዋል ያሉትን ግድያ እና እገታ በመቃወም ሰልፍ ማድረጋቸውን " ሀሩን ሚዲያ " ዘግቧል።

እስካሁን በአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትም ሆነ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ አስተያየት የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በክልሉ ተፈፅመዋል ስለተባሉ ግድያዎች ፣ ጥቃቶች ፣ ዘረፋና እገታዎች የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና የሚመለከታቸው አካላትን ለማነጋገር ጥረት እያደረገ ይገኛል፤ ምላሽ እንዳገኘ ተጨማሪ መረጃዎችን ያቀርባል።

@tikvahethiopia