TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WFP #UN #Ethiopia #TigrayRegion

ዛሬ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፤ አልሚ ምግብን ጨምሮ ህይወት አድን ፍጆታዎችን የጫኑ 47 ተሸከርካሪዎች ወደ ትግራይ ጉዞ መጀመራቸውን አሳውቋል።

ከ47ቱ ተሽከርካሪዎቹ በተጨማሪ ለመሰረታዊ አገልግሎቶች የሚውል ነዳጅ የጫኑ 3 ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ።

ከሁሉም ባለስልጣናት በተደረገው ድጋፍ እስካሁን ጉዞው የተሳካ እና መልካም የሚባል እንደሆነ ጠቁሟል።

ለሰብዓዊነት ተብሎ ግጭት የማቆም ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ እስካሁን ድረስ ወደ 26 ተሸከርካሪዎች ብቻ ናቸው ወደ ክልሉ የገቡት።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በክልሉ በችግር ላይ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን የሰብዓዊ ፍላጎት ለማሟላት በየዕለቱ 100 ተሽከርካሪዎች ወደ ክልል መግባታ እንዳለባቸው ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል።

በሌላ መረጃ ፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት በ “any other business” ስር ዛሬ በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ በዝግ ይመክራል።

በስብሰባው ላይ የሰብአዊ ጉዳዮች ም/ ዋና ጸሃፊ ማርቲን ግሪፍትስ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የዛሬውን ስብሰባውን የጠየቁት የA3 የምክር ቤቱ አባላት (ጋቦን፣ ጋና እና ኬንያ) ናቸው። #በA3 ብቻ በኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ስብሰባ ሲጠየቅ ይህ የመጀመሪያው መሆኑን ተመድን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን አስነብቧል።

@tikvahethiopia