TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.44K videos
208 files
4.01K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ህዝበ ወሳኔ እንዲካሄድ🔝

የሲዳማ ብሔር ክልል ሆኖ #እንዲደራጅ በቀረበው ጥያቄ መነሻ የክልሉ ምክርቤት ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት ህዝበ ውሳኔ እንዲያገኝ ለኢፌድሪ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት መፃፉን የተረጋገጠ ሲሆን ደብዳቤው በነገው እለት ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ያደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ህገመንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት አስፈፃሚ ኮሚቴዎች #ሪፈረንደም ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮምኒኬሽን መምሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሪፈረንደም

" ህዝብ የሚያቀራርብ ሌላ መፍትሄ ካለ መጠቆምና መነጋገር ይቻላል " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ጥያቄ በሚነሳባቸው የአማራ እና ትግራይ አካባቢዎች ጉዳይ መንግሥት ይዞት ከመጣው መፍትሄ የተሻለና የተለየ መፍትሄ ያለው ማቅረብ ይችላል አሉ።

ዶ/ር ዐቢይ ፤ የፌደራል መንግስት በትግራይና አማራ ክልሎች አወዛጋቢ የሆኑ የወሰን ጉዳዮች #በህዘበ_ውሳኔ እንዲፈታ እንደሚፈልግ አሳውቀዋል።

ይህ የመፍትሄ ሀሳብ በክልሎቹ መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እንዲሁም አንዱ ተደስቶ ሌላው እንዳያኮርፍ የሚያደርግ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ለዚህም ፌዴራል መንግሥት ከሁለቱም ክልሎች አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጉንና አቅጣጫ አስቀምጦ እየሰራበት እንደሆነ ተናግረዋል።

" የህዝበ ውሳኔው / ሪፈረንደም ብቸኛ አማራጭ አይደለም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " የሁለቱንም ክልሎች ዘላቂ ሰላም የሚያመጣ፤ ህዝብ የሚያቀራርብ ሌላ መፍትሄ ካለ መጠቆምና መነጋገር ይቻላል " ብለዋል።

" የአማራ እና ትግራይ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ተወያይተው ዘላቂ ሰላም የሚያመጣ መፍትሄ አለን ካሉ በደስታ እንቀበላልን " ሲሉ ገልጸዋል።

" መንግሥት ሪፈረንደም ይደረግና በህግ መሰረት በአካባቢዎቹ ዘላቂ ሰላም ይስፈን ብሎ እየሰራ ነው ፤ ከዚህ ውጭ አማራጭ ያለው ያቅርብ " ብለዋል።

መፍትሄ መጠቆም ሳይቻል ግን በመንግስት የቀረበውን የመፍትሄ ሃሳብ አለመቀበል ግን ተገቢ አይደለም፤ ወደ ሰላም አይወስድም ፤ ለአንዱ ቢመለስም ለሌላው ጥያቄ ሆኖ ይቀጥላል ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#Puntland #Somalia

ፑንትላንድ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ይፋ አድርጋለች።

ከፊል ራስ ገዝ የሆነችው #ፑንትላንድ በሞቃዲሾ ለሚገኘው ለሶማሊያ የፌደራል መንግሥት ከዚህ ቀደም ሰጥታው የነበረውም ዕውቅና አንስታለች።

የፑንትላንድ መንግሥት ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዶ ፑንትላንድ የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ተቋማት ላይ የነበራትን መተማመን በማጣቷ ትሰጥ የነበረውን ዕውቅና እንዳነሳች አሳውቋል።

ምክንያቱ ምንድነው ?

የሶማሊያ መንግሥት ፓርላማ ብዙ ባወዛገበ ሂደት በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።

የሕገ መንግሥት ማሻሻያው ፕሬዝዳንቱ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የማሰናበትን ሙሉ ሥልጣን የሚሰጥ ሲሆን ‘ አንድ ሰው አንድ ድምጽ ’ የሚለውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መርህ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያደርግና ሌሎችም ማሻሻያዎች አሉበት።

NB. በሶማሊያ #ውስብስብ የሆነውን እና በጎሳ መሠረት የሚደረገውን ምርጫ ከ50 ዓመታት በላይ ስትጠቀምበት ቆይታለች፡፡ አሁን ' አንድ ሰው አንድ ድምፅ ' የሚለው ማሻሻያ በፑንትላንድ ባለልስጣናት ተቃውሞ ገጥሞታል።

በአጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት ያካሄደው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ በፑንትላንድ አልተወደደም ውድቅም ተደርጓል።

ፑንትላንድ ፤ " በጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት ሕገ መንግስታዊ ሂደት እስከሚፈጠር ድረስ የፑንትላንድ አስተዳደር ለፌዴራል ተቋማት እውቅና አይሰጥም፣ ተቋማቱ ላይም እምነት የለውም " ብላለች።

ሕዝበ ውሳኔ (#ሪፈረንደም) የሚደረግበት ሕገ መንግስት እስከሚወጣ ድረስ፣ ፑንትላንድ የራሷ የሆነ መንግስታዊ ስልጣን እንደሚኖራት አስታውቃለች፡፡

ከአሁን በኋላ ፍላጎቷን ለማስጠቅ ከማዕከላዊ የሶማሊያ መንግሥት እውቅና ውጪ በራሷ አማካይነት #የውጭ_ግንኙነቶችን እንደምታደርግ ገልጻለች።

ይህ የፑንትላንድ ውሳኔ ከሶማሊያ ተነጥሎ ነጻ አገርነትን ከማወጅ ጋር ሊስተካከል እንደሚችል በመጥቀስ #ከሶማሊላንድ ቀጥሎ ለፌደራል መንግሥቱ ሌላ ራስ ምታት እንደሚሆን ተንታኞች እየገለጹ ነው።

ፑንትለንድ በተፈጥሮ ሃብቶችና #በቦሳሶ_ወደቧ በመተማመን እ.አ.አ 1998 ነው ከፊል ራስ ገዝ መሆኗን ያወጀችው። እራሷን እንደ ነጻና ሉኣላዊ ሀገር የምትቆጥረው የሶማሊላንድ ጎረቤትም ናት።

መረጃው ከቪኦኤ እና ቢቢሲ የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia
#ትግራይ

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ?

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች በክልሉ ለሚገኙ ሚድያዎች መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፥ " በፕሪቶሪያ ውል ያልተፈፀሙት እንዲተገበሩ እየሰራን እንቀጥላለን " ብለዋል። 

" የፕሪቶሪያ ውል የፈረምነው የተለያዩ የትግራይ ቦታዎች ከክልሉ አስተዳደር ውጭ በነበሩበት በርካታ ወገኖች ከቄያቸው በተፈናቅሉበት ጊዜ ነበር " ያሉት ጄነራሉ " የውሉ ተዋዋዮች በህገ-መንግስት መሰረት የትግራይ ግዛታዊ አንድነት እንዲረጋገጥ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ተስማምተዋል " ብለዋል። 

" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውልን በጥንቃቄ መተግበር ይገባል " ሲሉ ገልጸዋል።

" አሁን በመታየት ያለው ውጤት የጦርነቱ ውጤት እንጂ የጦርነቱ መነሻ አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግራይ በሃይል የተያዘባት መሬት ሙሉ በሙሉ መልሳ የተማላ ቁመናዋ መያዝ ፤ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ እንዲተገበሩ ያስገድዳል ይህ እንዲሆን ደግሞ በሃይል በተያዙ ቦታዎች ያሉ ታጣቂዎች መውጣትና ህጋዊ ያልሆነው አስተዳደር መፍረስ አለባቸው " ብለዋል።     

" ህጋዊ ያልሆኑ አስተዳደሮች ማፍረስና ታጣቂዎች ትጥቃቻውን ማስፈታት የፕሪቶሪያ ውል የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን ቀጥሎ የሚደረገው ሁሉ #ሰላም ከተረጋገጠ በኋላ የሚሆን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ተፈናቃዮች ሲመለሱ ክብራቸው ተጠብቆ ፣ የሚያስፈልጋቸው መሰረተ ልማት ሁሉ ተሟልቶ ሰብአዊ ድጋፍ ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎች በማድረግ መሆን አለበት "  ያሉት ጀነራሉ  " አስተዳደርን በሚመለከት ቀበሌዎችና ወረዳዎችን የሚያስተዳድሩ ጊዚያዊ  አስተዳደሮች ራሱ ህዝቡ ይመርጣል " ብለዋል።  

ዘላቂ መፍትሄ በሚመለከት ምን አሉ ?

" የፌደራል መንግስት ' አከባቢዎቹ በፌዴራል ስር ቆይተው #ሪፈረንደም ይካሄድ ' የሚል አቋም ያለው ሲሆን በእኛ በኩል ደግሞ በአከባቢው ጊዚያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ትግራይ ይመለሱ የሚል አቋም ነው ያለው፤ ይህ የአቋም ልዩነት እስካሁን አልተፈታም እንዲፈታ ደግሞ ቀጣይ ሰላማዊ ትግል እናደርጋለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

Photo Credit - Tigrai & DW TV
                                          
@tikvahethiopia