#Attention
አዲስ አበባን ከባህር ዳር እና ጎንደር ጋር የሚያገናኘው መንገድ ዛሬም አልተከፈተም፤ መንገድ ላይ ያደሩ ተጓዦች እንደተቸገሩ ናቸው፡፡ መንገዱ ከትናንት ረፋድ ጀምሮ ጎሃ ጽዮን አካባቢ በመዘጋቱ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ማለፍ አልቻሉም፡፡ ከጎንደርና ጎጃም ሁሉም አካባቢዎች በመነሳት ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ላይ የነበሩ ሁሉም የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች እንዳያልፉ በመከልከላቸው ተጓዦቹ ለከፋ እንግልት ተዳርገዋል፡፡ ወደ #ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች፣ ለሕክምና ክትትል የሚሄዱ ታካሚዎች፣ በሃይማኖታዊ ጉዞ የነበሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ ነጋዴዎችና ቤተሰብ ለመጠየቅ የሚጓዙ ሁሉ ናቸው ለእንግልት የተዳረጉት፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-12-2
Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#ዩኒቨርሲቲ
ከሰሞኑን የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች አሉን ካሏቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ " ምላሽ አላገኘንም ፤ መንግስት ትኩረት ሊሰጠንና ጥያቄዎቻችን ሊመልስ " ይገባል በሚል ከህዳር 26 ቀን / 2015 ዓ/ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ የሚጠራ መልዕክት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተሰራጭቶ ነበር።
" የስራ ማቆም አድማው " ን መልዕክት የያዘው ፅሁፍ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨ ፤ በአምስት ገፆች የተዘጋጀና " የኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች የአቋም መግለጫ " ፤ የሚል ሲሆን በዚሁ ላይ አለን ያሉትን ጥያቄዎች ዘርዝረዋል።
ይህ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከተሰራጨ በኃላ እንደ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከበርካታ የቤተሰባችን አባላት ከሆኑ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች መልዕክቶች ድረሰውን ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት ጥረት አድርገናል።
የትምህርት ሚኒስቴርን ጉዳዩን በተመለከተ ጠይቀን ፤ መምህራን የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችን ህጋዊ ከሆነው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ጋር ብቻ በመነጋገር የሚፈታ እንደሆነ አመልክቷል።
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በበኩሉ ፤ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች ስም የተሰራጨውን አቋም " #አላውቀውም " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
ማህበሩ በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲ መምራን ያነሱትን ጥያቄዎች ለትምህርት ሚኒስቴርና ለሚመለክታቸው የፌዴራል መንግስት አካላት እያቀረበ ለመፍትሄው እየሰራ መሆኑን ገልጾ " አንዳንድ ጥያቄዎች በፍጥነት ምላሽ ማግኘት የሚገባቸው መሆኑን " እናምናለን " አንዳንዶቹ ደግሞ ጊዜ የሚፈልጉ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል " ብሏል።
ዛሬ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመልዕክት መለዋወጫ ሳጥን ውስጥ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰሩ መምህራን አድማ አድርገው ወደ ስራ እንዳልገቡ ገልፀዋል።
በአጠቃላይ በምን ያህል ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እና ምን ያህል መምህር በዚህ ላይ ተሳትፏል የሚለውን ለማወቅ ለጊዜው አዳጋች ነው።
ይህን አድማ በግልፅ አስተባብራለሁ የሚል እና ምን ያህሉ መምህር ተሳታፊ እንደሆነ በዝርዝር የሚገልፅ አካል ማግኘት ባለመቻሉ የተሟላ መረጃ ማጋራት ያዳግታል።
ያም ሆኖ ፤ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከሚሰሩ መምህራን ወደ ስራ ያልገቡ ስለመኖራቸው ከራሳቸው እና ከሚያስተምሯቸው ተማሪዎች እንዲሁም ከዚህ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የታሰሩም እንዳሉ ተሰምቷል።
አንዳንድ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ መምህራን እና ተማሪዎች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራ ላይ መዋላቸውን ገልፀዋል።
ከዚህ ፤ ከመምህራን ጥያቄ እና አድማ ጋር በተያያዘ የማህበራዊ ሚዲያ ቅኝት ያደረግን ሲሆን በተለይ መምህራን መንግስት በምን ያህል ችግር ውስጥ እንዳሉ በመገንዘብ ለጥያቄዎች ምላሽ እና ትኩረት እንዲሰጥ ድምፃቸውን ያሰሙ እንዳሉ ሁሉ አንዳንዶች ደግሞ ጥያቄው እና የስራ ማቆም አድማው አሁን ላይ ሰዓቱን እና የጠበቀ አይደለም፤ ሀገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ያገናዘበ አይደለም በማለት የተቃወሙም አሉ።
በቀጣይ ቀናት ያለውን ሁኔታ በመከታተል መምህራንን ጨምሮ የሚመለከታቸውን የዩኒቨርሲቲ አካላት በማነጋገር ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ለናተ ቤተሰቦቻችን እንልካለን።
የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች ጥያቄዎች ምንድናቸው ?
ማስታወሻ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/74911
@tikvahethiopia