TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Gofa

ጎፋ ዞን አስተዳደር በትግራይ ሰብዐዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ገለፀ።

የዞኑ አስተዳደር ፥ በትግራይ ክልል በተፈጠረው ፀጥታ ችግር እና አለመረጋጋት ከቤት ንብረታቸው፣ ከአካባቢያቸው ለተፈናቀሉ እና ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ነው ያሳወቀው።

"ለወገን ደራሽ ወገን ነው" በሚል ለተጎዱት እና ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከ 7 ወረዳዎች እና ከ2 ከተማ አስተዳደሮች እርዳታውን እንዳሰባሰበ ገልጿል።

ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ያሰባሰበውን ጤፍ = 107.4 ኩንታል ፣ ስንዴ 12 ኩንታል ፣ ባቄላ 4 ኩንታል በድምሩ 123.4 ኩንታል እህል በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እንዲደርስ መላኩን አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#GOFA

በጎፋ ዞን ለተከታታይ 4 የምርት ዘመን በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተው የምግብ እጥረት በዛላ ፣ ኡባ ደብረ-ፀሃይ እና ደምባ ጎፋ ወረዳዎች እጅግ በርካታ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ ፈላጊ ሆነዋል።

በተለይም በዛላ ወረዳ በአየር ንብረት መዛባት ምክንያት በምርት ዘመን አስፈላጊው ምርት ባለማግኘቱ ዜጎች ለከፍተኛ ራሃብ ተጋልጠዋል።

በዛላ ወረዳ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ፤ አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ " ለተከታታይ 3 እና ከዛ በላይ ዓመታት በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ የአየር ንብረት መዛባትን ተከትሎ በተከሰተው የዝናብ እጥረት ምርት መድርቁ በምርት ዘመን ምርት ባለማግኘቱ ነዋሪው ለከፍተኛ ራሃብ እና ለከፋ ችግር ተጋልጧል።  " ሲል ገልጿል።

"ይሄ ህዝብ በደጉ ጊዜ የተራበን አጥግቦ ልኳል ፣ ውሃ ሲጠይቁት ወተት አጠጥቷል አሁን ያ ደጉ የዛላ ህዝብ በከፍተኛ ችግር ላይ ነው" ሲል ያለውን ሁኔታ አስረድቷል። "ትኩረት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ላለው ለዛላ ህዝብ" ሲልም ድምፁን አሰምቷል።

በጎፋ ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ እየተሰባሰበ ሲሆን "የጎፋ ዞን የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትና መልሶ ማቋቋሚያ" በሚል በኢ/ን/ባ በ1000511561276 ላይ ገንዘብ እየተሰባሰበ ይገኛል።

ከዚህ በተጨማሪ በአየር ንብረት መዛባት ከፍተኛ ረሃብ በተከሰተበት የዛላ ወረዳ ደረጃ፤ " የዛላ ወረዳ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትና መልሶ ማቋቋሚያ " በሚል በ1000510173612 የባንክ አካውንት የገንዘብ ድጋፍ እየተሰባሰበ ይገኛል።

ከገንዘብ በተጨማሪ ለተቸገሩ ወገኖች የአይነት ድጋፍም እየተደረገ መሆኑን ለማውቅ ችለናል።

ድጋፍ በማስተባበር እና በማሳወቅ በኩል የዞን እና የወረዳ የኮሚኒኬሽን ቢሮዎች በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ተመልክተናል።

@tikvahethiopia
#Gofa

ዛሬ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ፤ በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የወረዳው ዋና አስተዳደር ፥  እሰካሁን በተደረገው ፍለጋ ከ 20 በላይ አስከሬን መገኘቱን አመልክቷል።

የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተገልጿል።

በስፍራው ለነፍስ አድን ተግባር የተሰበሰቡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ  የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን ተሰምቷል።

በአደጋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት እንደሚገኙ ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

መረጃው ከገዜ ጎፋ ወረዳ ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የ3 ቀን ብሔራዊ ሐዘን ዛሬ ጀምሯል።

ዛሬ በጀመረው ብሔራዊ የሐዘን ቀን በጎፋ ዞን፣  ገዜ ጎፋ ወረዳ ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሽራተት አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡና የተጎዱ ወገኖቻችን ይታሰባሉ።

በነዚህ ብሔራዊ የሐዘን ቀናቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በሁሉም የሀገሪቱ ግዛቶች ፤ በሁሉም የኢትዮጵያ መርከቦች ፤ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽ/ቤቶች የሪፐብሊኩ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እየተወለበለበ ይገኛል።

#Ethiopia #GOFA

@tikvahethiopia