TIKVAH-ETHIOPIA
#ኦሮሚያ #ትኩረት በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች አሁንም በቀጠለው የፀጥታ ችግር በርካቶች ህይወታቸው እያለፈ ፣ አካላቸው እየጎደለ፣ ንብረታቸው እየወደመ እንደሚገኝ ቤተሰቦቻችን ጠቁመዋል። ባለፉት ዓመት ህዝቡ በሰላም እጦት ብዙ ቢሰቃይም መፍትሄ ሳይገኝ አሁንም እየተባባሰ በመቀጠሉ ንፁሃን ክፉኛ እየተጎዱ እና ስቃያቸውም እየተባባሰ እንደሚገኝ ነው ቤተሰቦቻችን የገለፁት። ከጥቂት ቀን በፊት…
" የሰው ደም ከፈሰሰ በኃላ የመግለጫ ጋጋታና ሰበር ዜና ለኛ ትካዜ እና ሀዘን እንጂ ጥቅም የለውም " - የቲክቫህ ቤተሰብ አባል
በምስራቅ ወለጋ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሁንም የዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ፤ በርካቶችም ሰላምን ፍለጋ ከቄያቸው እንዲፈናቀሉ እያደረገ ቀጥሏል።
ከጥቂት ቀናት በፊት በአካባቢው ስላለው የፀጥታ ችግር እና እየደረሰ ስላለው ጉዳት ቤተስቦቻቸው በዛው የሚኖሩ የቲክቫህ አባላት በተደጋጋሚ ማሳወቃቸው ይታወሳል።
አሁንም ችግሩ መቀጠሉን የገለፁልን ቤተሰቦቻችን በተለይም በአንገር ጉትን ከፍተኛ ችግር መኖሩን ገልፀው አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግ ድምፃቸውን አሰምተዋል።
አንድ የቤተሰባችን አባል ዛሬ በምስራቅ ወለጋ ፤ በአንገር ጉተን ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ገልፆ የሚመለከተው አካል እንዲደርስ ጥሪ አቅርቧል።
ሌላ አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ " ወለጋ ላይ ባለው ችግር ወገኖቻችን እየረገፉ ነው " ሲል የከዚህ ቀደሙን አስታውሶ ዛሬም በጉትን ከተማ ዙሪያ ላይ ከፍተኛ ችግር መኖሩን አመልክቷል።
ይህንን ጉዳይ የሚመለከተው አካል እንዲያውቅ ድምፁን ያሰማው የቤተሰባችን አባል ፤ " ህዝብ ረግፎ ከማለቁ በፊት ቢያንስ መከላከያ ገብቶ ያረጋጋልን ፤ የሰው ደም ከፈሰሰ በኃላ የመግለጫ ጋጋታና ሰበር ዜና ለኛ ትካዜ እና ሀዘን እንጂ ጥቅም የለውም " ሲል አስገንዝቧል።
በተጨማሪ ሌላው የቤተሰባችን አባል ፤ በአንገር ጉተን ከፍተኛ ችግር መኖሩንና የህዝቡም ደህንነት አደጋ ላይ በመውደቁ ቶሎ መፍትሄ እንዲፈለግ ፤ ሀገር መከላከያም እንዲገባ ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethiopia

#እንድታውቁት በአዲስ አበባ ከ4 ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረዉ የመታወቂያ #እድሳት አገልግሎት በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል። @tikvahethiopia
#መታወቂያ
የአዲስ አበባ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ፤ የተፈቀዱ አዲስ የነዋሪነት ምዝገባ እና የመታወቂያ አገልግሎቶችን አሳውቋል።
በከተማ አስተዳደሩ ተቋርጦ የነበረዉ የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት ከህዳር 1/2015ዓ.ም ጀምሮ የተፈቀደ መሆኑ ያስታወሰው ኤጀንሲው አሁን ደግሞ ፦
👉 በቤተሰብ ማህደር ተመዝግበው 18 ዓመት የሞላቸው ነዋሪዎች፤
👉 ለህክምና ክትትል የሚፈልጉ እና ህጋዊ የህክምና ማስረጃ የሚያቀርቡ ዜጎች፤
👉 በከተማዉ ፍ/ቤት መብት ለማስከበር የሚያበቃቸዉ የመብት ጉዳይ ኖሯቸዉ #የነዋሪነት_መታወቂያ ለሚያስፈልጋቸዉ ነዋሪዎች አሰራርን በመከተል አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች ሲያሟሉ አገልግሎት እንዲያገኙ መፈቀደኑን ገልጿል።
ይህ የተፈቀደው ከትላንት ዓርብ ህዳር 23/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን ተገልጋዮች ሊኖር የሚችለውን ጫና ከግምት በማስገባት በተረጋጋ ሁኔታ ቀርባድ አገልግሎት እንዲያገኙ መልዕክት አስተላልፏል።
በሌላ በኩል ፤ የአዲስ አበባ ከተማ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 24 #ሙሉ_ቀን በሁሉም የወረዳ ፅ/ቤቶች አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለፀ ሲሆን ነገ እሁድ ህዳር 25 አገልግሎት ዝግ መሆኑን አሳውቋል።

ሰው አግተው ከፍተኛ ገንዘብ ሊቀበሉ የነበሩ አጋቾች #ተገደሉ።
እንደ መተማ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት መረጃ ፦
1ኛ. አጋች ጥጌ አበበ አለሙ
2ኛ. አጋች ባበይ አበባው የተባሉ ግለሰቦች አድራሻቸው መተማ ወረዳ መቃ ቀበሌ ሲሆን ሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ በመሄድ " በመተማ ወረዳ ገንዳውሃ ከተማ #ሱቅ ብትሰሩ ቶሎ መቀየር እና ሀብታም ትሆናላችው " በማለት የላሊበላ ከተማ ነዋሪ እና በአነስተኛ ጥቃቅን የሚሰሩ ግለሰቦችን ፦
1ኛ. አፀደ መኮነን
2ኛ. እመቤት መለሰ
የተባሉ ግለሰቦችን ተሰፋ በመስጠት በቀላሉ እንደሚከብሩ በመግለፅና ደውሉልን በማለት ስልክ ሰጠው ይሄዳሉ።
በኃላን እነዚህ ግለሰቦች ይህን ተሰፋ በማድረግ ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ ከተማ በመነሳት ማዕከላዊ ጎንደር ዞን አይከል ከተማ ካደሩ በኃላ በነበራቸው የስልክ ልውውጥ በሁለተኛው ቀን ከአይከል ከተማ በመነሳት ወደ #ገንዳውሃ _ከተማ ይመጣሉ።
1ኛ.አጋች ጥጌ አበበ አለሙ
2ኛ. አጋች ባበይ አበባው የተባሉት ግለሰቦች ህዳር 21ቀን 2015 ዓ.ም መተማ ወረዳ መቃ ቀበሌ ዝንጀሮ በር ከተባለው ልዩ ቦታ ፦
1ኛ አፀደ መኮነን ከ2 ዓመት ልጇ ጋር ፤ 2ኛ እመቤት መለሰ ከ3 ዓመት ልጇ ጋር ከተቀበሏቸው በኃላ ወደ መቃ ቀበሌ ባርኩርኩር ጎጥ ጫካ ውሰጥ በመውሰድ እያንዳንዳችው ታግታችሁዋል ብር ካልከፈላችው አትለቀቁም ይሏቸዋል።
አጋቾቹ በአጠቃላይ " 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) ብር ክፈሉ ካልከፈላችው ህይወታችሁን ታጣላችው " በማለት ለቤተሰቦቻቸው የደወሉ ሲሆን ቤተሰቦችም " እኛ ትንሸ ብር ነው ያለን ይህን መክፈል አንችልም " ሲሉ ይመልሳሉ።
አጋቾቹ፤ " ላሊበላ ከተማ ላይ ብር በልመና ስለሚገኝ የቤተክርሰቲያን ሄዳችሁ ጥላ ይዛችው ለምኑ ያለዚያ ህይወታቸውን ታጣላችው " በማለት በማስለመን 600,000 ብር ከብዙ ክርክር ካደረሱ በኃላ ሊከፍሉ ሲሉ የመተማ ወረዳ ፓሊስ ከማህበረሰቡ ጥቆማ ይደርሰዋል።
የወረዳው ፖሊስም ፤ ከአማራ ክልል ፓሊሰ ልዩ ሃይል " ኮከብ ክፍለጦር " ጋር በመቀናጀት በደረሰው ጥቆማ መሰረት ታጋቾችን ህዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት ላይ መቃ ቀበሌ ባርኩርኩር ላይ የተኩሰ ልውውጥ በማድረግ ታጋቾችን አስለቅቋል።
አጋቾቹ በፀጥታ ሀይሉ የተገደሉ ሲሆን አምስት ቦንብ መያዙ ተገልጿል።
መገጃው ከምዕራብ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ከተገኘ ነው።

" የሰው ደም ከፈሰሰ በኃላ የመግለጫ ጋጋታና ሰበር ዜና ለኛ ትካዜ እና ሀዘን እንጂ ጥቅም የለውም " - የቲክቫህ ቤተሰብ አባል በምስራቅ ወለጋ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሁንም የዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ፤ በርካቶችም ሰላምን ፍለጋ ከቄያቸው እንዲፈናቀሉ እያደረገ ቀጥሏል። ከጥቂት ቀናት በፊት በአካባቢው ስላለው የፀጥታ ችግር እና እየደረሰ ስላለው ጉዳት ቤተስቦቻቸው በዛው የሚኖሩ የቲክቫህ አባላት በተደጋጋሚ…
" እዛ እየሆነ ያለው ድርጊት ይሄ ነው ተብሎ የሚነገር አይደለም። " - ተፈናቃይ
በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ባለው የፀጥታ ሁኔታ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቄያቸው ተፈናቅለዋል ፤ ህይወታቸውን ለማትረፍ ሸሽተዋል።
እንደ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ዘገባ ተፈናቃይ ወገኖች / ህይወታቸውን ለማትረፍ የሸሹ ወገኖች ሰላምን ፍለጋ 40 ኪሎ ሜትር ድረስ በእግር ታጉዘው ጊዳአያና ወረዳ መግባት ችለዋል።
በወረዳው በ19 ቀበሌዎች ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ነቀምቴ እና ጊዳ አያና ወደሚገኙ አካባቢዎች ለመሸሽ ተገደዋል።
ባለፈው ሀሙስ ኪረሙ ላይ ከፍተኛ ውድመት የደረሰ መሆኑ ተመላክቷል።
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ፥ " እዛ እየሆነ ያለው ድርጊት ይሄ ነው ተብሎ የሚነገር አይደለም። " ያሉ ሲሆን ብዙ ህዝብ መፈናቀሉን ፣ ተፈናቃዮች ሰላምን ፍለጋ በሸሹበት ወቅት እየራባቸው ፤ እየደከማቸው በእግር ለመጓዝ መገደዳቸውን ገልፀዋል።
ከተፈናቃዮች መካከል ፤ አንድ አዛውንትም በመንገድ ላይ ደክሟቸው ህይወታቸው እንዳለፈ ያጠቆሙት እኚሁ ነዋሪ " ባለፉት ሳምንታት በነበረው ግጭት ኪረሙ ላይ በአንድ ጉድጓድ ሃያ (20) እና አርባ (40) ሰው ስንቀብር ነበር " ሲሉ የሁኔታውን አስከፊነት ተናግረዋል።
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት እንዳሳወቁት ፤ ከሰሞኑን በነበረው ሁኔታ የሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን እናቶች ልጆቻቸውን ተሸክመው ጫካ ለጫካ እንዲንከራረቱ፣ እንዲሰቃዩ ሆነዋል።
በኦሮሚያ ክልል መንግስት በተለያዩ ዞኖች አካባቢዎች በተለይም ደግሞ በወለጋ ላለፉት ዓመታት የነበረው የፀጥታ ችግር፣ ጥቃት፣ መፈናቀል፣ ሞት ፣ መፍትሄ ሳያገኝ ዛሬም ድረስ የቀጠለ ሲሆን ችግሩ እልባት ከማግኘት ይልቅ ይበልጥ እየተባባሰ እና እየተወሳሰበ መጥቷል።
የአካባቢው ህዝብ ዘርቶ ማጨድ ፣ ሰርቶ መብላት ፣ እንደልቡ ወጥቶ መግባት፣ ልጆቹን በሰላም ያለስጋት ማሳደግ አልቻለም።
- በተደጋጋሚ ጊዜ ፤ የፀጥታ ችግር ያለባቸው ቦታዎች በግልፅ ተለይተው እየታወቁ ችግርም ሲኖር የድረሱልን ጥሪ እየቀረበ በፍጥነት መፍትሄ መስጠት ለምን አልተቻለም ?
ሁሌም ክቡር የሆነው የሰዎች ህይወት ከረገፈ በኃላ የአንድ ሰሞን ትኩረት ተሰጥቶ ፤ ሰሞነኛ ጩኸት ተጩሆ ከዛ ችግሩ ለምን ይቀጥላል ?
- ስንት ሰው ሲያልቅ ነው ዘላቂ መፍትሄ የሚበጀው ? አሁን እየሆነ ላለው እና ለነበረው ነገር ሁሉ ማነው ተጠያቂ ?
- ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ ፤ እንመራዋለን የሚሉትን ህዝብ ሰላሙንና ደህንነቱን ማስጠበቅ ያልቻሉ የመንግስት አካላት መቼ ነው በህግ ፊት ተጠያቂ የሚሆኑት ?
- የተሰቃዩ ፣ የተበደሉ ፣ የሚወዱትን የተነጠቁ እንዴት ነው ፍትህ የሚያገኙ ? የሚሉ ጥያቄዎች መልስ ሊሰጣቸው ይገባል።

አሜሪካ 500 ሺህ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን እየገነባች እንደሆነ ፕሬዜዳንቷ ገልፀዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደራቸው በመላ አገሪቱ 500,000 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን እየገነባ እንደሆነ አሳውቀዋል።
በአሜሪካ የኤሌክትሪክ መኪና ተገልጋዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ሲሆን ሀገሪቱም ይህንን በእጅጉ እያበረታታች ነው።
በአሜሪካ ጎዳናዎች ላይ የሚሽከረከሩ የኤሌክትሪ መኪናዎች ከዓመት ወደ ዓመት እጅግ በጣም ፈጣን የሚባል ባይሆንም እድገት እያሳዩ ይገኛል። የመኪና አምራቾችም ከጊዜ ወደ ጊዜ በተያየ ሞዴል እያመረቱት ያለውን የኤሌክትሪክ መኪና እየጨመሩ ይገኛሉ።
አሜሪካ በ2050 ከካርቦን-ነፃ እንድትሆን አሽከርካሪዎች በነዳጅ ኃይል ከሚሰሩ ወደ ኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች እንዲቀይሩ ማድረግ ወሳኝ እንደሆነ ታምናለች።
የአሁኑ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በ2030 ከአዳዲስ የመኪና ሽያጭ ግማሹ የኤሌክትሪክ ፣ ወይም ሃይብሪድ ተሽከርካሪዎች እንዲሆኑ ትልቅ ግብ የወጠኑ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2030 ግማሹ ኤሌክትሪክ ከሆኑ፣ በ2050 በአሜሪካ ጎዳናዎች ከሚሽከረከሩት መኪኖች ከ60-70 በመቶ የኤሌክትሪክ / ሃይብሪድ ተሽከርካሪዎች ሊሸፍኑ ይችላሉ።

Photo
#Update
2 ህፃናት በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው የቤት ሰራተኛ #በሞት እንድትቀጣ ተወሰነ።
2 ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች ተብላ የተከሰሰችው የጥፋተኝነት ፍርድ የተሰጠባት ህይወት መኮንን የተባለችው የቤት ሰራተኛ በሞት ቅጣት እንድትቀጣ ተወስኗል።
የቅጣት ውሳኔውን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የከባድ ግድያና የውንብድና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ተከሳሽ ህይወት መኮንን ሀይሉ በነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠኋቱ 3:30 ላይ በለሚኩራ ክ/ከ አራብሳ ኮንዶሚኒዬም በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ በምትሰራበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የህጻን ግዮናዊት መላኩ አፏን በማፈን በቢላ በማረድ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጓን እና ህጻን ክርስቲና መላኩን አፏን በማፈን በማነቅ በአጠቃላይ ህፃናቶቹን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች ሲል በግድያ ወንጀል እና በወቅቱ የሟች ቤተሰቦችን የሰነድ ማስረጃዎች ቀዳዳ በማጥፋት በአጠቃላይ በተደራራቢ ክስ በጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ/ም የወንጀል ክስ ተመስርቶባት እንደነበር ይታወሳል።
https://telegra.ph/Tarik-Adugna-12-05
(ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ)

#ፍትሕ_ሚኒስቴር
የሁለት ህፃናትን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ያጠፋችው ህይወት መኮንን በዛሬው ችሎት ዐቃቤ ህግ በሞት እንድትቀጣ ካለ በኃላ ፦
- ከዚህ ቀደም ወንጀል ፈፅሜ የማላውቅ፣
- ወንጀሉን የፈጸምኩት ከእውቀት ማነስና ያልተማርኩ በመሆኔ መሆኑ፣
- እጄን ለፖሊስ አምኜ የሰጠው በመሆኔ ከግምት ገብቶ ቅጣቱ ይቅለልልኝ በማለት የቅጣት ማቅለያዎችን ከመንግስት በተመደበላት የተከላካይ ጠበቃ አማካኝነት የጠየቀች ቢሆንም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ተከሳሿ ያቀረበችውን ማቅለያዋን #አልተቀበለውም፡፡
ፍርድ ቤቱ ሌሎች አጥፊዎችን ያስጠነቅቃል በማለት ተከሳሿ #በሞት እንድትቀጣ ሲል ወስኖባታል፡፡

#ዩኒቨርሲቲ
ከሰሞኑን የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች አሉን ካሏቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ " ምላሽ አላገኘንም ፤ መንግስት ትኩረት ሊሰጠንና ጥያቄዎቻችን ሊመልስ " ይገባል በሚል ከህዳር 26 ቀን / 2015 ዓ/ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ የሚጠራ መልዕክት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተሰራጭቶ ነበር።
" የስራ ማቆም አድማው " ን መልዕክት የያዘው ፅሁፍ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨ ፤ በአምስት ገፆች የተዘጋጀና " የኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች የአቋም መግለጫ " ፤ የሚል ሲሆን በዚሁ ላይ አለን ያሉትን ጥያቄዎች ዘርዝረዋል።
ይህ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከተሰራጨ በኃላ እንደ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከበርካታ የቤተሰባችን አባላት ከሆኑ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች መልዕክቶች ድረሰውን ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት ጥረት አድርገናል።
የትምህርት ሚኒስቴርን ጉዳዩን በተመለከተ ጠይቀን ፤ መምህራን የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችን ህጋዊ ከሆነው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ጋር ብቻ በመነጋገር የሚፈታ እንደሆነ አመልክቷል።
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በበኩሉ ፤ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች ስም የተሰራጨውን አቋም " #አላውቀውም " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
ማህበሩ በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲ መምራን ያነሱትን ጥያቄዎች ለትምህርት ሚኒስቴርና ለሚመለክታቸው የፌዴራል መንግስት አካላት እያቀረበ ለመፍትሄው እየሰራ መሆኑን ገልጾ " አንዳንድ ጥያቄዎች በፍጥነት ምላሽ ማግኘት የሚገባቸው መሆኑን " እናምናለን " አንዳንዶቹ ደግሞ ጊዜ የሚፈልጉ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል " ብሏል።
ዛሬ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመልዕክት መለዋወጫ ሳጥን ውስጥ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰሩ መምህራን አድማ አድርገው ወደ ስራ እንዳልገቡ ገልፀዋል።
በአጠቃላይ በምን ያህል ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እና ምን ያህል መምህር በዚህ ላይ ተሳትፏል የሚለውን ለማወቅ ለጊዜው አዳጋች ነው።
ይህን አድማ በግልፅ አስተባብራለሁ የሚል እና ምን ያህሉ መምህር ተሳታፊ እንደሆነ በዝርዝር የሚገልፅ አካል ማግኘት ባለመቻሉ የተሟላ መረጃ ማጋራት ያዳግታል።
ያም ሆኖ ፤ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከሚሰሩ መምህራን ወደ ስራ ያልገቡ ስለመኖራቸው ከራሳቸው እና ከሚያስተምሯቸው ተማሪዎች እንዲሁም ከዚህ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የታሰሩም እንዳሉ ተሰምቷል።
አንዳንድ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ መምህራን እና ተማሪዎች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራ ላይ መዋላቸውን ገልፀዋል።
ከዚህ ፤ ከመምህራን ጥያቄ እና አድማ ጋር በተያያዘ የማህበራዊ ሚዲያ ቅኝት ያደረግን ሲሆን በተለይ መምህራን መንግስት በምን ያህል ችግር ውስጥ እንዳሉ በመገንዘብ ለጥያቄዎች ምላሽ እና ትኩረት እንዲሰጥ ድምፃቸውን ያሰሙ እንዳሉ ሁሉ አንዳንዶች ደግሞ ጥያቄው እና የስራ ማቆም አድማው አሁን ላይ ሰዓቱን እና የጠበቀ አይደለም፤ ሀገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ያገናዘበ አይደለም በማለት የተቃወሙም አሉ።
በቀጣይ ቀናት ያለውን ሁኔታ በመከታተል መምህራንን ጨምሮ የሚመለከታቸውን የዩኒቨርሲቲ አካላት በማነጋገር ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ለናተ ቤተሰቦቻችን እንልካለን።
የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች ጥያቄዎች ምንድናቸው ?
ማስታወሻ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/74911

#Mekelle ትላንት 13 የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ኮንቮይናና 3 የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የጭነት ተሽከርካሪዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ጭነው ትግራይ ክልል መቐለ ገብተዋል። ተሽከርካሪዎቹ የዳይለሲስ እቃ እንዲሁም በኢትዮጵያ ስኳር ህሙማን ማህበር የተበረከተ ኢንሱሊንን ጨምሮ አጠቃላይ 200 ቶን የሚጠጋ ሰብዓዊ ድጋፍ ፣ምግብ እና መድሃኒት የጫኑ እንደሆኑ ከICRC ያገኘነው መረጃ ያሳያል።…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Tigray
የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ፤ ቡድኖቹ #ትግራይ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታሎች እና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያዎች ለታካሚዎች እና ጤና ባለሙያዎች ተጨማሪ የህክምና ቁሳቁሶችን እና የምግብ አቅርቦትን እያከፋፈሉ መሆኑን አሳውቋል።
ትላንትም 16 የጭነት ተሽከርካሪዎች ድጋፍ ይዘው ሽረ መግባቸውን አመልክቷል።
በገጠር አካባቢዎች ስርጭቱ መቀጠሉንም ገልጿል።

#GOFA
በጎፋ ዞን ለተከታታይ 4 የምርት ዘመን በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተው የምግብ እጥረት በዛላ ፣ ኡባ ደብረ-ፀሃይ እና ደምባ ጎፋ ወረዳዎች እጅግ በርካታ ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ ፈላጊ ሆነዋል።
በተለይም በዛላ ወረዳ በአየር ንብረት መዛባት ምክንያት በምርት ዘመን አስፈላጊው ምርት ባለማግኘቱ ዜጎች ለከፍተኛ ራሃብ ተጋልጠዋል።
በዛላ ወረዳ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ፤ አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ " ለተከታታይ 3 እና ከዛ በላይ ዓመታት በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ የአየር ንብረት መዛባትን ተከትሎ በተከሰተው የዝናብ እጥረት ምርት መድርቁ በምርት ዘመን ምርት ባለማግኘቱ ነዋሪው ለከፍተኛ ራሃብ እና ለከፋ ችግር ተጋልጧል። " ሲል ገልጿል።
"ይሄ ህዝብ በደጉ ጊዜ የተራበን አጥግቦ ልኳል ፣ ውሃ ሲጠይቁት ወተት አጠጥቷል አሁን ያ ደጉ የዛላ ህዝብ በከፍተኛ ችግር ላይ ነው" ሲል ያለውን ሁኔታ አስረድቷል። "ትኩረት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ላለው ለዛላ ህዝብ" ሲልም ድምፁን አሰምቷል።
በጎፋ ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ እየተሰባሰበ ሲሆን "የጎፋ ዞን የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትና መልሶ ማቋቋሚያ" በሚል በኢ/ን/ባ በ1000511561276 ላይ ገንዘብ እየተሰባሰበ ይገኛል።
ከዚህ በተጨማሪ በአየር ንብረት መዛባት ከፍተኛ ረሃብ በተከሰተበት የዛላ ወረዳ ደረጃ፤ " የዛላ ወረዳ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትና መልሶ ማቋቋሚያ " በሚል በ1000510173612 የባንክ አካውንት የገንዘብ ድጋፍ እየተሰባሰበ ይገኛል።
ከገንዘብ በተጨማሪ ለተቸገሩ ወገኖች የአይነት ድጋፍም እየተደረገ መሆኑን ለማውቅ ችለናል።
ድጋፍ በማስተባበር እና በማሳወቅ በኩል የዞን እና የወረዳ የኮሚኒኬሽን ቢሮዎች በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ተመልክተናል።

" መንግስት በማንኛውም ሁኔታ የዜጎችን ሁለንተናዊ ደህንነት የመጠበቅ ሃለፊነቱን በአግባቡ ይወጣ " - የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት
የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በምዕራብ ኦሮሚያ ምሥራቅ ወለጋ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ሞት፣ መፈናቀል እና ሰቆቃ በእጅጉ እንደሚያሳስበው ገልጾ መንግስት የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ጥሪውን ያቀርቧል።
ምክር ቤቱ በላከል መግለጫ ፤ ሰሞኑን በምዕራብ ኦሮሚያ ምሥራቅ ወለጋ በቀጠለው ግጭት በዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱን ከአካባቢው በሚወጡ መረጃዎች መረዳቱን ገልጿል።
በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ሞት፣ መፈናቀል እና ሰቆቃ በእጅጉ ያሳሰበው መሆኑን የገለፀው ምክር ቤቱ ፤
1ኛ) መንግስት በማንኛውም ሁኔታ የዜጎችን ሁለንተናዊ ደህንነት የመጠበቅ ሃለፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ፤
2ኛ) ብዥታን ለማስወገድ እና የተሳሳቱ መረጃዎችን ለማጥራት፤ በጉዳዩ ላይ ወቅታዊ፤ተጨባጭ እና ትክክለኛ መረጃ ለህዝብ እንዲደርስ እንዲያደርግ፤
3ኛ) በአካባቢው ያለው ሁኔታ ተጣርቶ፤ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ፤
4ኛ) አፋጣኝ ሰብዓዊ እርዳታና ድጋፍ ለተጎጂዎች እንዲቀርብ ፤ እንዲሁም ፤ ለጉዳዩ ፤ ዘላቂ እና ሁለንተናዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርቧል።
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ብሎም በየትኛውም የሀገሪቱ ማእዝናት የሚኖሩ ዜጎች ሁለንተናዊ ደህንነታቸው እንዲረጋገጥ የጀመረውን የሰላም ግንባታ ስራዎች አጠናክሮ ለመቀጠል ያለውን ቁርጠኝነትና ዝግጁነት አረጋግጧል።

#ነዳጅ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሕዳር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል። ሚኒስቴሩ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የነዳጅ ዋጋ #በጥቅምት_ወር በነበረው እንደሚቀጥል ገልጿል። የነዳጅ ዋጋው ከጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሕዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሚዘልቅ ነው። በሁለተኛው ምዕራፍ ከመስከረም 18 ቀን 2015…
#ነዳጅ
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር 2015 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን ዛሬ አስታውቋል።
ከዛሬ ኅዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር 2015 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ ይቀጥላል ብሏል።
ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

በርካታ ወላጆችን ያስጨነቀው የ " ፍራንስ ሌይ " የህፃናት ወተት ጉዳይ ምንድነው ?
ፍራንስ ሌይ ላብራቶሪ የፈረንሳይ ኩባንያ ሲሆን " ፍራንስ ሌይ " የተባለ የህፃናት ወተቶች አምራች ነው።
ይህንን ወተት ወደ " #ኢትዮጵያ " እያስመጣሁ አሰራጫለሁ ያለው " ዶክ ቶክ " የተባለ አስመጪና ላኪ ከሰሞኑን ከህፃናት ወተቱ ጋር በተያያዘ በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጨ ሀሰተኛ መረጃ ወላጆች እየተረበሹ መሆኑንና ስራውንም ላይ እክል እንደገጠመው ገልጿል።
የህፃናት ወተቶቹ አለም አቀፍ ደረጃቸዉን የጠበቁ በአውሮፓ ስታንዳርድ የተመረቱ የ CODEX SASO, FDA መስፈርቶችን ያሟሉ ናቸው ያለው ይኸው አስመጪ ድርጅት እነዚህ ምርቶች በአምራች ኩባንያዉ የአሰራር ሂደት መሰረት ለምርቶቹ መለያ ይሆን ዘንድ የማይቀየርና ወጥ የሆነ መለያ ቁጥር (Bar Code) የሚጠቀሙ ናቸው ብሏል።
ይህ ባር ኮድ የምርቱን ትክክለኛነትና የምርቱን አይነት (type of product and type of Sku) ለመግለፅ ይጠቅማል ፤ እንዲሁም እነዚህ የዱቄት ጣሳዎች እንደማንኛዉም ምርቶች የባች ቁጥር (Batch Number) ያላቸዉ ናቸው ይህም የምርቱን ሁኔታ ለመከታተል (Product traceability, production date and time, expire date) ይረዳል ሲል አስረድቷል።
በዚህም ባር ኮድና የምርቱ መጠቀሚያ ጊዜ መካከል ምንም አይነት ግንኙነት የለም ሁለቱም የተለያዩ መረጃዎችን ጥቅሞችን ይይዛሉ፤ አንድ ባር ኮድ የተለያዩ የባች ቁጥር እና የመጠቀሚያ ጊዜን ይይዛል ብሏል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/France-Lait-12-07