#Save_the_Children
Save the Children የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የተኩስ አቁም ውሳኔ ካሳለፈ በኃላ ለክልሉ የሚደረገውን ድጋፍ በጸጥታ ስጋት ምክንያት በጊዜያዊነት እንዳቆመ አስታወቀ።
ይህን ያሳወቁት በኢትዮጲያ የ Save the Childern ቃል አቀባይ የሆኑት ወ/ሮ ህይወት እምሻዉ ለአሀዱ 94.3 ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ነው።
ወ/ሮ ህይወት ከተናጠል ተኩስ አቁሙ አስቀድሞ ከጊዚያዉ መስተዳደሩ ጋር በመነጋገር የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ እንደቆዩ እና የተናጠል የተኩስ አቁም ዉሳኔዉ በመንግስት በኩል ከተላለፈ በኃላ በጊዚያዊነት ለክልሉ የሚላኩ ድጋፎች መቋረጣቸዉን ገልጸዋል፡፡
ለመቋረጡ ዋነኛ ምክንያቶች ብለዉ የጠቀሱት ፦
- የድርጅቱ ሰራተኞች ደህንነት ፤
- የመገናኛ ዘዴዎች መቋረጥ፤
- ወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ አስተማማኝ ነገር ስለሌለዉ እና ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ አመቺ ሁኔታ እስኪፈጠር በሚል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ሆኖም አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች ያለዉን የመገናኛ ዘዴ እና መንግስት ያመቻቸዉን ሁኔታ ተጠቅመዉ እርዳታዎችን እያቀረቡ በመሆኑ ድርጅታቸዉ ተቋርጦ የቆየዉን የሰብዓዊ ድጋፍ በድጋሚ ለመጀመር ከሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ጋር እየተወያዩ መሆኑን ለሬድዮ ጣቢያው (አሀዱ 94.3) ገልፀዋል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Save_the_Children Save the Children የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የተኩስ አቁም ውሳኔ ካሳለፈ በኃላ ለክልሉ የሚደረገውን ድጋፍ በጸጥታ ስጋት ምክንያት በጊዜያዊነት እንዳቆመ አስታወቀ። ይህን ያሳወቁት በኢትዮጲያ የ Save the Childern ቃል አቀባይ የሆኑት ወ/ሮ ህይወት እምሻዉ ለአሀዱ 94.3 ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ነው። ወ/ሮ ህይወት ከተናጠል ተኩስ አቁሙ አስቀድሞ…
#Save_the_Children
"ከቀድሞ ጋር ሲነፃፀር በመጠን ቢያንስም አሁንም ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረግን ነው" - ወ/ሮ ህይወት እምሻው
የሕፃናት አድን ድርጅት አሁንም በትግራይ ክልል ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
በኢትዮጵያ የ Save the Children ቃል አቀባይ ወይዘሮ ህይወት እምሻው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት " አሁናዊ መረጃ እና ማረሚያ " ድርጅቱ በትግራይ ከቀድሞው ጋር ሲነፃፀር በመጠን ቢያንስም፣ አሁንም ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
ድጋፎቹ በትምህርት ፣ በጤና ፣ በውሃ አቅርቦት እንዲሁም የምግብ እርዳታ ላይ ያተኮሩ እንደሆኑም ገልፀዋል።
Save the Childern በመቐለ፣ በአክሱም እና በዓዲግራት ውስን ሰራተኞችን በመጠቀም ስራውን እያከናወነ ይገኛል።

በኦሮሚያ፣ ደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች የህፃናት አድን ድርጅት (Save the Children) በ136 ትምህርት ቤቶች ላይ የምገባ ፕሮግራም እየሰጠ መሆኑን ለኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን አሳውቋል።
ለ90 ሺህ ተማሪዎች በ136 ትምህርት ቤቶች ላይ በኦሮሚያ ፣ ደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች በ4 ወረዳዎች GPE ከተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት በተገኘ ድጋፍ የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን የኢትየጵያ ደቡባዊ አካባቢ ማናጀር የሆኑት ዶክተር ሀይሉ ተስፋዬ ገልፀዋል።
በዚህ የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ማድረጉንና በተማሪዎች ትምህርት ውጤት እና የትምህርት ጥራት ላይ ከፍተኛ መሻሻል እንዲመጣ ማድርጉን ማናጀሩ ጨምረው ገልፀዋል።
ዶክተር ሀይሉ ተስፋዬ በቀጣይ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር Save the Children ዋነኛ አላማ ያደረገው የህፃናትን ትምህርትንና የምገባ ፕሮግራም የሚደረስና ጥራቱን የመጠበቅ ተግባር እንቀጥላለን ብለዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ስራው እንዲሳካ ለሚያደርገው ደግፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን

#Save_the_Children #Tigray
የህጻናት አድን ድርጅት ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ መድረሱን ድርጅቱን አሳውቆናል።
የህጻናት አድን ድርጅት በላከልን መልዕክት ፤ የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ ወዲህ የመጀመሪያ ዙር የሰብዓዊ እርዳታን #በአምስት ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ማጓጓዙን ገልጾልናል።
" ህጻናት በዚህ ግጭት ክፉኛ ተጎድተዋል፤ አፋጣኝ እርዳታም ሊያገኙ ይገባል፡፡ " ያሉት፣ በኢትዮጵያ የድርጅቱ ኃላፊ ዣቬር ዡቤር፣ ተጨማሪ ምግብና ሌሎች የእርዳታ ቁሳቁስ የጫኑ ተጨማሪ ዘጠኝ ተሽከርካሪዎች በመንገድ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የህጻናት አድን ድርጅት በሰሜኑ ኢትዮጵያ ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ በአፋርና አማራ ክልሎች ለችግር ለተጋለጡ ህጻናትና ቤተሰቦቻቸውም ተመሳሳይና ያልተቋረጠ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጾልናል።