TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች!

በአቃቂ መሿለኪያ ድልድይ የሚያልፍበት ወንዝ ሙላት ምክንያት የሚፈጠሩ እንግልቶችን ለማስቀረት ህብረተሰቡ የተለያዩ የመንገድ #አማራጮችን እንዲጠቀም የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ያሳስባል፡፡

አማራጮችን ለመጠቆም ያህል፡-

1. ወደ ምስራቅ አዲስ አበባ መሄድ የሚፈልጉ ተሽከርካሪዎች ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ አደባባይ ወደ ቱሉ ዲምቱ ማሳለጫ (ወደ ጎሮ የሚወስደውን ውጫዊ የቀለበት መንገድ) መጠቀም ይችላሉ።

2. ወደ መሃል አዲስ አበባ ለመሄድ የሚፈልጉ ተሸከርካሪዎች ዋናውን አቃቂ ድልድይ መጠቀም ይችላሉ።

3. ወደ ምዕራብ አዲስ አበባ መሄድ የሚፈልጉ ተሸከርካሪዎች ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ አደባባይ በግራ በኩል ወደ ለቡ የሚወስደውን ውጫዊ የቀለበት መንገድ መጠቀም ይችላሉ።

4. ከአዲስ አበባ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ የሚጓዙ ተሸከርካሪዎች በላይ አብ ሞተርስ አለፍ ብሎ ወደ ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚኒየም በመታጠፍ መስቀለኛ መንገዱን መጠቀም ይቻላሉ።

እንደሚታወቀው ቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ - ቱሉ ዲምቱ አደባባይ መንገድ ለረጅም ጊዜ የከተማው የምስራቅ መውጫ በር በመሆን በማገልገሉ ምክንያት በመጎዳቱ እና የሚያስተናግደውም የትራፊክ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ በማደጉ ወቅቱ የሚጠይቀውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል ማስተር ፕላኑን ጠብቆ እንደ አዲስ በመገንባት ደረጃውን የማሻሻል ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በክረምት ወራት በሚጥለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በመንገዶች ላይ በሚፈጥረው #የጎርፍ ችግር ምክንያት በነዋሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ለሚፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ እየጠየቀ አሽከርካሪዎች ከምን ጊዜውም በላይ ሲያሽከረክሩ ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ እና ሌሎች የመንገድ አማራጮች በመጠቀም ከጎርፍ ስጋትና ከእንግልት እንዲድኑ ይመክራል፡፡

©የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን
@tsegbwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

" የድርቅና ጎርፍ አደጋዎች በቀጣዮቹ ሳምንታትም #ተባብሠው ሊቀጥሉ ይችላሉ " - የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከሠቱ ያሉት የድርቅና የጎርፍ አደጋዎች በቀጣዮቹ ሳምንታትም #ተባብሠው_ሊቀጥሉ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

የኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳሬክተር አቶ ክንፈ ኃ/ማሪያም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ62ኛ በኢትዮጵያ ለ42ኛ ጊዜ በሚከበረው የሚቲዎሮሎጂ ቀን ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው ይህ የተሰማው።

አቶ ክንፈ " በተቋሙ የተሠሩ ጥናቶች የሚያሳዩት #የድርቅ እና #የጎርፍ አደጋዎች በሀገሪቱ በቀጣይም በይበልጥ ተጠናክረው ይከሰታሉ " ብለዋል።

" የሚደርሰውን አደጋ ለመቋቋም የተጠናከረ የአየር ሁኔታ መከታተል ፣ መተንበይ እና ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን መገንባትና ማዘመንን ይገባል " ያሉት ምክትል ዳይሬክተሩ " እየተከሰተ ያለውን የአየር ንብረት መዛባት ቀድሞ ለመተንበይ የሚያስችል ብሔራዊ የአየር ጠባይ አገልግሎት ማዕቀፍ በሀገሪቱ ተዘርግቷል ፤ ይህ ተጠናክሮ ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲገባ የባለድርሻ አካላት ርብርብ ያስፈልገዋል " ብለዋል።

አቶ ክንፈ ፤ በሀገሪቱ ለማኅበራዊ እና ለኢኮኖሚ መሠረት የሆኑ የግብርና፣ የውሀ፣ የኢነርጂና የአደጋ ሥጋት ቅነሳ መርሐ ግብሮች በአየር ንብረት መዛባት ተፅዕኖ ስር መሆናቸውን ገልፀው በእነሱ ላይ የሚደርሠውን የአየር ንብረት መዛባት አደጋ ለመቀነስ ተቋሙ ጥናትና ክትትል የማድረግ ሥራ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

" በአየር ንብረት መዛባት የሚመጡ አደጋዎችን ማለትም ጎርፍ፣ ድርቅና የመሳሰሉትን ለመቀነስ ተቋሙ ክትትልና ጥናት በማድረግ ኅብረተሰቡን ከአደጋ ለመከላከል እየሠራ ነው " ሲሉ የገለፁት አቶ ክንፈ ፥ በአየር ንብረት መዛባት የሚደርሰውን የተለያየ አደጋ በዘላቂነት ለመቋቋም ተቋሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሠራ መሆኑን ባለድርሻ አካላትም በአጋርነት እየሰሩ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።

#ኢፕድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ከተጎጂዎች መካከል 30,427 ህፃናት ናቸው። የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ደርሷል ” - ሴቭ ዘ ቺልድረን በሶማሌ ክልል ከተከሰተ የወራት ያለፈው የጎርፍ አደጋ የውሃ መጠኑ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም ትንበያዎች የሚያመለክቱት በመጪው የዝናብ ወቅት ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንዲሚችል ስለሆነ፣ ህብረተሰቡም አሁንም ካለፈው የጎርፍ አደጋ ገና እያገገመ በመሆኑ፣ ትልቅ ፈተናና ስጋት መፍጠሩን በቦታው የሚገኘው…
#SavetheChildren

“ በሚያሳዝን ሁኔታ 70 ሰዎች በኮሌራ ሕይወታቸውን አጥተዋል። 9 ሰዎች በኩፍኝ ሞተዋል ” - የህጻናት አድን ድርጅት

በሶማሌ ክልል በተለይም #የጎርፍ_አደጋ በደረሰባቸው ወረዳዎች በተፈናቀሉ ወገኖች የተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሆነ የክልሉ የህጻናት አድን ድርጅት (Save the children) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የድርጅቱ ምሥራቅ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ አህመድ ፣ የኮሌራ ወረርሽኙ እንደቀጠለ መሆኑን በሴፕተምበር 2023 ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ በድምሩ 7, 480 ሰዎች እንደተጎዱ ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ በሰጡት ቃል፣ “ በሚያሳዝን ሁኔታ 70 ሰዎች በኮሌራ ሕይወታቸውን አጥተዋል። 9 ሰዎች ደግሞ በኩፍኝ ሞተዋል ” ብለዋል።

በተጨማሪም ከ2024 መጀመሪያ ጀምሮ 533 ሰዎች በኩፍኝ በሽታ እንደተያዙ፣ 9ኙ ሰዎች ለሞት የተዳረጉት በጎዴ ከተማ፣ ጎዴ ወረዳ፣ በራኖ አካባቢዎች መሆኑን አስረድተዋል።

ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ምንድናቸው ?

📣 በጎርፍ ለተጎዳ ማህበረሰብ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረግ ምላሽ፣ የአደጋ ጊዜ መጠለያ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ ለማደረግ አቅርቦቶችን ማጎልበት። የኮሌራ ክትባቶች ከፍተኛ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች መስጠት ይገባል።

📣 የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ መሠረታዊ እና አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ወሳኝ በሆኑ የጤና ተቋማት ላይ ጉዳት እንዳደረሰ በመገንዘብ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የጤና መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ መዋዕለ ነዋይ ሊፈስ ይገባል።

📣 #ህፃናት በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሆናቸው ልዩ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል። 

#ጥሪ

(አቶ አብዲራዛቅ አህመድ)

" ለለጋሽ ማህበረሰቡ አንድ ጥሪ ማቅረብ እፈልጋለሁ። ወረርሽኝ እና ተደጋጋሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ የሚያመጣውን ከፍተኛ ጉዳትና ተጽዕኖ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመቀነስ የገንዘብ ድጋፍ ያስፈልጋል። "

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia