#ንግድፍቃድ #እድሳት
የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ የንግድ ስራ ፈቃድ የሚያድሱ ተገልጋዮች ከሰኞ እስከ እሁድ ባሉት የስራ ሰዓት አገልግሎቱን በኦንላይን ማግኘት እንደሚችሉ ገልጿል።
በክልሎች ሲሠጡ የነበሩ የአስመጪነት እና የላኪነት የንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አገልግሎቶች እንደ ቀድሞው ወደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መመለሳቸውንም አሳውቋል።
በሚኒስቴሩ የሚሠጡ የንግድ ስራ መደቦች ላይ በበጀት ዓመቱ ከሐምሌ1/2015 ዓ.ም እስከ ታኅሣሥ 30/ 2016 ዓ.ም ድረስ የንግድ ስራ ፈቃድ ለሚያድሱ ተገልጋዮች፤ ከሰኞ እስከ እሁድ በመንግስት የስራ ሰዓት የፈቃድ ዕድሳት አገልግሎቶችን በኦንላይን ማግኘት ይቻላል ተብሏል።
ወቅቱ የዕድሳት አገልግሎት የሚሰጥበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፤ በመጨረሻ ቀናት የሚከሰቱ የሲስተም ወረፋዎችን ለመከላከል እንዲቻል፤ ተገልጋዮች የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች በሟሟላት የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን በቀሩት ቀናት አስቀድመው በኦንላይን እንዲያድሱ በሚኒስቴሩ ጥሪ ቀርቧል።
የንግድ ፍቃድ ማደሻ አድራሻ (ድረገፅ) www.etrade.gov.et. ነው።
ምንም እንኳን ሚኒስቴሩ ንግድ ፍቃዳችሁን በኦንላይን ከሰኞ እስከ እሁድ በስራ ሰዓት ማደስ ትችላላችሁ ቢልም የንግድ ፍቃድ ማደሻው ድረገፅ እንደ ከዚህ ቀደሙ በአግባቡና በፍጥነት አገልግሎት እየሰጣቸው እንዳልሆነ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። ይህ ችግር እንዲስተካከልም ጥሪ አቅርበዋል።
@tikvahethiopia