TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው 31 ቁጥር ማዞሪያ አካባቢ ዛሬ ጠዋት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ  ስድስቱ ደግሞ  የአካል ጉዳት ደረሰባቸው።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢዜአ እንደገለፀው አደጋው የደረሰው ተሳፋሪ ጭኖ ከቁስቋም ወደሽሮሜዳ ሲጓዝ የነበረ ሰሌዳ ቁጥሩ 10633 ኮድ አንድ የሆነ ሚኒባስ ታክሲ አቅጣጫውን ስቶ ከኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ምሶሶ ጋር በመጋጨቱ ነው።

በአደጋው ሁለት ተሳፋሪዎች #ሞተዋል፤ ጉዳት ከደረሰባቸው ስድስት ሰዎች መካከልም ሁለቱ በከባድ መጎዳታቸውም  ተመልክቷል። 

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው። 

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሆነም የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ተናግረዋል።

በአደጋው የሞቱት ሴቶች ሲሆኑ የተጎዱት ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን ነው ኢንስፔክተር ማርቆስ የጠቀሱት። 

በአደጋው መስተዋቱን ጨምሮ #የተሽከርካሪው አካል መጎዳቱን በቦታው የተገኘው የኢዜአ ሪፖርተር ተመልክቷል።

የዓይን እማኞች እንደገለፁት አደጋው በተሽከርካሪው ፍሬን ችግር የተከሰተ ነው።

በታክሲው ተሳፍረው ሲጓዙ የነበሩት አቶ አንዷለም ለማ እንዳሉት በጠዋት ወደ ቢሮ ለመሄድ በጉዞ ላይ እያሉ አንዲት ተሳፋሪ መውረጃዋ ደርሶ “ወራጅ” ብትልም ታክሲው ሊቆም አልቻለም።

“ከዚያም ከደቂቃዎች ልዩነት በኋላ የታክሲው ረዳት ሰዎችን ከመንገዱ ዞር እንዲሉ ማስጠንቀቅ ጀመረ፤ ሹፌሩም የመኪናውን መሪ ይዞ ሲታገል ነበር “ያሉት አቶ አንዷለም ከዛ በኃላ መኪናው ተጋጭቶ ሲቆምና ከመኪናው ውጪም የተጎዳ ሰው ማየታቸውን ያስታውሳሉ።

ተሳፋሪው ከተረጋጋ በኃላ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን እንደሰሙም አክለዋል።

አሽከርካሪዎች ሲጓዙ የቴክኒክ ፍተሻ በማድረግ ራሳቸውንና ኀብረተሰቡን ከአደጋ መጠበቅ እንዳለባቸውም አቶ አንዷለም መልዕክት አስተላልፈዋል። 

ምንጭ፦ ኢዜአ
ፎቶ፦NTU(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia