TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#CIA #USA #CHINA

የኮሮና ቫይረስ መነሻው ምንድነው ? መደምደሚያ ያላገኘው ጥያቄ አሁንም መነጋገሪያነቱ እንደቀጠለ ነው።

የአሜሪካ ብሔራዊ የስለላ ቢሮ ዳይሬክተር ጽ/ቤት የኮሮና ቫይረስ "ከቻይና ቤተ ሙከራ ያፈተለከ ነው ወይስ በተፈጥሮ የተከሰተ ነው" በሚለው ላይ ለ2 ተከፍሏል።

ነገር ግን ይህ የአገሪቱን 18 የስለላ ኤጀንሲዎች የሚቆጣጠረው ተቋም ኮሮናቫይረስ ባዮሎጂካል የጦር መሣሪያ እንዳልሆነ መደምደሚያ ላይ ደርሷል ሲል ቢቢሲ በድረገፁ ላይ አስነብቧል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የCIA ሪፖርት ከመውጣቱ ቀደም ብሎ ሪፖርቱን "ፀረ ሳይንስ" በማለት ውድቅ አድርጎታል።

ይህ ከዳይሬክተሩ ጽሕፈት ቤት የወጣው ሪፖርት የደኅንነቱ ማኅበረሰብ በኮሮናቫይረስ መነሻ ላይ አሁንም የተከፋፈለ አቋም መያዙን ገልጿል።

"ሁሉም ኤጀንሲዎች በቫይረሱ ከተበከለ እንስሳ ጋር በተፈጠረ ተፈጥሯዊ ንክኪ ወይም ከቤተ ሙከራ ጋር በተያያዘ ክስተት አምልጦ ይሆናል በሚሉት በሁለቱም ግምቶች ይስማማሉ" ሲል ሪፖርቱ አስነብቧል።

በሪፖርቱ ላይ ስማቸው ያልተጠቀሰ የስለላ ተቋማት፤ ኮሮና ቫይረስን ከሚሸከም እንስሳ ወይም ከቫይረሱ ጋር ቅርበት ካለው ሌላ ቫይረስ ካለበት እንስሳ ጋር በተፈጠረ ንክኪ ቫይረሱ ወደ ሰዎች ተላልፎ ይሆናል ብለው ያምናሉ። ነገር ግን በዚህ መደምደሚያ ላይ ዝቅተኛ እምነት እንዳለቸው ተጠቅሷል።

አንድ የስለላ ድርጅት ከ10 ዓመታት በላይ የኮሮና ቫይረስን በተለይም በለሊት ወፎች ላይ ሲያጠና በቆየው የዉሃን የቫይረሶች የምርምር ተቋም ውስጥ የመጀመሪያው የሰዎች ንክኪ ተፈጥሯል የሚል የተሻለ እምነት ማሳደሩ ተጠቅሷል።

የቢቢሲን ዘገባ ያንብቡ : telegra.ph/BBC-08-28

@tikvahethiopia