TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት‼️

ፓርላማው ነገ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢን ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

• የቀድሞ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ወ/ት #ብርቱካን_ሚደቅሳ ሰብሳቢ ይሆናሉ ተብሏል

• የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጉዳይ #ውሳኔ ላይ #አልተደረሰም

በነገው ዕለት አራተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሰባተኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል ተብሎ የሚጠበቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት በጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አሕመድ ዕጩ ሆነው የሚቀርቡትን የቀድሞዋ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪና የሕግ ባለሞያ ወ/ት ብርቱካን ሚደቀሳ ሹመት ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሞያው አቶ ዳንኤል በቀለ (እጩ ዶክተር) ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነርነት በዕጩነት ቀርበው በመንግሥትና በእርሳቸው በኩል የተጀመረ ንግግር ቢኖርም እስካሁን የመጨረሻ ውሳኔ ላይ አለመደረሱን ምንጮች ጠቁመዋል።

በመንግሥትና በአቶ #ዳንኤል_በቀለ መካከል ንግግር መጀመሩንና ነገር ግን ውሳኔው አለመጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል።

🔹አቶ ዳንኤል በቀለ (እጩ ዶክተር) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪና በዲቨሎፕመንት ስተዲስ በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቀዋል። እንግሊዝ ከሚገኘው ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በዓለም አቀፍና የሰብዓዊ መብቶች ሕግ በማስተርስ ተመርቀዋል። በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ሕግ ከዚያው ከኦክስፎርድ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ለመጨረስ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ ይቀራቸዋል።

አቶ ዳንኤል በቀለ በኢትዮጵያ የሕግ አማካሪና ጠበቃ ሆነው ሠርተዋል፣ በሕብረት ኢንሹራንስ የሕግ ዳይሬክተረ ነበሩ። መንግሥታዊ ባልሆነው ግብረ ሰናይ ድርጅት (Actionaid- Ethiopia ) አክሽን ኤድ ኢትዮጵያ የፖሊሲ ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል። በምርጫ 97 ከቅንጅት አመራሮች ጋር ታስረው ነበር። ከእስር ከተለቀቁ በኋላ በዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ዲቪዥን ዳይሬክተር ነበሩ።

ምንጮች እንደገለፁት አቶ ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት እዲመሩት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለና በቅርቡ ውሳኔ ላይ እንደሚደረስ ነው። በዚህ መሰረት በነገው ዕለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚቀርበው ሹመት የብሔራዊ ምራጫ ቦርድ እጩ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ብቻ ነው።

🔹ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሕግ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል። ከረዳት ዳኛነት እስከ ፌደራል ፍርድ ቤት በዳኛነት አገልግለዋል። በጥብቅና ሞያና በሕግ አማካሪነት ሠርተዋል። በ1992 ዓ.ም ተወልደው ያደጉበትን (ፈረንሳይ ለጋሲዮን) አካባቢ በመወከል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግል ተወዳዳሪ ነበሩ። የቅንጅት ፓርቲ ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር ሆነው ሠርተዋል። በእዚህ ወቅትም ለእስር ተዳርገዋል። ከእስር ከተፈቱ በኋላ አንድነት ፓርቲን በሊቀመንበርነት መርተዋል። በመጨረሻም ለሁለተኛ ጊዜ ታስረዋል። ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተጉዛ National Endowment for Democracy (NED) ኔድ በተሰኘ የታወቀ የዴሞክራሲ የምርምር ተቋም ውስጥ ተመራማሪ ፌሎ በመሆን ለአንድ ዓመት በዴሞክራሲ ላይ ምርምር አድርገዋል። በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ውስጥም (Scholars at Risk) በተሰኘ ፕሮግራም ለአንድ ዓመት ሰልጥነዋል።

በዚሁ በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ የሕዝብ አስደዳደር (Public Administration) በሁለተኛ ዲግሪ ተመረቀዋል። ምክር ቤቱ ነገ አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያን በወ/ት ብርቱካን ተክቶ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም ያልተሟሉ የምክር ቤቱን የቋሚ ኮሚቴ ሊቀ መናብርት ሹመትን ለማፅደቅ የውሳኔ ሐሳብ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ፂዮን ግርማ(ቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በአሁኗ ኢትዮጵያ በፀረ ሽብር ሕጉ ክስ መኖር #የለበትም" #ዳንኤል_በቀለ

BBC ከዳንኤል በቀለ ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ👇
https://telegra.ph/D-07-06-2