TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ 4.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበት እየተገነባ ነው የሚገኘው የተባለው የዓድዋ ዜሮዜሮ ፕሮጀክት #ወደመጠናቀቁ መሆኑ ተነግሯል። ፕሮጀክቱ በውስጡ ፦ - በዓድዋ ጦርነት የተሰዉ ጀግኖችን የሚዘክር ሙዚየም፣ - የመዝናኛ ሥራዎች፣ - ካፍቴሪያዎች፣ - ሲኒማ ቤቶችና ሁለገብ አዳራሾችን - የህፃናት መጫወቻ - አንድ ሺህ (1000) መኪና ማቆም የሚያስችል ፖርኪንግ - የንግድ ቤቶችን የያዘ ነው ተብሏል።…
#አፄምኒሊክ #እቴጌጣይቱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር " በዓድዋ ዜሮ ዜሮ " ፕሮጀክት መግቢያ ፊለፊት ላይ የአፄ ምኒሊክ እና የእቴጌ ጣይቱ ሃውልት እንደሚኖር ገልጿል።

ምኒሊክ አደባባይ የሚገኘው " የአፄ ምኒሊክ ሃይውልት ሊፈርስ ነው፤ ከቦታው ተነስቶ ወደ ሙዚየም ሊገባ ነው " የሚባለው ፍፁም #ሀሰት ሲል ገልጿል።

የከተማው ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሰጡት ቃል ፤ " በዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎሜትር ፕሮጀክት የአፄ ምኒሊክ እና የእቴጌ ጣይቱ ሃውልት ፊትለፊት ላይ ገና መግቢያው ላይ አለ፤ አዲስ ተጨምሮ። ያንን አዲስ የሚሰራ እንዴት ነው አሮጌውን የሚያፈርሰው ? ይሄ ያስኬዳል ? እንዴት ነው የበዓል ማክበሪያ ቦታ በዛ በኩል የሚደረገው ? " ሲሉ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ ፤ " አፄ ምኒሊክ የራሱ ትክክል አይደለም የምንለው የሰራቸው ጥፋቶች አሉ ብለን እናምናለን። በዓድዋ ላይ ደግሞ የሰራቸው ትልልቅ ታሪኮች አሉ። አንድ የሆነ ጥፋት ካለ  ሌላውን ሁሉ እውነት በዛ እንሸፍናለን ማለት አይደለም። የሆነ እውነት ካለ በጥፋቱ ሸፍነን እናያለን ማለት አይደለም። ታሪክን ጥፋትም ይኑር በጎ ገፅታውን ፣ መልካም ገፅታውንም እንዳለ እውነቱን ማስቀመጥ ነው ከእኛ የሚጠበቅ " ሲሉ ተናግረዋል።

" እኛ አልሰራነው፤ ለምን የአሁኑ ትውልድ መከራውን እንደሚያይ ብዙ አይገባንም። እኛ አልሰራነው ፤ ይሄ ትውልድ አልሰራው የጥፋቱንም የጀግንነት ፓርቱንም ይሄ ትውልድ አልሰራውም። ግን የራሱ ሃገር ታሪክ ነው፤ የራሱ ህዝብ ታሪክ ነው በመልካምነት የሚይዘውን ይኮራበታል፤ ይይዘዋል፤ ያሳይበታል። ትክክል አልነበረም የምንለውን አንደግመውም፤ በእኛ ዘመን መደገም የለበትም። " ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች " አሮጌ አካባቢን ባደስን ቁጥር ቅርስ ፈረሰ ነው የሚባለው ይሄ አዲስ አበባ ላይ ትልቅ የልማት እንቅፋት ሆኖብናል " ሲሉ አክለዋል።

የ " ዓድዋ ዜሮ ዜሮ " ፕሮጀክት ከጥቂት ቀናት በኃላ ለህዝብ ክፍት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia