TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Amhara #BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እና በአማራ ክልል ወረዳዎች እንደቀድሞው ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር መግባባት ላይ መደረሱ ተገለፀ።

አራት ዓመታትን ያስቆጠረው የመተከል ዞን የሰላም መደፍረስ ወደ ፍፁም ሰላም እንዲመለስ በመተከል እና በአማራ ክልል አጎራባች ወረዳዎች በትናንትናው ዕለት የምክክር መድረክ ተካሂዷል ።

የጓንጓ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ በሰጡት ቃል የትላንቱን የምክክር መድረክ " ከሁሉም የመተከል ዞን ወረዳዎች እና የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ወረዳዎች የተውጣጡ የእምነት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የፖለቲካ አመራሮች እና በአጠቃላይ ከ500 በላይ እንግዶች ተሳትፈውበታል " ብለዋል።

ኃላፊው ፥ ወረዳዎቹ ከዚህ በፊት ብዙ ተፈናቃዮችን ያስተናግዱ እንደነበር እና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የችግሩ ገፈጥ ቀማሽ እንደነበሩ ገልፀው ፤ አሁን ላይ የነበረውን ግጭት ወደ ጎን ትተው #ለእርቅ መስማማታቸውን ገልፀዋል።

ከሁለቱም ወገን እንደቀድሞው ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር መግባባት ላይ መደረሱ የተነገረ ሲሆን በቦታው ያሉ ልዩ ሀይሎች፣ መከላከያን ጨምሮ እንዲሁም ጥምር የፌዴራል ፖሊስ ሃይል ሀላፊነት እንዳለባቸው ተነስቷል።

ከዚህ በፊት ሸፍተው በጫካ የነበሩ የጉሙዝ ብሔረሰብ ተወላጆች እጃቸውን በመስጠት ትጥቅ ፈትተው፤ በባህላቸው መሠረት ዕርቅ ፈፅመው ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀላቸውን የጓንጓ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ መኮንን ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

Credit : Ethio FM 107.8

@tikvahethiopia