TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" እነዚህ የፈሪ ጥቃቶች መንግስት በማንኛውም መልኩ አሸባሪዎችን ለማጥፋት ያለውን ቁርጠኝነት ፈጽሞ አያቆሙም " - ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ ዛሬ በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ፤ ሞቃዲሾ በተፈፀመ የሽብር ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ተገደሉ። በዞቤ መንገድ ሁለት የቦምብ ጥቃቶች የተፈፀሙ ሲሆን የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ላይ የተነጣጠረ ነበር ተብሏል። በተፈፀመው የሽብር ጥቃት የፖሊስ አባል፣…
#Update

በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ትላንት በተፈፀመው የሽብር ጥቃት በትንሹ 100 ሰዎች ሲሞቱ 300 ሰዎች ተጎድተዋል።

በሁለት መኪና በተፈፀመውን የቦንብ ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ተገድለዋል።

የሶማሊያ ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ፤ የትላንቱን የሽብር ጥቃት " ጭካኔ የተሞላበት እና የፈሪዎች ጥቃት " ሲሉ ገልፀው ድርጊቱን የፈፀመው ሽብርተኛው አልሸባብ መሆኑን አመልክተዋል።

በጥቃቱ ሲቪሎች መሞታቸውን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ የአልሻባብ የሽብር ቡድን ድርጊት ተስፋ ሊያስቆርጠን አይችልም ፤ ይልቅ ለአንዴና ለመጨረሻ ጌዜ ለማሸነፍ (አልሸባብን) ያለንን ቁርጠኝነት ያጠናክራል ሲሉ ገልፀዋል።

ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ የሽብር ጥቃቱ የተፈፀመበትን ቦታ በአካል የተመለከቱ ሲሆን በጥቃቱ በትንሹ 100 ሰዎች መገደላቸውን እና 300 የሚደርሱ ሰዎች መጎዳታቸውን ገልጸዋል።

የተጎዱትን ለማከም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህክምና ዶክተሮች እና የህክምና ቁሳቁሶችን እንዲልክ ተማፅነዋል።

ህዝቡም ወደ ሆስፒታል እየሄደ ደም እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

በትላንቱ እንዲሁም በሌሎች የአልሸባብ የሽብር ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ህፃናት ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚመቻች ፕሬዜዳንቱ ቃል ገብተዋል።

የትላንቱ የመኪና የቦምብ ጥቃት በመዲናዋ ሰው ከሚበዛባቸው መገናኛዎች ውስጥ በሚገኘው #የትምህርት_ሚኒስቴር ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ተነግሯል።

@tikvahethiopia