TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ከ6,000 በላይ መፅሀፍት . . .

በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በየአመቱ የመማሪያ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ እንደሚካሄድ ይታወቃል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኃላም በጦርነት ምክንያት ለ2 ዓመት የተቋረጠው የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ዳግም ጀምሯል።

በሰኔ ወር 2014 በአዲስ አበባ ብቻ የጀመረው የመፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ እየተሰራ እጅግ በርካታ መፅሀፍትን ማሰባሰብ ተችሏል።

በኃላም ፤ በነሃሴ ወር ላይ በሀገር ወቅታዊ ሁኔታ ተቋርጦ መስከረም ወር 2015 ዓ/ም ዳግም ተጀምሮ ነበር።

እስካሁን ባለው ቆጠራ አጠቃላይ ከ6000 በላይ መፅሀፍት ተሰብስቧል።

ይህ ከቤተሰቦቻችን #በየቤታቸው_ሄደን የተቀበልናቸው እና በመላው ቤተሰቡ ስም በማስታወቂያ ገቢ የተገዙትን ይጨምራል። (በየዓመቱ በሚሰራው የመፅሀፍ ማሰባሰብ ከቲክቫህ አባላት ገንዘብ እንደማይሰበሰብ ይታወቃል)።

ይህ ዘመቻ በጥቂት ቀናት ተጠናቆ በፍጥነት መፅሀፍቱን ወደ አስፈላጊ ቦታ በማድረስ ህዳር 1/2015 የ5ኛውን ዓመት ስራ ለማጠናቀቅ ታቅዷል።

መፅሀፉ የሚያስፈልጋቸውን ትክክለኛ ትምህርት ቤቶችን እና ስንት መፅሀፍ እንደሚላክላቸው የመለየት ስራም በፍጥነት እየተሰራ ሲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግሮች እንዳለቁ እናሳውቃችኃለን።

መፅሀፍቶቹ እንደደረሱም " በመፅሄት መልክ " በፎቶ ሪፖርት አቅርበን መፅሀፍ ላበረከቱ ቤተሰቦቻችን እንልካለን።

በቀጣይ ጥቂት ቀናት መፅሀፍት ለመሥጠት የምትፈልጉ ደውሉልን 0919743630 / መፅሀፍ ገዝታችሁ መስጠትም የምትፈልጉ በገንዘብ መልክ የምንቀበልበት ምንም መንገድ ስለሌለ መፅሀፉን ገዝታችሁ ያላችሁበትን ድረስ መጥተን እንወስዳለን።

አጠቃላይ የመፅሀፍት ዝርዝር በቀጣይ ሲጠናቀቅ እናሳውቃለን።

#TikvahFamily❤️

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኤር_ኤክስፕረስ_አፍሪካ ኤር ኤክስፕረስ አፍሪካ የግል የአውሮፕላን አየር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ሆኖ በኢትዮጵያ ተመዘገበ። የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ፤ ኤር ኤክስፕረስ አፍሪካ የግል የአውሮፕላን አየር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ሆኖ መመዝገቡን አሳውቋል። ተቋሙ ምዝገባውን በስኬት ያጠናቀቀው አለም አቀፍ አሰራርን ተከትሎ የተቀመጠውንና በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን…
#ETHIOPIA

በሀገራችን ኢትዮጵያ 13ኛው የግል የአውሮፕላን አየር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ተመዝግቧል።

13ኛው የግል የአውሮፕላን አየር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ሆኖ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የተመዘገበው " ጎልድ ስታር አቪዬሽን " ነው።

ተቋሙ ምዝገባውን በስኬት ያጠናቀቀው ዓለም አቀፍ አሰራርን ተከትሎ የተቀመጠውንና በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የሚተገበሩትን 5 ደረጃዎችን (five phases) በስኬት አጠናቆ በመገኘቱ ነው።

በውስጣቸው በርካታ ተግባራትን የያዙት አምስት ስታንዳርዶች pre-application, formal application, Document evaluation and Inspection and finally Certification የሚባሉ ሲሆን ጎልድ ስታር ትላንት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር የተፈረመበትን ሰርትፊኬት በይፋ ተቀብሏል፡፡

በአሁን ሰዓት በሀገራችን " ጎልድ ስታር አቪዬሽን " ን ጨምሮ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ተመዝግበው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የአውሮፕላን አየር ትራንስፖርት ተቋማት 13 ደርሰዋል፡፡

" ጎልድ ስታር አቪዬሽን " የእውቁ ባለሀብት #ወርቁ_አይተነው ድርጅት መሆኑን ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
" እነዚህ የፈሪ ጥቃቶች መንግስት በማንኛውም መልኩ አሸባሪዎችን ለማጥፋት ያለውን ቁርጠኝነት ፈጽሞ አያቆሙም " - ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ

ዛሬ በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ፤ ሞቃዲሾ በተፈፀመ የሽብር ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ተገደሉ።

በዞቤ መንገድ ሁለት የቦምብ ጥቃቶች የተፈፀሙ ሲሆን የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ላይ የተነጣጠረ ነበር ተብሏል።

በተፈፀመው የሽብር ጥቃት የፖሊስ አባል፣ አንድ ጋዜጠኛን ጨምሮ ሴቶች እና ህፃናት ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።

ፖሊስ አጠቃላይ የደረሰውን ጉዳት በዝርዝር ለመግለፅ የሟቾች እና የቆሰሉ ሰዎችን መረጃ ለማሰባሰብ እየሰራ ነው።

ከተጎዱት መካከል የሮይተርስ የፎቶ ጋዜጠኛ እና የቪኦኤ ፍሪላንሰር እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።

እስካሁን ለሽብር ጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል ብቅ ባይልም ድርጊቱን የፈፀሙት የአልሸባብ ሚሊሻዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል ፤ የሶማሊያጠቅላይ ሚንስትር ሀምዛ አብዲ ባሬ በሞቃዲሾ ሴቶችን እና ህጻናትን ጨምሮ የንፁሀን ዜጎችን ህይወት የቀጠፈውን አሰቃቂ የሽብር ጥቃት በፅኑ ማውገዛቸውን የሀገሪቱ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " እነዚህ የፈሪ ጥቃቶች መንግስት በማንኛውም መልኩ አሸባሪዎችን ለማጥፋት ያለውን ቁርጠኝነት ፈጽሞ አያቆሙም " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እነዚህ የፈሪ ጥቃቶች መንግስት በማንኛውም መልኩ አሸባሪዎችን ለማጥፋት ያለውን ቁርጠኝነት ፈጽሞ አያቆሙም " - ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ ዛሬ በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ፤ ሞቃዲሾ በተፈፀመ የሽብር ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ተገደሉ። በዞቤ መንገድ ሁለት የቦምብ ጥቃቶች የተፈፀሙ ሲሆን የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ላይ የተነጣጠረ ነበር ተብሏል። በተፈፀመው የሽብር ጥቃት የፖሊስ አባል፣…
#Update

በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ ትላንት በተፈፀመው የሽብር ጥቃት በትንሹ 100 ሰዎች ሲሞቱ 300 ሰዎች ተጎድተዋል።

በሁለት መኪና በተፈፀመውን የቦንብ ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ሲቪሎች ተገድለዋል።

የሶማሊያ ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ፤ የትላንቱን የሽብር ጥቃት " ጭካኔ የተሞላበት እና የፈሪዎች ጥቃት " ሲሉ ገልፀው ድርጊቱን የፈፀመው ሽብርተኛው አልሸባብ መሆኑን አመልክተዋል።

በጥቃቱ ሲቪሎች መሞታቸውን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ የአልሻባብ የሽብር ቡድን ድርጊት ተስፋ ሊያስቆርጠን አይችልም ፤ ይልቅ ለአንዴና ለመጨረሻ ጌዜ ለማሸነፍ (አልሸባብን) ያለንን ቁርጠኝነት ያጠናክራል ሲሉ ገልፀዋል።

ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ የሽብር ጥቃቱ የተፈፀመበትን ቦታ በአካል የተመለከቱ ሲሆን በጥቃቱ በትንሹ 100 ሰዎች መገደላቸውን እና 300 የሚደርሱ ሰዎች መጎዳታቸውን ገልጸዋል።

የተጎዱትን ለማከም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህክምና ዶክተሮች እና የህክምና ቁሳቁሶችን እንዲልክ ተማፅነዋል።

ህዝቡም ወደ ሆስፒታል እየሄደ ደም እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

በትላንቱ እንዲሁም በሌሎች የአልሸባብ የሽብር ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ህፃናት ነፃ የትምህርት ዕድል እንደሚመቻች ፕሬዜዳንቱ ቃል ገብተዋል።

የትላንቱ የመኪና የቦምብ ጥቃት በመዲናዋ ሰው ከሚበዛባቸው መገናኛዎች ውስጥ በሚገኘው #የትምህርት_ሚኒስቴር ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ ፤ " የቢጫ ወባ ክትባት " መጀመሩን እና አገልግሎቱን የሚፈልጉ በአገልግሎቱ መጠቀም እንደሚችሉ አሳውቆናል።

@tikvahethiopia
" ከ3 ሳምንት ያላነሰ ጊዜ የሚፈልገውን ሥራ  በአንድ ሳምንት ነው ያጠናቀቁት " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት ጉዳት ደርሶበት የነበረው የወልዲያ አላማጣ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።

ያለዕረፍት በተሰራ ሥራ የማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና እና የተሰበሩ ኢንሱሌተሮች ቅየራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ መስመሩን መፈተሽ እንደተገጀመረ ነው የተገለፀው።

በአንድ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የደረሰ ጉዳት በቀጣይ የሚጠገን ሲሆን የምሰሶው ጉዳት ግን መስመሩን ኃይል ከመስጠት የሚያግደው አይደለም ተብሏል።

በጥገና ሥራው ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች ከሦስት ሳምንት ያላነሰ ጊዜ የሚፈልገውን ሥራ  በአንድ ሳምንት እንዳጠናቀቁት ነው የተነገረው።

ከወልዲያ እስከ አላማጣ ማከፋፈያ ጣቢያ ድረስ ያለው መስመር ጥገና መጠናቀቅ ከአላማጣ ማከፋፈያ ጣቢያ በ66 ኪሎ ቮልት ኃይል ሲያገኙ የነበሩት ፦
- ላሊበላ፣
- ሰቆጣ
- ቆቦ እንዲሁም ማይጨው እና አካባቢያቸው ኃይል እንዲያገኙ ያስችላል።

መረጅው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PeaceTalks የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ እና ፖለቲካዊ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ በአፍሪካ ህበረት (AU) መሪነት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል። እስካሁን የንግግሮቹን ይዘት በተመለከተ ምንም አይነት መረጃ አልወጣም። በዛው ያሉ ሚዲያዎችም ስለ ሰላም ንግግሩ እና ስለሂደቱ መረጃ የሚያገኙበት መንገድ እንዳይኖር ተደርጓል።…
#PeaceTalks

ትላንት እሁድ ይጠናቀቃል ተብሎ ቀጠሮ የተያዘለት በደቡብ አፍሪካ እየተደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ ሰኞም እንደሚቀጥል ተሰምቷል።

ኤፒ አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ባለስልጣን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ የሰላም ንግግሩ ዛሬም ይቀጥላል።

ከኤፒ በተጨማሪም " SA FM RADIO " የሰላም ንግግሩ ዛሬ እንደሚቀጥል ዘግቧል።

የሰላም ንግግሩን ይዘትና አጠቃላይ አሁን ላይ የደረሰበትን ሂደት በተመለከተ ምንም ይፋዊ መረጃ የለም። የሰላም ንግግሩ ሚዲያዎች መረጃ ሊያገኙበት በማይችል ሁኔታ እየተካሄደ ነው።

ለሰላም ንግግሩ ቅርብ የሆኑ አንድ ባለስልጣን ንግግሩ ምን እድገት እንዳሳየ ሲጠየቁ፤ " እሱን ጊዜ ብቻ ነው የሚነግረን " ሲሉ መልሰዋል።

ሌሎች ምንጮች ደግሞ የሰላም ንግግሩ ዝግ እያለ እየሄደ ቢሆንም በአካል ተገናኝቶ ፊት ለፊት መነጋገሩ ተቀባይነትን እንዳገኘ አመላክተዋል።

በግጭት ማቆም፣ በሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነት እና በወሳኝ መሰረታዊ አገልግሎቶች እንደገና መጀመር ላይ በተደረገ ንግግር "ትልቅ እድገት" ታይቷል ሲሉ እነዚህ ምንጮች ገልፀዋል።

የሰላም ንግግሩ " ወደ ተኩስ አቁም ይመራል " የሚል ተስፋ እንዳላቸው ሙሳ ፋኪ መሀመት ከቀናት በፊት ተናግረው እንደነበር ይታወሳል።

እስካሁን ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች/ አዘጋጆች በኩል በቀጥታ የተሰጠ ይፋዊ መረጃ የለም፤ የሰላም ንግግሩ አዘጋጆች የንግግሮችን ይዘትና ሂደት በተመለከተ ከሚዲያዎች ርቀው ዝግ በሆነ መንገድ ነው እያስኬዱ የሚገኙት።

ውድ ቤተሰቦቻችን ከላይ ያነበባችሁት መረጃ የተሰባሰበው፦ ከ "The Star kenya" ጋዜጠኛው ኢሊዩድ ኪቢ፣ SA FM RADIO/SABC፣ ከDaily Maveric/South Africa/ እንዲሁም ከኤፒ ነው።

@tikvahethiopia