TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.5K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ERCS • የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የአምቡላንስ ሹፌር በታጣቂዎች ተገደለ። • ማኅበሩ በባልደረባው ሞት የጥልቅ ሐዘን እንደተሰማው ገልጾ ግድያውን አውግዟል። ታጣቂ ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ማህበሩ ተማፅኗል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰሜን ጎንደር ቅርንጫፍ #የአምቡላስ_ሾፌር የነበረው አቶ መንግስት ምንይል ታጣቂ ሃይሎች በፈፀሙት ጥቃት ተገድለዋል። ማህበሩ፤ ግድያውን በአፅንዖት…
#Update

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና የተመድ ሰብዓዊ ጉዳዮች በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል የአምቡላንስ ሹፌር ግድያ የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰሜን ጎንደር ቅርንጫፍ አምቡላንስ ሹፌር አቶ መንግስት ምንይል ላይ በደረሰው አሰቃቂ ሞት ድንጋጤ እና ጥልቅ ሐዘን እንደተሰማው የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ገልጿል።

" በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በተከሰተበት አካባቢ በስራ ላይ እያሉ ነው የተገደሉት፡፡ " ያለው ኮሚቴው " ሀሳባችን እና ጥልቅ ሀዘናችን ከሟች ቤተሰቦች፣ ከኢቀመማ ሰራተኞች እና በጎ ፈቃደኞች ጋር ነው " ብሏል።

በአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግ (IHL), የህክምና ሰራተኞች፣ ሆስፒታሎች እና ሌሎች የህክምና ክፍሎች እንዲሁም  አምቡላንስ እና ሌሎች የህክምና መጓጓዣዎች ለህክምና ተግባራት ወይም ዓላማዎች ብቻ የተመደቡ፣ በማንኛውም ሁኔታ #ሊከበሩ እና #ሊጠበቁ ይገባል ሲል ገልጿል።

ኮሚቴው ፤ በህክምና ሰራተኞች፣ በቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ እንቅስቃሴ ሰራተኞች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች እና የቀይ መስቀል ወይም ቀይ ጨረቃ አርማ የሚያሳዩ ነገሮችን ማጥቃት የተከለከሉ ናቸው ብሏል።

" የእርዳታ ሰራተኞች የጥቃት ኢላማ አይደሉም " ሲል አክሏል።

በተመሳሳይ ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሃፊና የአስቸኳይ ድጋፍ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ ግድያውን "አሰቃቂ" ሲሉ ገልፀው ለአቶ መንግስት ቤተሰቦች እና በዓለም ላይ እንዲሁም በኢትዮጵያ ለሚገኙት የICRC ሰራተኞች በሙሉ መፅናናትን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፤ አቶ መንግስት ምንይል በትግራይ፤ ዓድዋ በግጭት የተጎዱ ሰዎችን በማገዝ ስራ ላይ እያሉ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት መገደላቸውን ማሳወቁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia