TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ታላቅ አለም አቀፍ የዳዕዋ ዝግጅት በቡታጀራ ከተማ!

ከ 1 መቶ ሺህ በላይ ኢትዮጵያዋንም ጨምሮ የአለም ሀገራት የእስልምና እምነት ተከታዮችን እንግዶች ተቀብላ እያስተናገደች ነዉ። "አበሻ እጅቲማዕ" በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ይህ በሀገራችን ለመጀመርያ ጊዜ የሚካሄደዉን ታላቅ አለም አቀፍ የዳዕዋ ዝግጅት ነዉ። ከህንድ ፣ከሱዳን ፣ከኬንያና ከሌሎች የአለም ሀገራት የተዉጣጡ የእስልምና እምነት ተከታዮች የዳዕዋዉ ተሳታፊ ናቸዉ።

ከ1 መቶ ሺህ በላይ አትዮጵያዉያን ጨምሮ የአለም ሀገራት እያስተናገደች ትገኛለች። "አበሻ እሽቲማ" ዳዕዋ ከሕዳር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት ማለት እስከ እሁዱ የሚቀጥል ነዉ፡፡

የከማዉ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸዉን ለእንግዶች ክፍት አድርገዉ እንግዳ የመቀበል ባህላቸዉን በከፍተኛ ሁኔታ እያንጸባረቁ ነዉ። ከተለያዩ የአለም ሃገራት ማለትም ከአፍሪካና ከአውሮፓ ሃገሮች ከ አንድ መቶ ሺህ በላይ የእስልምና የእምነቱ ተከታዮች የዳዕዋዉ ተሳታፊዎች ናቸዉ።

(Gurage Zone Administration Public Relation Office)

#SRTA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

በሀዋሳ ከተማ በቱላ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ኩቤ ካባ ተብሎ በሚጠራው የድንጋይ ማምረቻ ካባ ተደርምሶ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ!

በሀዋሳ ከተማ በቱላ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ኩቤ ካባ ተብሎ በሚጠራው የድንጋይ ማምረቻ ከቀኑ አምስት ሰዓት ገደማ የድንጋይ ካባ ተደርምሶ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

የድንጋይ ከባው ለረዥም ዓመታት ለሀዋሳ ከተማ እና አካባቢው ለግንባት የሚውል ድንጋዮች የሚመረትበት ሲሆን በዛሬው ዕለት በደረሰው የካባ ድንጋይ መናድ በሁለት ሰዎች ላይ የሞት አደጋ የደረሰ ሲሆን በሦስት ግለሰቦች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ኮለኔል ሮዳሞ ኪአ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ገልፀዋል፡፡

ሟቾቹሁ የድንጋይ ካባውን በማውጣት ስራ ላይ የተሰማሩት የስካቫተር ሹፌርና የጉልበት ሰራተኛ መሆኑ ታውቋል፡፡

ሌሎች ጉዳት ደረሰባቸው ተጎጂዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆን ኮለኔል ሮዳሞ ኪአ ገልፀው የአደጋው ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

[ምንጭ፦ #SRTA, PHOTO : Tikvah Family]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ስታድየም ደርሰዋል። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝም በጂንካ ስታዲየም ተገኝተዋል። የአገር ሽማግሌዎች ኘሮግራሙን በምርቃት ጀምረዋል። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስታዲየሙ ለተገኘው ህዝብ መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል።

#SRTA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HAWASSA

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ዛሬ በሰጠው መግለጫ #ሁሉም አሽከርካሪዎች እና ተሳፋሪዎች ከመጪው ሰኞ ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የፊትና የአፍ መሸፈኛ ማስክ የማድረግ ግዴታ እንደሚኖርባቸው አሳውቋል።

ይህን መመሪያ በሚተላለፉ አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ መምሪያው በጥብቅ አስታውቋል፡፡

መመሪያው በመላው ሀገሪቱ #እየጨመረ የሚገኘውን ፤ እንዲሁም ወደ ከተማው የመግባት አዝማሚያ እያሳየ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል ይረዳል ተብሎ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

የባለ 2 እግር ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችን እንዲሁም የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ረዳቶችና ተሳፋሪዎችን ፤ እንዲሁም የግልና የመንግስት መኪና አሽከርካሪዎችና ተሳፋሪዎችን፤ ባጃጅና የመሳሰሉትን አነስተኛ የትራንስፖት ዘርፎች የሚያካትት ነው።

አሽከርካሪዎች ይህንን አውቀው በቀጣይ ሁለት (2) ቀናት ውስጥ ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የፊት ማስኮችን አድርገው መንቀሳቀስ እንደሚኖርባቸው ተገልጿል፡፡

#SRTA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በዛሬ መሰጠት ተጀመረ። #SRTA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በሐመር ወረዳ የአንበጣ መንጋ ተከስቷል !

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ ተከስቷል።

የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

አርሶ አደሩ የደረሱ ሰብሎችን ከማሳ ላይ ፈጥኖ መሰብሰብ እንደሚገባም ተገልጿል። #SRTA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30 ይሰጣል።

በደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 28 እስከ 30 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ የተማሪዎች መመዝገቢያ ቅጽ እንግሊዝ ሀገር ከሚገኝ DRS ድርጅት ግዢ እንደተፈጸመና ቢሮ መግባቱን አሳውቋል።

የቅጽ አሟላሉን በተመለከተ በክልሉ ለሚገኙ ሁሉም የፈተና ክፍል ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን ቢሮው ገልጿል።

በክልሉ የሚገኙ 16 ዞኖችና 7 ልዩ ወረዳዎች ፎርሙን ወስደው በመንግስትና በግል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን እያስሞሉ ነው ተብሏል።

የፈተና ዝግጅት ተጠናቆ የህትመት ስራ እየተሰራ ይገኛል።

ፈተናው በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30/2013 ይሰጣል ተብሏል። #SRTA

@tikvahethiopia
#ማሻሻያ

በደቡብ ክልል ለአስቸኳይ አዋጁ ማስፈጸሚያ የተጣሉ ገደቦች ላይ ማሻሽያ መደረጉን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል።

በክልሉ ነዋሪዎች እጅ የሚገኘውን የጦር መሳሪያ ለመመዝገብ እስከ ህዳር 10/2014 ድረስ በገደብ የተያዘ ስራ የተሰራ ሲሆን በዚህም ወቅት 27 ሺሕ 477 የጦር መሳሪያዎች ተመዝግቧል።

ነገር ግን በክልሉ አለ ተብሎ ከሚገመተው አንጻር ቁጥሩ ዝቅተኛ ነው።

የምዝገባው ጊዜ አጭር በመሆኑና በተላያዩ ምክንያቶች የምዝገባውን ጊዜ ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እስከ ሕዳር17/2014 ዜጎች በእጃቸው ያለውን የጦር መሳሪያ በአፋጣኝ ወደ ሚመለከተው አካል ቀርበው እንዲያስመዘግቡ ተብሏል።

ይሄን መመሪያ ተላልፈው የጦር መሳሪያ ይዘው በተገኙ ግለሰቦች ላይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት አስፈላጊው ሕጋዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተብሏል።

እስካሁን ባለው ከ80 ሺህ በላይ የሚሆኑ ባለ 2 ሞተር ሳይክሎች ተመዝግበው ወደ ህጋዊ ሰርዓት የገቡ ሲሆን አሁንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሞተር ሳይክሎች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደ ምዝገባው አልመጡም።

በዚህም ተጫማሪ ሰባት ቀናት የምዝገባ እድል የተሰጠ በመሁኑ ባለንብረቶች እስከ ህዳር 17/2014 ድረስ እድሉ እንዲጠቀሙ ተብሏል።

ከዚህ በፊት በ2 እግር ሞተር ስይክልና ባለ3 እግር ባጃጆች እስከ አመሻሽ 12 ሰዓት ባለው ጊዜ ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ መመሪያ የተላለፈ ሲሆን አሁን ግን ከጥብቅ ቁጥጥር ጋር እስከ ምሽት 2 ሰዓት ድረስ ፍቃድ ተሰጥቷል።

ሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ ተነስቶ በጥብቅ ቁጥጥር ተተክቷል።

#SRTA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል ዛሬ እና ነገ ይመሰረታል። 5 ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ ሆነው የሚያቋቁሙት የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ዛሬና ነገ በሚካሄዱ መርሀ ግብሮች 11ኛው ክልል ሆኖ በይፋ ይመሰረታል፡፡ ለክልሉ ምስረታ ከአምስቱ ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ የተውጣጡ የሥራ ሃላፊዎች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡ ከትላንት ምሽት ጀምራ የክልል እና የፌደራል እንግዶች ለክልሉ…
#Update

ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ በሀገራችን 11ኛው የክልል መንግሥት በይፋ ይመሰረታል።

11ኛው የክልል መንግሥት ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በቦንጋ ከተማ ይመሰረታል።

በቦንጋ እየተካሄደ በሚገኘው የክልል ምስረታ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ እንግዶችና ከ6ቱም መዋቅሮች የተገኙ የህዝብ ተወካዮች፣ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ የሃይማኖት አባቶችና ምሁራን እንዲሁም ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

#SRTA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" እስካሁን ባለው የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ ፤ ሁለት ከባድ ጉዳት እና ሌሎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና ላይ ይገኛሉ " - የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ

ዛሬ ጠዋት የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋናውን ግቢ እና የቴክኖሎጂ ካምፓስ ግቢን የሚያገኛኘው ድልድይ ተደርምሶ በደረሰው ጉዳት እስካሁን ባለው የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ እና ሁለት ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ይህን የገለፀው የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ነው።

የሲዳማ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሰጡት ቃል ፤ " እስከአሁን ባለው ሂደት በጉዳቱ የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ፣ ሁለት ከባድ ጉዳት እና ሌሎች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል " ብለዋል።

እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲከሰቱ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጆችና ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ ከሚመለከተው አካል ብቻ በማግኘት እንዲያረጋግጡና እንዲረጋጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#SRTA

@tikvahethiopia
#ATTENTION

" በድርቅ እና ለረጅም ጊዜ በተከሰተ የፀጥታ ችግር ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በርካት ሰዎች ለአደጋ ተጋልጠዋል " - የአማሮ ልዩ ወረዳ

• " ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለረሀብ፣ ለበሽታ እና ለሞት እየተዳረጉ ነው " - የቡርጂ ልዩ ወረዳ

በደቡብ ክልል አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች በተከሰተ ድርቅ ምክንያት ከ136 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።

#አማሮ

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የአማሮ ልዩ ወረዳን ዋቢ አድርጎ ባሰራጨው መረጃ ፤ በልዩ ወረዳው ለረጅም ጊዜ ዝናብ ባለመጣሉ በ22 ቀበሌዎች ድርቅ ተከስቷል፡፡

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በልዩ ወረዳው ከ96 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

በድርቁ ከ3 ሺህ 500 በላይ የቤት እንስሳት በድርቁ ምክንያት መሞታቸው ተገልጿል።

በልዩ ወረዳው የተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች የህብረተሰቡን ተጋላጭነት እንዳባባሱት ልዩ ወረዳው አመልክቷል።

በድርቁ እና ለረጅም ጊዜ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በርካት ሰዎች ለአደጋ መጋለጣቸው ተገልጿል።

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በተለያየ ጊዜ እርዳታ ቢያደርግም በልዩ ወረዳው ከከተከሰተው ጉዳት አንፃር ድጋፉ በቂ አለመሆኑን ልዩ ወረዳው አሳውቋል።

#ቡርጂ

የቡርጂ ሶያማ ልዩ ወረዳ በበኩሉ በልዩ ወረዳው በተከሰተው ድርቅ 83 ሺህ 528 ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አሳውቋል።

በልዩ ወረዳው ከ30 ሺህ በላይ እንስሳት መሞታቸውም ተጠቁሟል።

ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለረሀብ፣ ለበሽታ እና ለሞት እየተዳረጉ መሆኑ ተገልጿል።

ከክልሉ መንግስት በተጫማሪ የአካባቢው ተወላጆች እና ግለሰቦች እርዳታ ቢያደርጉም በልዩ ወረዳው ከተከሰተው ድርቅ አንፃር የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት በቂ አለመሆኑ ተመላክቷል።

በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት እና መልሶ ለማቋቋም ረጂ ድርጅቶችን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረታቸውን ወደ ልዩ ወረዳው እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#ኮንሶ

በኮንሶ ዞን በተከሰተ ድርቅ ከ800 ሺህ በላይ ዜጎች ለአስቸኳይ ድጋፍ መዳረጋቸውን ዞኑ አሳውቋል።

ለተከታታይ 5 ዓመት የተከሰተው የዝናብ መዘግየት እና እጥረት ባስከተለው ድርቅ ለአስቸኳይ ድጋፍ የተዳረጉት 822 ሺ 526 ዜጎቻችን ናቸው።
 
የተከሰተው ድርቅ ዜጎች ላይ አስከፊ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ሊደረግ ይገባል ተብሏል።

Credit : #FBC #SRTA

@tikvahethiopia