TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Turkey #Ethiopia የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ አካሂዶት በነበረው 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ከቱርክ ሪፐብሊክ ጋር የተደረጉ ወታደራዊ የትብብር ስምምነቶችን ላይ ውይይት አድርጓል። ምክር ቤቱ ፤ ቱርክና ኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገረ ጥብቅ ወዳጅነት ያላቸው መሆኑን በማስታወስ ቱርክ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን አጋር መሆኗን በተደጋጋሚ ያረጋገጠች አገር ናት ብሏል። በዚህ መነሻነት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ…
#Ethiopia #Turkey

የኢትዮጵያ ፓርላማ በ #ኢትዮጵያ እና #ቱርክ መካከል የተደረጉ ወታደራዊ ስምምነቶችን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ፓርላማው ስምምነቱን ያፀደቀው ባካሄደው ሰባተኛ መደበኛ ስብሰባው ነው።

ኢትዮጵያ እና ቱርክ ወታደራዊ ትብብሮችን ለማድረግ የሚያስችላቸውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ.ም በቱርክ አንካራ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

ከስምምነቱ መካከል በጥቂቱ ፦

(የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት)

➡️ ዓላማ፦ በ2ቱ አገሮች መካከል በመከላከያ ዘርፍ የሚደረገው ግንኙነት የሚመራበትን ግልጽ ማዕቀፍ ለመፍጠር ነው።

➡️ የስምምነቱ ይዘት ፦ በሁለቱ ሀገራት በትምህርት እና ስልጠና በተናጠልና በጋራ በሚዘጋጁ ወታደራዊ ልምምዶች ስለመካፈል፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪ፣ የመረጃ ልውውጥ፣ የሎጅስቲክ፣ የጤና አገልግሎት፣ የመረጃ ስርአት እና የሳይበር ጥቃትን መከላከልና በሌሎች ተያያዥ መስኮች ፣ ከመደበኛ ጦርነት ውጭ ባሉ የሰላም ማስከበር ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን ያካተተ ነው።

➡️ በኢትዮጵያ ላይ የሚጥለው ግዴታ ፦ ሚስጥራዊ መረጃዎች፣ ሰነዶች እና ማቴሪያሎች ፣ አእምሮአዊ ንብረቶችን አስፈላጊውን ጥበቃ የማድረግ ኢትዮጵያ ለትምህርት እና ስልጠና ወደ ቱርክ ለምትልካቸው የመከላከያ አባላት እና ተማሪዎች በተቀባይ ሀገር የማይሸፈኑትን የህክምና ወጪዎችን ፣ ሌሎችንም የትምህርት እና ስልጠና ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ ይጥላል።

➡️ ከዚህ ስምምነት ኢትዮጵያ የምታገኘው ጥቅም ፦ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ፣ የሎጅስቲክ አቅርቦቶችን እና ድጋፎችን ለማግኘት የሰራዊት ትጥቆችን እንዲሁም በሰው ኃይል እና አስተዳደር ዙሪያ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ፣ የትምህርትና ስልጠና እድሎችን ለማግኘት ያስችላል።

(የወታደራዊ ፋይናንስ ትብብር ስምምነት)

➡️ ዓላማው ፦ በሁለቱ ሀገራት መካከል በመከላከያ ዘርፍ የሚደረገው ግንኙነት የሚመራበት ግልፅ የህግ ማዕቀፍ በመፍጠር የቱርክ መንግስት 100 ሚሊዮን የቱርክ ሊሬ ተመጣጣኝ የሆነ የአሜሪካ ዶላር ለኢትዮጵያ መንግስት ፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ለመከላከያ ዓላማ የሚውል 100% በቱርክ ሀገር የተመረቱ የመከላከያ ቁሳቁሶችን እና አገልግሎቶችን መግዛት የሚችልበትን መርዕ ለመወሰን ነው።

➡️ የስምምነቱ ይዘት ፦ የቱርክ መንግስት 100 ሊሬ ተመጣጣኝ የአሜሪካ ዶላር ለኢትዮጵያ መንግስት ስለሚሰጥበት ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት በዋናነት በቱርክ ከሚገኙ ኩባንያዎች 100% በቱርክ የተመረቱ የመከላከያ ቁሳቁሶችንና አገልግሎቶችን መግዛት የሚችልበትን መርህ ይደነግጋል።

➡️ በኢትዮጵያ ላይ የሚጥለው ግዴታ ፦ በሁለቱ ሀገራት የመረጃ ልውውጥ የተገኙ እና ሚስጥራዊ ተብለው የተለዩ መረጃዎችን ከሌላኛው ወገን የፅሁፍ ፍቃድ ሳይገኝ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ያለ መግለፅ እና ሚስጥራዊ መረጃዎችን መጠበቅ እንዲሁም ከቱርክ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የተላለፈ ሀብት ፣ እቃ ወይም አገልግሎት ያለ ቱርክ መንግስት የፅሁፍ ፍቃድ ለሌላ ሀገር ወይም ሶስተኛ ወገን እንዳይተላለፍ ወይም ጥቅም ላይ እንዳይውል የማድረግ ግዴታን ይጥላል።

➡️ ከስምምነቱ ኢትዮጵያ የምታገኘው ጥቅም ፦ ኢትዮጵያ ከቱርክ መንግስት የምታገኘው 100 ሚሊዮን የቱርክ ሊሬ ተመጣጣኝ የአሜሪካ ዶላር ወታደራዊ ቁሳቁስ እና አገልግሎት ከቱርክ ድርጅቶች በመግዛት ለአስፈላጊ አገልግሎት ማዋል እንድትችል ያደርጋታል።

#Ethiopia_Turkey
#ኢትዮጵያ_ቱርክ #ወታደራዊ_ስምምነቶች

@tikvahethiopia