TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" አሁንም ኢትዮጵያ ውስጥ ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ የማያውቁ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ " - የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል (ICRC) ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 9 ወራት በተለይ በጦርነት በተጎዳው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢ ቤተሰቦችን ለማገናኘት ከ185,000 #የስልክ_ጥሪዎችን እና #የመልዕክት_ልውውጦችን ማድረጉን ገልጿል።

በሰብዓዊ ቀውስ ምክንያት ቤተሰቦች ሲለያዩ በሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጭንቀት እና የስነልቡና መታወክ በማሰብ ይህን አገልግሎት እንደሚሰጥ እንደሆነ አመልክቷል።

በኢትዮጵያ ICRC አስተባባሪ ክርስቲና ሶፊያ ኢምባህ ፎን አክስ ፤ " ለሁሉም ወገን አስቸጋሪ በመሆኑ፤ እርግጠኛ ያለመሆን አስፈሪ ነው። የበለጠ የደህንነት ስሜት እንዲፈጠር የቤተሰብ ግንኙነት እንዲቀጥል እንሠራለን " ብለዋል።

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ የቀይ መስቀል ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነ ከውጪ ሀገር የሚኖሩ የተለያዩ ቤተሰቦች እንዲገናኙ ለማድረግ ቁጥርተኛ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ICRC ፤ የሚቻል ፣ የሚፈለግ ሲሆን እና አስተማማኝ ሁኔታ ሲፈጠርም ቀይ መስቀል ቤተሰቦች ዳግም እንዲገናኙ የሚያመቻች ቡድን እንዳለው ተገልጿል።

ከ2021 ጥር ወር ጀምሮ በግጭትና ቀውስ ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ #ለመለያየት_ለተገደዱ_ቤተሰቦች በአጠቃላይ እስካሁን 367,000 የተሳካ የስልክ ጥሪ እና የመልዕክት ልውውጥ ማድረጉን የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል።

ቀይ መስቀል አሁንም ኢትዮጵያ ውስጥ ቤተሰቦቻቸው #የት_እንዳሉ_የማያውቁ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖራቸውን ገልጿል።

ሰዎቹ በግጭት ቀጣና ወይም በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት በደረሰበት ስፍራ ላይ በመሆናቸው እና ሊያገኟቸው ባለመቻላቸው " #ምን_ደርሶባቸው_ይሆን ? " በሚል ጭንቀት ውስጥ እንደሚገኙ አመልክቷል።

አሁንም ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል በጋራ በመሆን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉትን ሳይቀር አድራሻቸውን በማፈላለግ ለማገናኘት ጥረታቸውን እንደቀጠሉ ተመላክቷል።

ሌላው ቀርቶ ፤ የመገናኛ አገልግሎት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ሳይቀር የሳተላይት ስልኮችን በመጠቀም ለአንድ ወይም ለሁለት ደቂቃ በመደወል የተጠፋፉ ቤተሰቦች ስለደህንነታቸው ድምጽ እንዲሰማሙ እያደረገ መሆኑን ቀይ መስቀል ማስታወቁን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia