TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አስቸኳይ

“ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ‘1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን #ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን’ አሉኝ ” - የታጋች እናት

በሊቢያ ደላሎች የታገተው የሀዋሳው ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ወጣት ጌድዮ ሳሙኤል፣ በአጋቾቹ ልዩ ልዩ ድብደባዎች እየተፈጸሙበት እንደሚገኝ ፣ አጋቾቹ ወጣቱን ለመልቀቅ 1.7 ሚሊዮን ብር እንደጠየቁ፣ ገንዘቡ በፍጥነት ካልገባ “ እንገድለዋለን ” በማለት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደሰጡ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

የታጋቹ እናት ወ/ሮ ገነት ጥላሁን ይግለጡ በሰጡት ቃል፣ “ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ‘1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን’ አሉኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ እባካችሁ ልጄን ታደጉኝ ” ሲሉ እያለቀሱ ጠይቀዋል።

“ በሄደ በ17 ቀኑ ከሊቢያ ስልክ በጓደኛው አማካኝነት ተደወለልኝ። ስልኩን ሳነሳ ‘ሊቢያ ላይ ተይዟልና 950 ሺሕ ብር ተጠይቋል’ ብሎ ጓደኛው ነገረኝ ” ያሉት የታጋቹ እናት፣ “ ከዚያ ወዲያውኑ ደግሞ ሊቢያዎቹ እየገረፉት ምስል ላኩልኝ። አካውንትም ላኩልኝ ‘ገንዘብ ላኪ’ ብለው ” ሲሉ አስረድተዋል።

አክለውም፣ “ እንደገና ለ3ኛ ጊዜ መደኃኒት ሰጥተውት እንደ እብድ እያደረገው ቪዲዮ ላኩልኝ። እንደገና ለ4ኛ ጊዜ ደግሞ ወደ ታች #ዘቅዝቀው #እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ከዚያ ‘ተሽጧል 1.7 ሚሊዮን ብር አምጭ’ ብለው ደወሉ። ቪዲዮ እያሳዩም ‘1.7 ሚሊዮን ብር ታመጫለሽ አታመጭም?’ አሉኝ ” ብለዋል።

በዚህም “ እኔ የለኝም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉልበቴ ስለሆነ ለምኘ፣ እርዳታ አሰባስቤም እከፍላለሁ አልኳቸው። ለ5ኛ ጊዜ እንደገና #ፀጉሩን ላጭተው የሆነ #ውሻ አስመስለው ምስል ላኩልኝ። ከዚያ በኋላ በቃ ‘የጨመረሻ ቀን ብለው’ ደወሉ። ልጄም በጣም #እያለቀሰ ‘አስለቅቂኝ’ አለኝ። እነርሱም ‘ነገ #አርብ 1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን በፊት ለፊትሽ ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን ” አሉኝ ሲሉ አንብተዋል።

አጋቾቹ ‘ብር ላኪ’ ሲሏቸው ባለማወቅ የመፍትሄ መንገድ መስሏቸው የላኩትን አካውንት በሕግ እንዳሳገዱ፣ በዚህም አጋቾቹ የወጣቱን ስቃይ እንዳበዙት፣ ከታገተ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነው፣ ገንዘቡ እስኪሟላ ተጨማሪ ቀን መጠየቃቸውን የገለጹት እናት፤ “ ፌደራልም ሊቢያና ሱዳን ድንበር ላይ የሊቢያ መግቢያ ላይ ነው የታገተው ብለው ነገሩኝ ” ብለዋል።

ወ/ሮ ገነት፣ ምርመራውን ይዞታል የተባሉ የፌደራል ፓሊስ አባል የአጋቹን አካል ቢደርሱበትም በሕግ በኩልም መፍትሄ እንዳላገኙ አስረድተዋል።

ያላቸው አሁናዊ የምርመራ ሂደትን በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው መርማሪው የፌደራል ፓሊስ ጉዳዩን በጽሞና ከሰሙ በኋላ “ መልስ መሰጠት የሚችለው እንደ ተቋም ስለሆነ በተቋሙ በኩል ኦፊሻል ደብዳቤ ይዘው በአካል መጥተው አመራሮችን ማነጋገር ይችላሉ ” ከማለት ውጪ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ሆኖም ስለጉዳዩ በደብዳቤ ጠይቀን ምላሹን በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

እናት አጋቾቹ ከጠየቁት ውስጥ እስካሁን የተሰበሰበው ወደ 350 ሺሕ ብር ብቻ እንደሆነ አስረድተው “ ሀዘን ላይ ነኝ። በቅርቡ ልጄ ሞቶብኛል። አሁን ደግሞ ይሄ ደረሰልኝ ብዬ፣ አሁን እንደዚህ ሆነብኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ረድቶኝ ልጄን እንዲያስለቅቅልኝ በትህትና እጠይቃለሁ ” ሲሉ ተማጽነዋል።

ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ የወ/ሮ ገነት ጥላሁን ይግለጡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000523577402 ሲሆን ሌሎችም የሂሳብ ቁጥሮች ከላይ ተያይዟል።

በስልክ ልታገኟቸው የምትፈልጉ 0916848184፣ 0911720985 ደውሉላቸው።

@tikvahethiopia