TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አረንጓዴአሻራ
#ሐምሌ22እንገናኝ

ሐምሌ 22 ለሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር የከተማ አስተዳደሩ ባደረጋቸው ቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ የከንቲባ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክረቴሪያት ወ/ት ፌቨን ተሾመ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ወ/ት ፌቨን በመግለጫቸው ፦

✿ የቦታ ልየታን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ፤

✿ በከተማዋ ባሉ 116 ወረዳዎች ወጣቶችን በማሳተፍ 2.8 ሚሊየን ጉድጓድ ቁፋሮ መደረጉን ፤

✿ በዕለቱ 400 በላይ የመትከያ ሳይቶች መዘጋጀታቸውን ፤

✿ በከተማዋ ያሉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ የሚሳተፍበት ቦታ ተዘጋጅቷል ፤

✿ በዕለቱ 100ሺ የሚሆኑ ወጣቶች ዝግጅቱን ለማስተባበር መዘጋጀታቸውን ፤

✿ በዕለቱ የሚሰሩ ስራዎችን የሚመራ ግብረ ሃይል መቋቋሙን በመግለጫቸው ጠቅሰዋል፡፡

ስለዚህ በአራዳ ክ/ከተማ ፣ ልደታ ክ/ከተማ ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ እና አዲስ ከተማ ክ/ከተማ የመትከያ ሰፋፊ ቦታ የሌላቸው ወረዳዎች ላይ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከቅዳሜ ጠዋት ጀምሮ በወረዳቸው በመገኘት ችግኞችን በመውሰድ በጊቢያቸው እና በ20/50 ራድየስ መትከል ይችላሉ፡፡

በማስፋፍያ አከባቢ የሚኖሩ የከተማዋ ነዋሪዎች በየአከባቢዎቻቸው በተዘጋጁ የመትከያ ጣቢያዎች በመገኘት መትከል ይችላሉ፡፡

በዕለቱ የከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞች በሙሉ የችግኝ ተከላ ላይ ስለሚሳተፉ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ለአገልግሎት ዝግ ይሆናሉ፡፡

የከተማው ነዋሪ ለከተማው ያለውን ፍቅር እና በጎ አመለካከት ችግኝ በመትከል በተግባር እንዲገልፅ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የአ/አ ከተማ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴአሻራ

የፊታችን ሀምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 200 ሚሊዮች ችግኞችን በመላው ሀገሪቱ ለመትከል ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ሐምሌ 22 ቀን የሚደረገዉን ብሔራዊ የችግኝ ተከላ ቀን በተመለከተ ያስተላለፉት መልእክት👇
https://telegra.ph/PMO-07-26

#አረንጓዴአሻራ
#PMOEthiopia
#አረንጓዴአሻራ

የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ በከተማዋ ሁሉም ክፍሎች እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ጋር በመሆን የሺ ደበሌ አከባቢ ችግኝ ተክለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴአሻራ

የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በከተማዋ ሁሉም ክፍሎች በድምቀት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ ለረዥም ጊዜያት በከተማዋ የቆሻሻ መጣያ ሆኖ በቆየው በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ችግኝ ተክለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GreenLegacy in Wolayta Soddo

#አረንጓዴአሻራ በወላይታ ሶዶ

#PMOEthiopia
#ጎንደር

"የኃይሌ ሪዞርት-ጎንደር ማኔጀመንት እና ሰራተኞች በጎንደር ገነት ተራራ ላይ የ #አረንጓዴአሻራ ችግኝ ተከላ አካሂደናል!"