TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች " ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ፤ ድምፄን አሰማለሁ " በሚል በተለይም የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ሰልፍ ተደርጓል።

ሰልፉን የሞያ ማህበራት፣ የሲቪክ ማህበራት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደጠሩት ነው የተገለፀው።

በዚሁ ሰልፍ ላይ የሰልፉ ተሳታፊዎች፣ ህወሓት ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና የትግራይ ህዝብ አሁን ላለበት ችግር ምንጭ ነው ያሉ ሲሆን ለቀጠናው ዘለቂ ሰላም ህወሓት #ትጥቅ_መፍታት አለበት ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ሰልፈኞቹ " በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ሁለት የጦር ሰራዊት አይኖርም ፣ በሉዓላዊነታችን አንደራደርም ፣ በሰብዓዊ እርዳታ ስም ጣልቃ ገብነት ሊቆም ይገባል " ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሰልፉ ተካፋዮች ፤ " የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተጀመረው ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አሳፋሪ ድርጊት መፈፀሙን ተከትሎ ነው " ያሉ ሲሆን " ከዛ በኃላም ለሰላም የተሰጠውን ዕድል አልተጠቀመም አሁንም ቢሆን ለ4ኛ ዙር ጥቃት እንዲከፍት ዕድል መስጠት አይገባም። " ብለዋል።

ምዕራባውያንና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በእርዳታ ስም ሆነ በሌላ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና ለሰሜን ኢትዮጵያ ችግር ምንጭ የሆነውን " ህወሓት " ን መደገፍ ሊያቆሙ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
👍1.29K👎717🕊8845🙏44😢16😱9