TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
የፊታችን ሰኞ በደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግር ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።
ዛሬ የኢፌዴሪ ምክትል ጠ/ ሚ እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ አባላት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።
በዚሁ ማብራሪያ የኢትዮጵያ መንግስት የሰሜኑን ጦርነት በሰላም ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።
የመንግስት ልዑክ ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ በታሰበው የሰላም ውይይት ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠውላቸዋል።
ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅና የግዛት አንድነቷን ለማረጋገጥ በምትወስደው እርምጃ ላይ ግን የሚደረግን ማንኛውንም አይነት ጫና እንደማትቀበል አመልክተዋል።
በሌላ በኩል ፤ ህወሓት ሰኞ ጥምቅት 14 በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የሰላም ንግግር ላይ እንደሚሳተፍ አሳውቋል።
ህወሓት በደቡብ አፍሪካው የሰላም ንግግር ላይ " የኛም ልዑካን ይሳተፋሉ " ሲል ገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪ ፤ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ጸጥታ ም/ቤት የሰሜን ኢትዮጵያን ግጭት በሰላም ለመፍታት አፍሪካ ህብረት በሚመራው የሰላም ንግግር ዙሪያ ዛሬ ውይይት አድርጎ ነበር።
በውይይቱ የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ጸጥታ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዴዬ፣ በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ፣ የኢጋድ እና የኢትዮጵያ ተወካዮች ገለጻ አድርገዋል።
ሰኞ ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ/ም በደቡብ አፍሪካ የሚደረገው የሰላም ንግግር ከዚህ ቀደም በሎጅስቲክስ ዝግጅት ክፍተት ምክንያት የተራዘመው የሰላም ንግግር ሲሆን የሚመራው ደግሞ በአፍሪካ ህብረት አማካኝነት ነው።
@tikvahethiopia

#እንድታውቁት
ነገ በመስቀል አደባባይ፤ " ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ድምፄን አሰማለሁ " በሚል መሪ ቃል የድጋፍ ሰልፍ ይካሄዳል።
የድጋፍ ሰልፉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑት መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፦
- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከኤድናሞል በአትላሳ ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ ላይ
- ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ 4ኛ ክፍለጦር
- ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር ለሚመጡ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛ ላይ
- ከቡልጋሪያ በሜክሲኮ አደባባይ ወደለገሃር የሚሄዱ ለገሀር
- ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ እንዲሁም ከጦር ኃይሎች በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወደ ለገሃር የሚወስደው ሜክሲኮ አደባባይ
- ከተክለ ሃይማኖት በጎማ ቁጠባ ወደ ለገሃር ሰንጋተራ 40/60 ኮንደሚንየም አካባቢ
- ከጌጃ ሰፈር፣ በ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎማ ቁጠባ አካባቢ
- ከመርካቶ በተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሜትሮሎጂ በር ላይ
- ከራስ ቴአትር በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ መንገድ ላይ
- ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ ሼል አጠገብ
- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ለገሃር ቴዎድሮስ አደባባይ
- በአሮጌው ቄራ ፍል ውሃ ንግድ ማተሚያ ቤት አካባቢ
- ከካዛቺስ ወደ ሂልተን ካዛንቺስ ቶታል አካባቢ
- ከአዋሬ በካዛንቺስ ወደ ፍል ውሃ የሚወስደው መንገድ ፍል ውሃ አካባቢ #ከለሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይሆናል።
አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙና በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁመው መሄድ እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

#Telegram
ባለፉት ቀናት ከ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ሲገደብ የነበረው ቴሌግራም ዛሬ የ12ኛ ክፍል ፈተና መጠናቀቁን ተከትሎ ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል።
የ " ቴሌግራም " መገደብ ከፈተናው ጋር በተያያዘ የሀሰተኛ መረጃዎችን ስርጭት በመግታትና ተፈታኝ ተማሪዎች እና ወላጆች #እንዳይረበሹ በማድረግ በኩል ትልቅ የሆነ አስተዋጽኦ እንደነበረው መመልከት ተችሏል።
ባለፉት ዓመታት በነበሩ የብሄራዊ ፈተናዎች ላይ ከየትኛውም የማህበራዊ ሚዲያዎች በበለጠ በ " ቴሌግራም " በኩል ነበር የፈተና ወረቀቶች ከፈተና ቀን ቀደም ብሎ ሲሰራጭ የነበረው።
በአሁኑ የ2014 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ አስገብቶ ማስፈተኑ የፈተና ስርቆትን እና ቀድሞ ማሰራጨትን መከላከል ያስቻለ ሲሆን በአንዳንድ ተቋማት ስልክ ይዘው የገቡ ተማሪዎች ከፈተና ክፍል ሆነው የፈተና ወረቀት እያነሱ በቴሌግራም ግሩፖች እና ቻናሎች ላይ ሲያሰራጩ ነበር።
ነገር ግን በአብዛኛው ተማሪ ስልክ ይዞ እንዳይገባ በመደረጉ እና " ቴሌግራም " ም ሲገደብ ስለነበር ተፅእኖውን መቋቋም እንደተቻለ ይታመናል።
በቀጣዩ የ2015 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ላይ መሰል ክፍተቶች እንዳይኖሩ ለማድረግ ከአሁኑ ፈተና ትምህርት በመውሰድ አስፈላጊ ማስተካከያ ማድረግ ይገባል።

#USA አሜሪካ ትላንት ምሽት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒ ብሊንከን አማካኝነት በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዙሪያ መግለጫ አውጥታለች። በዚህ መግለጫ ምንድነው ያለችው ? - በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል " በሽሬ ዙሪያ " ግጭት እየጨመረ መምጣቱ፣ የሰው ህይወት እያለፈ መሆኑ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ያለየ ጥቃት እና ውድመት መከሰቱ በጣም ያሳስበናል ብላለች። - " የኢትዮጵያ…
#Update
ትላንት ለሊት አሜሪካ ሰኞ ሊደረግ ከታቀደው የሰላም ንግግር ጋር በተያያዘ መግለጫ አውጥታለች።
በዚህ መግለጫ በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ ክልል ባለስልጣናት መካከል በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሊደረግ የታቀደውን የሰላም ንግግር በደስታ እንደምትቀበለው ገልፃለች።
አሜሪካ ፤ " ደቡብ አፍሪካ ውይይቱን ስላስተናገደች እናደንቃለን " ያለች ሲሆን የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ እና የአፍሪካ ህብረት የፓናል አባላት ፑምዚሌ ምላምቦ-ንጉካ እና ኡሁሩ ኬንያታ ፤ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመስከረም ወር ላይ ለተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ጦርነቱ የሚያበቃበትን እና የህዝቡን ደህንነት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ስምምነት እንዲደረግ ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ ነን ስልት አሳውቃለች።
አሜሪካ የአፍሪካ ህብረት አጋር እንደመሆኗ መጠን በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ንቁ ተሳትፎዋን ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኗን ገልፃለች።
ለሰብዓዊ ድጋፍ ሲባል ለ5 ወር የዘለቀው ግጭት የማቆም ውሳኔ ነሃሴ ወር ላይ ከፈረሰ በኃላ የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ ፣ ውድመት ስለመድረሱ ፣ ሲቪሎችን ባለየ ሁኔታ የተፈፀሙ ድብደባዎች እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችን የሚመለከቱ ሪፖርቶች ያሳስቡኛል ብላለች።
አሜሪካ በትላንት መግለጫዋ ፤ ሁሉም ወገኖች በአስቸኳይ ግጭት እንዲያቆሙ ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ እና የኤርትራ መከላከያ የጋራ ወታደራዊ ኦፕሬሽን እንዲያቆሙና ሰላማዊ ሰዎችን እንዲጠብቁ በድጋሚ ጠይቃለሁ ብላለች።
በተጨማሪ #ኤርትራ ጦሯን ከሰሜን ኢትዮጵያ እንድታስወጣና ያልተቆራረጠ ሰብዓዊ ድጋፍ ለተቸገሩ ወገኖች ሁሉ መደረሱን እንዲቀጥል ጠይቃለች።

#UNSC
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት " የአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ " በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ትላንት መክሮ ነበር።
ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት A3 (ኬንያ፣ ጋቦንና ጋና) የነበሩ ሲሆን በዝግ ነው የተካሄደው።
የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ከስብሰባው በኃላ አንድ የጋራ መግለጫ ለማውጣት ሳይስማማ ቀርቷል።
ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አንድ የጋራ መግለጫ ማውጣት ሳይችል የቀረው ቻይና እና ሩስያ ባለመደገፋቸው ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች " ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ፤ ድምፄን አሰማለሁ " በሚል በተለይም የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ሰልፍ ተደርጓል።
ሰልፉን የሞያ ማህበራት፣ የሲቪክ ማህበራት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደጠሩት ነው የተገለፀው።
በዚሁ ሰልፍ ላይ የሰልፉ ተሳታፊዎች፣ ህወሓት ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና የትግራይ ህዝብ አሁን ላለበት ችግር ምንጭ ነው ያሉ ሲሆን ለቀጠናው ዘለቂ ሰላም ህወሓት #ትጥቅ_መፍታት አለበት ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሰልፈኞቹ " በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ሁለት የጦር ሰራዊት አይኖርም ፣ በሉዓላዊነታችን አንደራደርም ፣ በሰብዓዊ እርዳታ ስም ጣልቃ ገብነት ሊቆም ይገባል " ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የሰልፉ ተካፋዮች ፤ " የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተጀመረው ህወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አሳፋሪ ድርጊት መፈፀሙን ተከትሎ ነው " ያሉ ሲሆን " ከዛ በኃላም ለሰላም የተሰጠውን ዕድል አልተጠቀመም አሁንም ቢሆን ለ4ኛ ዙር ጥቃት እንዲከፍት ዕድል መስጠት አይገባም። " ብለዋል።
ምዕራባውያንና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በእርዳታ ስም ሆነ በሌላ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና ለሰሜን ኢትዮጵያ ችግር ምንጭ የሆነውን " ህወሓት " ን መደገፍ ሊያቆሙ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

#Malawi
ባለፈው ሳምንት " 25 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች " አስክሬን ያለበት የጅምላ መቃብር ምዚምባ በተባለ ግዛት ደን ውስጥ መገኘቱን የማላዊ ፖሊስ ገልጿል።
የአካባቢው ወጣቶች ደኑ ውስጥ የሚያውክ ሽታ እንዳለ መጠቆማቸውን ተከትሎ ነበር አስክሬኖቹ በቁፋሮ የተገኙት።
የጅምላ መቃብሩ ከተገኘ በኋላ በቅርብ ርቀት ሌላ የጅምላ መቃብር ተገኝቶ ተጨማሪ 4 አስክሬኖችን ፖሊስ አውጥቷል።
ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ፤ የማላዊ መንግሥት እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
የማላዊ የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስትር ጃን ሴንዴዝ ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ የተናገሩት፦
- በጣም የሚያሳዝን ነው። አስከፍቶናል። መንግሥታችን እንዲህ ያለ ድርጊት በጽኑ ያወግዛል። ትክክል አይደለም።
- ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ነው ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ እጃቸው ያለበት ሰዎች በቁጥጥር ሥር ይውላሉ።
- ኢትዮጵያውያኑ በምን ምክንያት እንደሞቱ ለማወቅ የአስክሬን ምርመራ ይደረጋል።
- የጅምላ መቃብሩ ከተገኘበት ጥበቅ ደን ርቆ በሚገኝ ሌላ ደን ውስጥ 72 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ተገኝተው በፖሊስ ተይዘዋል።
- ድንበር አቅራቢያና በአውራ ጎዳናዎች ላይ የሚያደርገው ቁጥጥር ጠብቋል። በሰሜናዊ የማላዊ ግዛት ሰው አዘዋዋሪዎችን ለመያዝ እየተሞከረ ይገኛል።
ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በማዘዋወር የተጠረጠሩ 10 የማላዊ ዜጎች መታሰራቸው የተነገረ ሲሆን እስከሁን ግን ፍ/ቤት አልቀረቡም ተብሏል።
አብዛኞቹ ማላዊ የሚገቡ ስደተኞች ከምሥራቅ አፍሪካ የሚነሱ ናቸው።
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ፤ኢትዮጵያ ከማላዊ መንግሥት ጋር በመተባበር ስለ ክስተቱ ምርመራ እያደረገች ነው ብለዋል። በክስተቱ ሐዘን እንደተሰማቸው ገልፀው የምርመራው ውጤት ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ሲሉ ገልፀዋል።

የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ቤተሰቦች ስለ አንፋጋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ምን አሉ ? ፍርድዮስ ዩሱፍ ለኤፍ ኤም 97.1 ሬድዮ የተናገሩት ፦ " ... አሊ በራ ሞተ ምናምን እያሉ በየጊዜ ያወጣሉ። ነገር ግን የትላንትናው በጣም እኛንም የጎዳ ያሳዘነን ነው። ከትላንት ወዲያ ነው ከሆስፒታል የወጣው ፤ በጤንነት ጥዋት ላይ ደግሞ የሚገርመው በእግሩ እኔ ሄዳለሁ አብራችሁኝ ሂዱ ብሎ በመኪና ይዘነው…
አንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት ክቡር ዶ/ር አሊ ቢራ #በህይወት አለ።
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አንጋፋው የሀገራችን አርቲስት ክቡር ዶክተር አሊ ቢራ " አረፈ / ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።
ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ባጋጠመው የጤና እክል የተነሳ በአዳማ ጄነራል ሆስፒታል ለላፉት ቀናት #የሕክምና_ክትትል እየተደረገለት ይገኛል።
የ75 ዓመቱ አርቲስት አሊ ቢራ ፤ ከዚህ ቀደምም የጤና እክል አጋጥሞት በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የውስጥ ደዌ ህክምና ተደርጎለት ነበር።
ከዚህ ቀደም ህክምና ላይ እያለ ህይወቱ እንዳለፈ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሀሰተኛ መረጃዎች ተሰራጭተው የነበረ ሲሆን በዚህ ሀሰተኛ መረጃ ቤተሰቦቹ እጅግ #መጎድታቸው እና #ማዘናቸውን መግለፃቸው ይታወሳል።
ሳናረጋግጥ የምናወራው ወሬ ምን ያህል የሰዎችን ህይወት እንደሚበጠብጥ እናውቀው ይሆን ? ሁሉ ነገር ስርዓት አለው ፤ የሰውን ሀዘን ለማርዳት ይሄን ያህል መቸኮል ምንድነው ? ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ወዳጅ ይደነግጣል አይባልም ? በችኮላ እና መረጃ አደረስኩ ለማለትና ለዩትዩብ ገንዘብ መሰብሰቢያ ሲባል ያልተረጋገጠ መረጃ ማሰራጨት ፍፁም ስርዓት የጎደለው ተግባር ነው።
#ውድ_ቤተሰቦቻችን ፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የምትመለከቱትን ሀሰተኛ መረጃ ከማጋራት ተቆጠቡ።

#USA #KENYA ትላንት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በስልክ ከጎረቤታችን ኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ጋር በተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮቻቸውና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን " ሲትዝን ቲቪ ኬንያ " ዘግቧል። እንደ ዘገባው ከሆነ ፤ ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ሲሆን የተወያዩባቸው #ዝርዝር_ጉዳዮች በይፋ አልተገለፀም። አሜሪካ ከሰሜን…
#Update
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጎረቤታችን ኬንያ ፕሬዜዳንት ዶክተር ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያዩ።
ውይይቱ ፤ በኢትዮጵያ እና በመላው ምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ኬንያ ስላላት ወሳኝ ሚና ላይ ያተኮረ እንደነበር የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።
ሚኒስትሩ ፤ በታህሳስ ወር ለማካሄድ ከታቀደው የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ዕቅዶች ዙሪያም ውይይት ማድረጋቸው ተመላክቷል።
በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ለሚገኘው ጦርነት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲገኝ አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ ማሳወቋ ይታወቃል።
ነገ ሰኞ / ጥቅምት 14 በደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ ህብረት መሪነት በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የሰላም ንግግር ለማድረግ ቀጠሮ መያዙ አይዘነጋም።

#EthiopianAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ካፒታሉን ወደ 300 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ማቅረቡን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
አየር መንገዱ አሁን ያለውን 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ለማሳደግ ያቀረበው ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ቦርድ ቀርቦ እየታየ ሲሆን ቦርዱ ተወያይቶ ውሳኔ ይሰጥበታል ተብል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ " አሁን ያለንን 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ማሳደግ የፈለግንበት ምክንያት፣ ወሮታችን ከፍ እያለ በመምጣቱ ሲሆን፣ በቅርቡ ያፀድቁልናል ብለን እናስባለን " ሲሉ ተናግረዋል።
የአየር መንገዱ የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ቦርድ ቀርቦ እየታየ እንደሚገኝ ጋዜጣው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፕ ማረጋገጡን አመልክቷል።
አቶ መስፍን የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄውን ምክንያት በተመለከተ፤ " የምናንቀሳቅሰው ገንዘብ እያደገ በመምጣቱና የካፒታል ማሻሻያ ከሌለ ትክክለኛ የፋይናንስ አያያዝ ለመፍጠር ስለሚያስቸግር " ነው ብለዋል።
" በተጨማሪም አሁንም አዳዲስ አውሮፕላኖች እያስመጣን ነው፡፡ በምናስመጣበት ወቅት የዕዳና ካፒታል ምጣኔ መመጣጠን አለበት፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የአውሮፕላን የሚገዛው በብድር ስለሆነ አበዳሪዎቹ ጋ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፍ ያለ የሀብት መጠን መድረስ አለበት። ብለዋል፡፡
የዕዳ እና ካፒታል ምጣኔ ተቋሙ ካለው ካፒታል አንፃር ሲታይ ምክንያታዊ ካልሆነ አበዳሪዎቹ ለማመን እንደሚቸገሩ አቶ መስፍን መግለፃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።