TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#OROMIA #PEACE " የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ... ለሰላም ክፍት ነን ድርድሮችም እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም ቢሆን ያሉ ችግሮች #በሰላም እንዲፈቱ መንግሥት #ለድርድር ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል። የክልሉ መንግሥት አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በአዲስ አበባ…
ኦነግ እና ኦፌኮ በውይይቱ ተገኝተው ነበር ?

#አልተገኙም

" ውይይት መደረጉን የሰማነው እራሱ በሚዲያ ነው " - ኦፌኮ

በኦሮሚያ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ከተባሉ ፓርቲዎች ጋር የክልሉ መንግሥት አድርጎታል በተባለው ውይይት ላይ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) #አልተሳተፉም

የኦፌኮ ዋና ፀሀፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ ለቪኦኤ ሬድዮ ፥ " ውይይቱ መደረጉን የሰማነው ከብዙሃን መገናኛ ነው። እንደ ግለሰብ ይሁን እንደ ተቋም የደረሰን ጥሪ የለም የኮሚኒኬሽን ክፍተቱ ከማን በኩል እንደሆነ አላውቅም " ብለዋል።

ኦፌኮ የክልሉ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ቢሆንም ባለው ቅሬታ ሙሉ ተሳትፎ እያደረገ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

አቶ ጥሩነህ ፤ ለውይይት በም/ቤት ይሁን በመንግስት ጥሪ አልደረሰንም ብለዋል።

የኦነግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ በበኩላቸው ፤ ፓርቲያቸው በውይይቱ #እንዳልተሳተፈ ገልጸዋል።

" ለውይይቱ ጥሪ ሊደረግ ይችላል እኛ ግን የምንፈልገው በአንድ አካል አቅራቢነት የሚደረገውን ውይይት ሳይሆን ሁሉም በእኩልነት የሚሳተፍበትን ውይይት ነው። " ብለዋል።

" የምንፈልገው አንድ ሀገርን የሚያስተዳደር መንግሥት በሚሰጥህ ቦታ ተወስኖ መወያየት ሳይሆን እራሳችንን የመፍትሄ አካል ነን ብለን የምናይ አካላት በአንድ ላይ ሆነን በተመሳሳይ ድምጽ ተወያይተን ዘላቂ መፍትሄ የምናስቀምጥበት ካልሆነ ኦነግ በአንድ አካል ጥሪ የሚሳተፍበት መድረክ አይኖርም " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሞን ችግር የሚፈተው በእውነታ ላይ የተሰመሰረተ አካታች ውይይት እንደሆነ የገለጹት አቶ ለሚ ፤ ውይይት ሂደቱን ጠብቆ አካታች በሆነ መልኩ መከናወን አለበት አሁን ያለው አካሄድ ሂደቱን ያልጠበቀ ቅንነት የሌለው በአንድ አካል ብቻ ተጎትቶ እየሄደ ያለ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ም/ቤት ሰብሳቢ እና የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት አቶ ሰለሞን ታፈሰ ኦነግ እና ኦፌኮ ከውይይት መቅረታቸውን አረጋግጠዋል።

" በድረገጻችን ላይ ለቀናል፣ በዋትስአፕ ላይ ተለቋል። እንደምንሄድ ኮሚቴው ሲወስን ተለቋል። በአካል አነጋሬያለሁ የሚመለከታቸውን ኦሮሚያ የኢትዮጵያ እምብርት ናት እናተ ስለሚመለከታችሁ ለምን አብረን አንሄድም? ብዬ ነግሬያቸዋለሁ። ተጋብዘዋልም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

#Ethiopia
#Oromia #VOA
#OFC #OLF

@tikvahethiopia