TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጠንቀቁ ⚠️ ከኦንላይ ዘራፊና አጭበርባሪዎች እራሳችሁን ጠብቁ። ነገሩ እንዲህ ነው ... ገንዘባቸውን ኦንላይን ተጭበርብረው የተበሉ ግለሰቦች መጀመሪያ በማያወቁት የውጭ ሀገር ስልክ ቁጥር በ #ዋትስአፕ / በ #ቴሌግራም መልዕክት ይደርሳቸዋል። ስልካቸውን / username እንዴት እንደሚያገኙት ባይታወቅም። የሚደርሳቸው መልዕክት " ጥሩ የስራ እድል እንደሆነ ፣ በትንሽ ስራም ብዙ ትርፍ እንደሚያገኙ…
#ScamAlert
በርካታ ሰዎች አሁንም በኦንላንይን #አጭበርባሪዎች ገንዘባቸውን የተጭበረበሩ ይገኛሉ።
ዛሬ እንዲሁም ትላንትና " #ተዘረፍን " ሲሉ መልዕክት የላኩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በዋስትስአፕ እና በቴሌግራም ያነገሯቸው ሰዎች ፤ " ቀለል ያለ ስራ ስሩና ትርፋማ ሁኑ " በማለት ከ150,000 ብር በላይ እንዲልኩላቸው ካደረጉ በኃላ ሰዎቹ የውሃ ሽታ ሆነዋል።
" በእኛ የደረሰ በናተ እንዳይደርስ ለማንም የማታውቁት ሰው መልዕክት አትመልሱ ፤ እንዲሁ ቁጭ ተብሎ ምንም ሳይደክሙ ብቻ ትርፋማ መሆን አይቻልምና ገንዘባችሁ እንዳትበሉ " ብለዋል።
በድጋሚ ማኛውም የማታውቁት ሰው በቴሌግራም ፣ ዋትስአፕ፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም ላይ " ትርፋማ ስራ እናሰራችሁ " ወይም ሌላም መልዕክት ሲልክላችሁ አትመልሱ።
ሌላው የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች የመገልገያ እቃዎችን " #በርካሽ እንሸጥላችኃለን ቅድሚያ የሂሳቡን ግማሽ ላኩ " ለሚሏችሁም ሰዎች መልስ አትስጧቸው / እቃውን ይላኩና ገንዘቡን ላኩላቸው።
አንድ የቤተሰባችን አባል " አዲሱን አይፎን 15 ስልክ ከአሜሪካ በርካሽ እንልክልሃለን ቅድሚያ ግን ግማሹን አስገባ " በማለት 50 ሺህ ብር ካስላኩት በኃላ አድራሻቸውን አጠፋፍተዋል።
ከዚህም ባለፈ ደግሞ ወደ ውጭ ሀገራት ለትምህርት ለስራ እንላካችሁ የሚሉም በዝተዋልና አድራሻሸውን ፣ ህጋዊናታቸውን አጣሩ። በቅድሚያ ምንም አይነት ክፍያ እንዳትከፍላቸው። " ቅድመ ክፍያ የለውም " ካሉም በኃላ በተለያየ መንገድ ጉዳይ መጨረሻ በሚል የሚበዘብዙ አሉና ተጠንቀቁ።
@tikvahethiopia