TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሀገር ስጋት⬇️

ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በአገር ደረጃ #ስጋት ሆኗል ተባለ፡፡ ከተለያዩ አገራት በድንበር በኩል የሚገባውን ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አስመልክቶ ጠንከር ያለ ሕጋዊ አሰራር ሊኖር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተናግሯል፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኢንዶክትሪኔሽንና ሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በከተማዋ በስፋት እየተስተዋለ ያለውን ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ለመግታት ጠንካራ የቁጥጥር ህግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

412 ሽጉጦችን፣ ከ12 ሺ በላይ የሽጉጥ ጥይቶችንና ከ9 ሺ በላይ የክላሽ ጥይቶችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የተገኙ 5 ተጠርጣሪዎችን ፍ/ቤት በዋስ መልቀቁ ጥብቅ የሆነ አሰራር ላለመኖሩ ማሳያ መሆኑን ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል፡፡

ከህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በተጨማሪ በጦር መሳሪያ የታገዘ ዘረፋና ቤት ሰብሮ ስርቆት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ እየተበራከተ መጥቷል ብለዋል፡፡

እነዚህን የወንጀል ድርጊቶች ለመከላከል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጥናት የተደገፈ የክትትልና የምርመራ ቡድን ማዋቀሩን ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ ህብረተሰቡን ከፍተኛ ጉዳት ላይ የሚጥሉና የአገርን ኢኮኖሚ የሚጎዱ የወንጀል ድርጊቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ተነግሯል፡፡

ነዋሪውም የከተማውን ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግ ለፀጥታ አካላት #ድጋፉን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia