#ETHIOPIA
በኤሌክትሪክ ሞተር ከሚሰሩት #በስተቀር የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች፣ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች እና የተገጣጠሙ ሞተር ሳይክሎችን ጨምሮ " ቅድሚያ የማይሰጣቸው " ተብለው የተለዩ 38 ዓይነት ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ እግድ ተጥሏል።
እግዱ መጣሉን ያሳወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው።
ይኸው እግድ የተላለፈው የህገወጥ የምንዛሬ ገበያውን ይበልጥ ለማውረድ በማሰብ መሆኑ ተገልጿል።
የእግዱ መተግበር በአማካኝ ግማሽ ያህል የውጭ ምንዛሬን ሊያስቀር ይችላል ተብሏል።
#ከሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው እገዳ የሚቆየው ላልተወሰነ ጊዜ ሲሆን እገዳ የተጣለባቸውን ምርቶች ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ መጠየቅ እንደማይቻል የብሄራዊ ባንክ አሳውቋል።
ወደ አገር እንዳይገቡ አገዳ የተጣለባቸው ምርቶች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA በኤሌክትሪክ ሞተር ከሚሰሩት #በስተቀር የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች፣ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች እና የተገጣጠሙ ሞተር ሳይክሎችን ጨምሮ " ቅድሚያ የማይሰጣቸው " ተብለው የተለዩ 38 ዓይነት ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ እግድ ተጥሏል። እግዱ መጣሉን ያሳወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው። ይኸው እግድ የተላለፈው የህገወጥ የምንዛሬ ገበያውን ይበልጥ ለማውረድ በማሰብ…
ከውጭ እንዳይገቡ እገዳ የተጣለባቸው ምርቶች ዝርዝር ፦
- ከረሜላዎች፣ ማስቲካዎችና ሌሎች ጣፋጭ ዝግጅቶች
- ቸኮሌት
- ብስኩቶች እና ዋፈሮች
- የፍራፍሬ ጭማቂዎች እና የታሸጉ ፍራፍሬዎች
- ከፍራፍሬ የተዘጋጁ ጃሞች፣ የድንች ጥብሶች ፣
- የታሸጉ ውሃዎች ለስላሳ መጠጦችና አልኮል የሌላቸው መጠጦች
- ውሰኪ፣ ወይን ቢራና ለሎች አልኮል መጠጦች በሙሉ
- ሲጋራ
- ሽቶዎችና ቶይሌት ዋተርስ
- የውበት ወይም የመኳኳያ ዝግጅቶች ፣
- ሳሙናዎች
- ርችቶች
- ቦርሳና ዋሌቶች
- ሳይክሎች
- በታሪፍ ቁጥር 9401 እስከ 9403 የሚመደቡ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች
- የገበታ ጨው
- የተለያዩ መጫወቻ እቃዎች
- የእጅ፣ የጠረጴዛና የግድግዳ ሰአቶች
- ዣንጥላዎች
- ምንጣፎች
- የአሳማ ስጋዎች
- የዶሮ ስጋዎች
- ቱናዎች፣ ሰርዲኖችና ሌሎች የአሳ ምርቶች
- ከህፃናት አልሚ ምግቦችና ወተቶች #በስተቀር የተለያዩ የታሸጉ ምግቦች
- ከሴራሚክስና ፖርስሊን የተዘጋጁ የቤት እቃዎች
- ጋዝ ላይተር
- የተለያዩ የጸጉር ጌጣጌጦች
- ልብስ ማሳያ አሻንጉሊቶች
- ከብርጭቆ የተዘጋጁ የመጠጥ መጠጫ እቃዎች፣ የስጋራ መተርኮሻዎች፣የአበባ መያዣና ተመሳሳይ እቃዎች
- የተታተመ ስዕላዊ መግለጫ ያላቸው ካርዶች፣
- የቀን መቁጠሪያ ካሌንደሮች፣
- ስዕሎች የግድግዳ ሥዕሎች ጨምሮ
- ባርኔጣዎችና ኮፍያዎች
- አርቲፊሻል አበባዎች
- የሰውና አርቴፊሻል ጸጉሮች ፣
- አርቴፊሻል ጌጣጌጦች
- የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢል ና ባለሶስት እግር ተሸከርካሪዎች /በኤሌክትሪክ ሞተር የሚሰሩትን ሳይጨምር/
- የተገጣጠሙ ሞተር ሳይክሎች /በኤሌክትሪክ ሞተር የሚሰሩትን ሳይጨምር/

" የባንክ ሂሳባቸው ታግዷል "
13 የ " ቤቲንግ " ሥራ ድርጅቶች እንዲሁም 109 አንቀሳቃሾቻቸው ከህብረተሰቡ የሚሰበስቡትን ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በመጠቀም በጥቁር ገበያ የውጭ ሀገር ምንዛሬ ግዢ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን በተደረገ ክትትል በመረጋገጡ የባንክ ሂሳባቸው እንዲታገድ ተደረገ።
ጉዳያቸውም በህግ እንደሚታይ ተገልጿል።
" ቤቲንግ " በሚል ስያሜ የሚታወቁትና የውርርድ ስራዎችን ላይ የተሰማሩት እነዚህ አካላት #የታክስ_ማጭበርበርን ጨምሮ በህገ-ወጥ የጥቁር ገበያ የውጭ ምንዛሬ ግዢ ወንጀል ድርጊት ላይ ተሳታፊ መሆናቸው #ተረጋግጧል ሲል የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል።
አገልግሎቱ የ13ቱን የቤቲንግ ስራ ድርጅቶች እና የ109 አንቀሳቃሾቻቸውን ስም ዝርዝር በይፋ አልገለፀም።
በእነዚህና በሌሎችም ዘርፎች በሚንቀሳቀሱ እና መሰል የወንጀል ተግባር ላይ በሚሳተፉ አካላት ላይ ቀጣይነት ያለው ክትትልና ህጋዊ የሆነ እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያስታወቀው የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ታሳታፊ እየሆኑ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethmagazine

#Update ለመጀመሪያ ጊዜ በፌዴራል ተቋማት / ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተሰጠ የሚገኘው የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የመጀመሪያው ዙር / የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ተጠናቋል። ከጥቅምት 5/2015 ዓ/ም ጀምሮ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መግባት ይጀምራሉ። ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ፤ የተማሪዎች ጉዳይ የሀገር ጉዳይ ስለሆነ ባለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችን ጉዳይ በንቃት…
#Update
ዛሬ እና ነገ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማእከላት / ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ።
ይህ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ጥብቅ በሆነ ህግ መሰጠት ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ ፈተናቸውን ጨርሰው የወጡት " የማህበራዊ ሳይንስ " ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የተመለከቱትን እና በቀጣዩ " የተፈጥሮ ሳይንስ " ፈተና ወቅት ሊስተካከለ ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አቅርበዋል።
ፈታኝ መምህራንም ሀሳባቸውን አጋርተዋል።
#ከማህበራዊ_ሳይንስ_ተፈታኞች ፦
- በባለፈው ፈተና ወቅት በአንዳንድ ተቋማት ውስጥ በምግብ አቅርቦት ጉዳይ ክፈትቶች የነበሩ ሲሆን ተማሪዎች በጊዜ ምግብ እንዲያገኙ እንዲሁም በግቢ ውስጥ ያሉት የአገልግሎት ሰጪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ሊያቀርቡ ይገባል። " የውሃ " አቅርቦትም ችግሮች የነበሩባቸው ተቋማት ነበሩ የሚገቡት ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያቸው እንደመሆኑን ለአምስት ቀን እንኳን ተማሪ ለማስተናገድ የሚሆን ውሃ ማቅረብ ይገባል።
- አንዳንድ ተቋማት ውስጥ ስርዓት የጎደላቸው ተፈታኝ ተማሪዎች በሌሎች ተማሪዎች ላይ ጫና ለማሳደር ሲሞክሩ ታይቷል ፤ በየዶርሙ እየዞሩ ምግብ አምጡ፣ ብር አምጡ ሲሉ የነበሩም ተማሪዎች የነበሩ ሲሆን በቀጣዩ የፈተና ወቅት እንዲህ አይነት ባህሪ ያላቸው ተፈታኞች ካጋጠሙ የሚመለከተው አካል ለሌሎች አስተማሪ የሆነ እርምጃ መውሰድ ያስፈልገዋል።
- በባለፈው ፈተና ወቅት በአንዳንድ ተቋማት ውስጥ ሌሎች ተማሪዎችን የሚረብሹ፣ የሚጮሁ ፣ በየዶርሙ እየሄዱ ተማሪ በተኛበት ሲያንኳኩ የነበሩ ተማሪዎች ነበሩ ፤ በተጨማሪ የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች " ፈተና ደርሷቸዋል " በሚል የተሳሳተ መረጃ ተማሪዎች ላይ ጫና ለማሳደር እና ለማስፈራራት የሞከሩ ነበሩና በዚህኛው ፈተና ሁሉም ተማሪ በቂ ገለፃ እና ከመሰል ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ማስገንዘብ ይገባል።
- ተፈታኝ ተማሪዎች ፤ ስለታም ነገሮች እና የተከለከሉ የሚጬሱ ነገሮችን ለምሳሌ እንደ ሲጋራ እንዳያስገቡ ፍተሻ ላይ የሚመደቡ የፀጥታ ኃይሎች ያለመሰልቸት ፍተሻ ማድረግ ይገባቸዋል። በግቢ ውስጥ ተማሪዎች ሲረብሹ ቢገኙ ደግሞ አጥፊዎችን ለይቶ ማስወጣት ይገባል እንጂ ሁሉም ተማሪዎች ላይ በጅምላ እምርጃ መውሰድ አይገባም።
- አንዳንድ ስነ ስርዓት የሌላቸው ተፈታኝ ተማሪዎች " ሴት ተማሪዎችን ለመተንኮስ " የሞከሩም ታይተዋልና የፀጥታ ኃይሎች ተማሪዎች ሳይጨነቁ እና ምንም ሳይፈሩ ፈተናቸውን እንዲወስዱ ማድረግ አለባቸው ፤ የላላ ቁጥጥር በተማሪዎች ውጤት ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖ ከባድ ነው።
- ከተማሪዎች ማደሪያ/ዶርም ጋር በተያያዘ ትክክለኛና ወጥ የሆነ አሰራር መዘርጋት ይኖርበታል። በአንዳንድ ተቋማት ተማሪዎች በተመደቡበት ሳይሆን እንደፈለጉ እየገቡ፣ ሌሎችን ተፈታኝ ተማሪዎች እየረበሹ የመኝታ ክፍል ለመያዝ ሲጥሩ ነበር። አንዳንድ ተማሪዎች " ተመድበንበታል " ብለው የሄዱበት ማደሪያ / ዶርም በሌሎች ተይዞ እንዳገኙ ገልፀዋል፤ በማደሪያ ክፍል ችግር የተንገላቱ ብዙ ናቸው። በቀጣይ ፈተና ወቅት ይህ ከማደሪያ ክፍል ጋር የተያያዘ ችግር መስተካከል ይኖርበታል።
- ምሽት ላይ የተማሪዎችን ደህንነት የማስጠበቅ ስራ መጠናከር አለበት፣ የሚረብሹ፣ የሚጮሁ ተማሪዎችን መቆጣጠር ይገባል። ከዚህ ባለፈ ከፍተሻ መሰላቸት ጋር በተያያዘ ሊሆን ይችላል ያልተፈቀዱ ነገሮች አልፈው ሲገቡ ታይተዋል ፤ ስልክም ደብቀው ይዘው የገቡም ነበሩና ጥብቅ የሆነ ፍተሻ እና ቁጥጥር ያስፈልጋል።
ማጠቃለያ ፦ የ2014 ተፈታኞቹ እንደመጀመሪያ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ቆያታቸውና በእንደህ አይነት መንገድ ለፈተና መቀመጣቸው አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርከታ እክሎች የነበሩ ቢሆን በቀጣይ ላለው ፈተና እንዲስተካከል ጠቁመዋል።
#ከፈታኝ_መምህራን ፦
- አንዳንድ ፈታኞች " ኩረጃን በሚያበረታታ " ድርጊት ሲፈፅሙ ነበር ፤ ይህ የትውልድ ጉዳይ ለመሆኑን ያለመሰላቸት የፈተናውን ሂደት መከታተል አለባቸው።
- ተማሪዎች ስልክ ይዘው ግቢ እንዳይገቡ የተደረገው ከውጭ በመደዋወል በሀሰተኛ ወሬ እንዳይረበሹ በማሰብ ነበር ነገር ግን አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፈታኝ በፈተነበት ተቋም ፀጥታ ለማስከበር የተሰማሩ አካላት ለተማሪዎች ስልክ ሲሰጡ ተመልክቷል። የፀጥታ ኃይሎች ግቢ ውስጥ ሬድዮ ብቻ ቢጠቀሙ እና ሞባይል ባይፈቀድ መልካም መሆኑን ጠቁሟል።
- አንድ የቤተሰባችን አባል የሆነ ፈተና ፈታኝ ተማሪዎች ለቀው ከወጡበት በአንዱ ተቋም እያስፈተነ የነበረ ሲሆን በፈተና ስርዓቱ ያጋጠሙ ችግሮችን በዝርዝር ገልጾልናል፡ ሱፐርቫይዘሮች እና የጣቢያ ኃላፊዎች ስራቸውን በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ እና በፈተና ክፍል ለሚስተዋሉ ችግሮች ፈጣን መፍትሄ ሊሰጡ ይገባል ብሏል።
- በፈተና ወቅት ለተፈታኞ የተሰጠው " የፈተና ሰዓት " በአግባቡ መቆጣጠር የሚገባ ሲሆን ቢቻል ቢቻል ፈተናው " ሙሉ በሙሉ " እስኪያልቅ የፈተናውን ወረቀት ይዘው እንዳይወጡ መከታተል ቢቻል ጥሩ ነው።
- "በቂ ዝግጅት" ያላደረጉ ተማሪዎች የኩረጃ መንገዱ ሁሉ ስለተዘጋባቸው የፈተናው ስርዓት እንዲረበሽ እና ፈተናው እንዲሰረዝ ለማድረግ ሲጥሩ ነበር። እነዚህ ተማሪዎች ዓለማቸውን ለማስፈፀም ሌላ አካባቢ " ፈተና ተሰረቋል " የሚል እና ሌሎችንም ያልተረጋገጡ ወሬዎችን ነው የሚያስወሩት።
በተጨማሪ ፦
• በአንዳንድ ተቋማት ውስጥ ተማሪዎች ፈታኞችን በግልፅ " እንድንኮራረጅ ካላስደረጋችሁን " ሲሉ ነበር ፤
• ፈታኝ የሚያክብሩ እንዳሉ ሁሉ ፈታኞችንና የፈተናውን ህግ የማያከብሩ ነበሩ፣
• አንዳንድ ተማሪዎች ለፈተና መምጣታቸውን በማወቅ መዘጋጀት ሲገባቸው በግቢ ውስጥ ጥንድ ጥንድ ሆነው ሲዟዟሩ/ሲዝናኑ ነበር ፣
• አንዳንድ ተማሪዎች " ፈተናውን አናልፍም " በሚል የጥያቄ ወረቀቱን ሳይከፍቱት የመልስ ወረቀቱን ዝም ብለው ሲሞሉ ነበር ፣
• ተማሪዎች " በጭንቀት " ብቻ ለህመም ስለሚጋለጡ ትምህርት ሚኒስቴር / ዩኒቨርሲቲዎች በተማሪዎች ስነልቦና ላይ ከፍተኛ ስራ ሊሰሩ ይገባል። ተማሪዎቹ ለፈተና ሊገቡ ሲሉ ፈተናውን በራሳቸው አቅም መስራት እንደሚችሉ ተስፋ ሊሰጣቸው ይገባል።
ማጠቃለያ ፦ ክፍተቶች በቶሎ ቢታረሙና መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች በፍጥነት ቢስተከከሉ ቀጣዩን ፈተና ካለፈው በመማር ስኬታማ ማድረግ ይቻላል።
#ለተፈጥሮ_ሳይንስ_ተማሪዎች ፦
ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሚናፈስ ምንም ያልተረጋገጠ እና ሀሰተኛ ወሬዎች ሳትረባሹ ቀደም ብለው ወደ ግቢ ገብተው ብሔራዊ ፈተናውን ከወሰዱት " የማህበራዊ ሳይንስ " ተፈታኝ ጓደኞቻችሁ ግቢውን ለመላመድ ይረዳቹ ዘንድ በቂ መረጃ በመጠየቅ ፣ የፈተና ህጎችን ሁሉ በማክበር ፈተናችሁን በስኬት ታጠናቅቁ ዘንድ እንመኛለን። መልካሙ ሁሉ ይግጠማችሁ ፤ መልካም ፈተና !
#ለማህበራዊ_ሚዲያ_ተጠቃሚዎች ፦
ዩኒቨርሲቲ ገብተው ፈተና የወሰዱት / በቀጣይ ቀናት የሚወስዱት ታዳጊዎች ለፈተና ስርዓቱ ብቻ ሳይሆን ለዩኒቨርሲቲ ዓለም አዲስ በመሆናቸው መደገፍ ፣ ማበረታታት እና በራሳቸውን እንዲተማመኑ ማድረግ ፣ እንጂ በሀሰተኛ እና ባልተረጋገጠ ወሬ እንዲረበሹ እና ይህን ገና ብዙ የሚሰሩበትን እድሜ የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ ማደርግ ፣ ተስፋቸው እንደጨለመ አድርጎ ወሬ መንዛት የአይገባም።
#TikvahFamily

#UN
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሃፊና የአስቸኳይ ድጋፍ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ በሽሬ ያሉ ሲቪሎች እና የሰብዓዊ እርዳታ ሰራተኞች ደህንነት ያሳስበኛል ብለዋል።
ግሪፊትስ ፤ በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን ገልፀው ፤ " ትላንት ሁለት የፊት መስመር ሰራተኞች መቁሰላቸውን ሰምቼ ደንግጫለሁ " ብለዋል።
" ጦርነቱ እነሱ ወዳሉበት እየቀረበ መሆኑን ተከትሎ ያደረባቸውን ጭንቀት እጋራለሁ " ያሉት ግሪፊትስ ፤ " ሁሉም ወገኖች ወደ ውይይት እንዲመጡ እስከዚያው ድረስ ግን ሲቪሎችን እና የረድኤት ሰራተኞችን እንዲጠብቁ በድጋሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ " ብለዋል።

#USA
አሜሪካ ትላንት ምሽት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒ ብሊንከን አማካኝነት በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዙሪያ መግለጫ አውጥታለች።
በዚህ መግለጫ ምንድነው ያለችው ?
- በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል " በሽሬ ዙሪያ " ግጭት እየጨመረ መምጣቱ፣ የሰው ህይወት እያለፈ መሆኑ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ያለየ ጥቃት እና ውድመት መከሰቱ በጣም ያሳስበናል ብላለች።
- " የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት በጋራ የሚያካሂዱትን ወታደራዊ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እና ኤርትራ ደግሞ ጦሯን ከሰሜን ኢትዮጵያ እንድታወጣ እንጠይቃለን " ብላለች።
- የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ከፀብ አጫሪነት ተግባራቸው እንዲታቀቡ አሳስባለች።
- ባለፈው ዓመት ነሃሴ ወር ላይ የትግራይ ክልል ኃይሎች በአማራ ክልል " ቆቦ " አቅራቢያ ያካሄዱት ዘመቻ ዳግም ግጭት እንዲቀሰቀስ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ይህም ለተጨማሪ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ግፎች ተጋላጭነት ከፍ እንዳደረገ ገልጻለች።
- ሁሉም የታጠቁ ኃይሎች ሲቪሎችን እንዲጠብቁ ፤ ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ያለ ምንም እንቅፋት ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደርስ እንዲያደርጉ ጠይቃለች።
- የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በአስቸኳይ ግጭት እንዲያቆሙ እና በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለሚካሄደው የሰላም ድርድር ላይ በቁም ነገር እንዲሳተፉ ደግመን ጥሪ እናቀርባለን ብላለች።
- አሜሪካ በተቻለ ፍጥነት የሰላም ንግግሮችን ለማደራጀት እና ለማሸማገል ከአፍሪካ ህብረት፣ ከኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ መንግስታት እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ አጋሮች ጋር ሙሉ በሙሉ እሰራለሁ ብላለች።

#TanaForum
ዛሬ በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር የጣና ፎረም መካሄድ ጀምሯል።
10ኛው የ " ጣና ፎረም " ጉባኤ በአፍሪካ የሰላም ፣ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ሲሆን እስከ ጥምቅት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
በባህር ዳር እየተካሄደ ባለው የጣና ፎረም ጉባኤ ላይ ፦
- የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፣
- የሶማሊያ ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ ፣
- የሱዳን የሉዓላዊ ም/ቤት ሊቀመንበር ፤ ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን እና ሌሎችም እየተካፈሉ ይገኛሉ።
ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ ፤ የጣና ፎረም አፍሪካውያን መሪዎችን እና ባለ ድርሻ አካላትን በአሕጉራዊ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በማወያየት ዘላቂ መፍትሔዎችን ለመቀየስ አልሞ ሚካሄድ ውይይት መሆኑን ገልፀው 10ኛው የጣና ፎረም ፤ " በአፍሪካውያን ለአፍሪካውያን የሚጠቅሙ መፍትሔዎች የሚወጡበት ውጤታማ የውይይት ጊዜ እንደሚሆንልን እምነቴ ነው " ብለዋል።
በሌላ በኩል ፤ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን የሽግግር መንግስት ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ከሆኑት ሌተናል ጀነራል አል ቡርሃን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል ፤ ከዚህ በተጨማሪ ዓባይ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ ያለውን ግዙፍ የድልድይ ግንባታ ስራ ጎብኝተዋል።
ፎቶ ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት

#Update ዛሬ እና ነገ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማእከላት / ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ። ይህ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ጥብቅ በሆነ ህግ መሰጠት ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ ፈተናቸውን ጨርሰው የወጡት " የማህበራዊ ሳይንስ " ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የተመለከቱትን እና በቀጣዩ " የተፈጥሮ ሳይንስ " ፈተና ወቅት ሊስተካከለ ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች በዝርዝር…
#NationalExam
የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባት ጀምረዋል።
ተማሪዎች ነገ ተጠቃለው የሚገቡ ሲሆን ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ (ኦሬንቴሽን) ይሰጣቸዋል።
ከጥቅምት 08 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ።
ከዚሁ ከሁለተኛ ዙር ፈተና ጋር በተያያዘ የባለፉት ክፍተቶች መታረም ያለባቸው ሲሆን፤ ትምህርት ሚኒስቴር ሴት ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ በቀን ሆነ በማታ ምንም አይነት ትንኮሳ እንዳይደርስ እና ፈተናውን ተረጋግተው እንዳይወስዱ የሚያደርጉ ጫናዎች እንዳይፈጠሩ እንዲሁም ምቾታቸውን ሆነ ደህንነታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል እንቅስቃሴ እንዳይኖር ጥብቅ ቁጥጥር ማደረግ ይኖርበታል።
የፀጥታ ኃይሎች የግቢ መውጫ እና መግቢያ ላይ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ዙርያ ገባው ላይ ቁጥጥራቸውን ማጠንከር እንዳለባቸው የከዚህ ቀደም ተፈታኝ ተማሪዎች ጠቁመዋል። (በአጥር የተከለከሉ ነገሮች እንዳይገቡ)
ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ የ2014 የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ ሁሉንም የፈተና ህጎችን በማክበር በመረጋጋት፣ በከፍተኛ የራስ መተማመን እንዲሁም በብሩህ ተስፋ ፈተናችሁን እንድትወስዱ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ደግሞ እነዚህ ታዳጊዎች አሁን ለተተገበረው የፈተና ስርዓት/ለዩኒቨርሲቲም አዲስ በመሆናቸው ማበረታታ እና መደገፍ እንጂ ባልተረጋገጠ መረጃ እንዲረበሹ፣ ተስፋ እንዲቆርጡ፣ በራሳቸውን እንዳይተማመኑ ማድረግ የለባችሁምና ስለምታጋሩት መልዕክት ጥንቃቄ አድርጉ እንላለን።
ተማፅኖ፦ ተፈታኝ ተማሪዎችን ወደ ፈተና ማዕከል በማጓጓዝ ላይ አሽከርካሪዎች በእርጋታ እና በጥንቃቄ ማሸከርከር እንዳትዘነጉ እንማፀናለን።
መልካም ፈተና!
Tikvah Family!