TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባት ጀምረዋል። ተማሪዎች ነገ ተጠቃለው የሚገቡ ሲሆን ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ (ኦሬንቴሽን) ይሰጣቸዋል። ከጥቅምት 08 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ። ከዚሁ ከሁለተኛ ዙር ፈተና ጋር በተያያዘ የባለፉት ክፍተቶች መታረም ያለባቸው ሲሆን፤ ትምህርት ሚኒስቴር  ሴት ተፈታኝ…
#ማስታወሻ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ " የፈተና ስርቆት እና ኩረጃ ከፍተኛ የደንብ ጥሰትና #ወንጀል " መሆኑን የሚገልፅ ሲሆን እንዲህ ያለው ድርጊት በህግ እንደሚያስጠይቅ ያስገነዝባል።

የማህበረሰብ የጋራ ሀብት በሆነው ፈተና ላይ ሚፈጸም ማንኛውንም አይነት ወንጀል በጋራ መከላከል ይገባል ይላል አገልግሎቱ።

የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የብሔራዊ ፈተና ከማክሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከ አርብ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TanaForum ዛሬ በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር የጣና ፎረም መካሄድ ጀምሯል። 10ኛው የ " ጣና ፎረም " ጉባኤ በአፍሪካ የሰላም ፣ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ሲሆን እስከ ጥምቅት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይቆያል። በባህር ዳር እየተካሄደ ባለው የጣና ፎረም ጉባኤ ላይ ፦ - የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን…
#TanaForum

በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የነበረው 10ኛው ጣና ፎረም ዛሬ ተጠናቋል።

ፎረሙ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም የተዘጋጀ ሲሆን ለ3 ቀናት ሲካሄድ ነበር።

በዛሬ መርሃ ግብር " የአፍሪካ የሰላምና ደህንነት ስነ ምህዳር እና ምላሾች" በሚል ርዕስ ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሂዶ ነበር በውይይት አፍሪካዊያን ምሁራን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ አምባሳደር አቴ ዌበር፣ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሀመር፣ የተመድ የአፍሪካ ቀንድ አምባሳደር ሀና ቴተህ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ተገኝተው ነበር።

በወቅቱም ኬኒያዊው የህግና ፖለቲካ ተንታኙ ፕ/ር ፓትሪክ ሉሙምባን ጨምሮ ሌሎች አፍሪካዊያን ምሁራን ለሐመር ጥያቄ አቅርበዋል።

ምሁራኑ ለአምባሳደር ሐመር ካቀረቧቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ አፍሪካ የራሷን ችግር በራሷ እንድትፈታ ለምን አትተዋትም? የሚል ሲሆን አሜሪካ በአፍሪካ የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ እየገባች ነው፤ ቻይና ለአፍሪካ ከአሜሪካ በተሻለ መንገድ እየሰራች ነው የሚሉና ሌሎች ጉዳዮችን አንስተዋል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር ፦

" አፍሪካ በራሷ ችግሯን መፍታት ትችላለች ?  እንደዛ ማድረግ የምትችል አይመስለኝም።

እኔ ባህርዳር የተገኘሁት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ለመንገር አይደለም። አፍሪካም ሆነች አሜሪካ ችግራቸውን ለመፍታት በጋራ መስራት ግን አለባቸው።

በአፍሪካ እንደ አሜሪካ ብዙ ገንዘብ ኢንቨስት ያደረገ ሀገር ወይም ተቋም የለም፣ የአፍሪካዊያንን ህይወት በመታደግ ከአሜሪካ በላይ የሰራ ሀገር የለም፣ ፍጹም ላንሆን እንችላለን።

አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለባትን ሀላፊነት ታውቃለች ነገር ግን በብዙ መንገድ ለአፍሪካ ድጋፍ እያደረግን እንገኛለን። " ሲሉ መልሰዋል።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TanaForum በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የነበረው 10ኛው ጣና ፎረም ዛሬ ተጠናቋል። ፎረሙ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም የተዘጋጀ ሲሆን ለ3 ቀናት ሲካሄድ ነበር። በዛሬ መርሃ ግብር " የአፍሪካ የሰላምና ደህንነት ስነ ምህዳር እና ምላሾች" በሚል ርዕስ ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሂዶ ነበር በውይይት አፍሪካዊያን ምሁራን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ አምባሳደር አቴ…
#TanaForum

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በጣና ፎረም የተናገሩት ፦

" ያለፈው ታሪካችን ሊያስተምረን ይገባል፤ ስለችግሮቻችን ማንንም አንወቅስም መውቀስ ካለብን ራሳችንን ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ በአክሱም ዘመን የነበረንን ስልጣኔ ተመልከቱ፤ በግብጽ የነበረንን የቀደመ ስልጣኔ አስቡ፤ ችግራችን የነበረንን ጥንታዊ ስልጣኔ እና ታሪክ በተገቢው መንገድ ለልጆቻችን አለማስተማራችን ነበር። አሁን ግን ለልጆቻችን ከማስተማራችን በፊት ስለራሳችን የተሳሳተውን እይታችን ማረም ይገባናል።

አዎ ! ላለፉት 40 እና 50 ዓመታት #አሜሪካ ለሀገሬ ኢትዮጵያ በመቶ ሚሊየኖች የሚቆጠር ዶላር አውጥታ ምግብ እረድታ ይሆናል፤ ነገር ግን አሜሪካ የረዳችን ከችግራችን በምንወጣበት መንገድ አልነበረም።

ግብርናችን እንዲሻሻል፣ ቴክኖሎጂ እንድንጠቀም እና የተሻሻለ አሰራርን እንድንተገብር ተደጋጋሚ ድጋፍ የጠየቅናት አሜሪካ በፖሊሲ ሰበብ ፈቃደኛ አልነበረችም።

ኢትዮጵያዊቷ ንግስት ሳባ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ተሻግራ እንደ ሀገር ንጉስ ሰለሞንን ስትጎበኝ አሜሪካ እንደ አህጉርም እንደ ሀገርም አትታወቅም ነበር።

ከኋላ እየመጡ ለሚቀድሙን ሁሉ እርግጥ ነው ኅላፊነቱን መውሰድ ያለብን ራሳችን ነን።

የጣና ፎረም መንፈስም ችግርን በግልፅ ተናግሮ በጋራ እና በትብብር መፍትሔ መፈለግ ነው። "

Credit : AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባት ጀምረዋል። ተማሪዎች ነገ ተጠቃለው የሚገቡ ሲሆን ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ (ኦሬንቴሽን) ይሰጣቸዋል። ከጥቅምት 08 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ። ከዚሁ ከሁለተኛ ዙር ፈተና ጋር በተያያዘ የባለፉት ክፍተቶች መታረም ያለባቸው ሲሆን፤ ትምህርት ሚኒስቴር  ሴት ተፈታኝ…
#Update

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባታቸውን ማምሻውን አሳውቋል።

አገልግሎቱ ተማሪዎቹ ነገ በ7/02/ 2015 ገለጻ እንደሚደረግላቸው እና 08-11/02/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልጿል።

" በራስ ጥረት፣ በብርቱ ድካምና በፈጣሪ እርዳታ የሚገኝ ውጤት መጨረሻው ያማረ ነው። " ያለው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት " የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለመጀመሪያ ጊዜ በፌዴራል ተቋማት / ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተሰጠ የሚገኘው የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የመጀመሪያው ዙር / የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ተጠናቋል። ከጥቅምት 5/2015 ዓ/ም ጀምሮ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መግባት ይጀምራሉ። ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ፤ የተማሪዎች ጉዳይ የሀገር ጉዳይ ስለሆነ ባለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችን ጉዳይ በንቃት…
#Telegram

በኢትዮጵያ #የቴሌግራም አገልግሎት እንዲገደብ ተደርጓል። አገልግሎቱ ከእኩለ ቀን አንስቶ ነው የተገደበው።

እስካሁን በጉዳዩ ላይ በሚመለከታቸው አካላት ማብራሪያ ባይሰጥም ከዚህ ቀደም እንደታየው የቴሌግራም መገደብ ነገ ከሚጀምረው "የተፈጥሮ ሳይንስ" የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል።

ባለፈው ሳምንት የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን በሚወስዱበት ቀናት/ወደ ክፍል ገብተው ፈተናቸውን በሚወስዱበት ሰዓት / ፈተናውን ጨርሰው እስኪወጡ ድረስ የቴሌግራም አገልግሎት እንዲገደብ ሲደረግ ነበር።

" በማህበራዊ ሳይንስ " የፈተና ወቅት ተማሪዎች ከፈተና ክፍል ሲወጡ ቴሌግራም ወደ አገልግሎት ሲመለስ የነበረ ሲሆን አሁኑ ላይ ግን ከፈተና አንድ ቀን ቀደም ብሎ አገልግሎቱ ተገድቧል።

የቴሌግራም አገልግሎት በኢትዮጵያ ባሉት ሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እንደማይሰራ ማረጋገጥ ችለናል።

ምንም እንኳን " የቴሌግራም " አገልግሎት ቢገደብም ሌሎች እንደ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ትዊተር የመሳሰሉ መተግበሪያዎች ያለ ገደብ እየሰሩ ናቸው።

የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ወቅት ወደ መፈተኛ ማዕከላት (ዩኒቨርሲቲ) ተማሪዎች ይዘው እንዳይገቡ በጥብቅ የተከለከለውን ስልክ ይዘው የገቡ ተፈታኞች ፈተናው እየተሰጠ ከመፈተኛ ክፍል እና ፈተና ሲጠናቀቅ ከማደሪያቸው የፈተና ወረቀቶችን በቴሌግራም ግሩፖች እና ቻናሎች ላይ ሲያሰራጩ ነበር።

በዚህም አንዳንድ ሰዎች " የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተሰርቋል " የሚሉ መረጃዎችን ቢያሰራጩም ፈተናው መሰጠት ከጀመረበት ሰዓት በፊት ቀድሞ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለመሰራጨቱ የሚያሳይ ማስረጃዎች ማግኘት አልተቻለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባታቸውን ማምሻውን አሳውቋል። አገልግሎቱ ተማሪዎቹ ነገ በ7/02/ 2015 ገለጻ እንደሚደረግላቸው እና 08-11/02/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልጿል። " በራስ ጥረት፣ በብርቱ ድካምና በፈጣሪ እርዳታ የሚገኝ ውጤት መጨረሻው ያማረ ነው። " ያለው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት "…
#Update

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ፈተናው እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ መሰጠት ይቀጥላል።

በሌላ በኩል ከትላንት ሰኞ ከእኩለ ቀን አንስቶ የተገደበው የቴሌግራም አገልግሎት ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት ሙሉ አገልግሎት እየሰጠ ነው።

ቴሌግራም ኢትዮጵያ ባሉት በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል።

የቴሌግራም መገደብን በተመለከተ ማብራሪያ የሚሰጠን አካል ባይኖርም ከዚህ ቀደም በነበሩት የብሔራዊ ፈተና ቀናት / በባለፈው የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ወቅትም (ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ፈተናቸውን እስኪፈተኑ ድረስ) ሲገደብ ነበር።

@tikvahethiopia
#ከሰሞኑን - ሰሜን ኢትዮጵያ !

ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት ከኢፌድሪ መንግስት ፣ ከአሜሪካ መንግስት ፣ ከተመድ ፣ ከአውሮፓ ህብረት እንዲሁም ከአፍሪካ ህብረት የተሰጡ መግለጫዎች እና ወቅታዊ መረጃዎች ፦

➦ አሜሪካ ባወጣችው መግለጫ ፤ በባለፈው ዓመት ነሃሴ ወር አጋማሽ ላይ " ህወሓት / TPLF " በአማራ ክልል በ " ቆቦ " አካባቢ ዘመቻ ማካሄዱንና በዚህም ጦርነቱ #ዳግም_ለመቀስቀሱ አስተዋፆ ማድረጉን ይህን ተከትሎ ተጨማሪ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ግፎች ተጋላጭነት ከፍ እንዳደረገ ገልፃለች። አሜሪካ የኢትዮጵያ መከላከያ እና የኤርትራ መከላከያ በጋራ የሚያካሂዱትን ወታደራዊ ጥቃት እንዲያቆሙ እና ኤርትራ ጦሯን ከ " ሰሜን ኢትዮጵያ " እንድታስወጣም ጥይቃለች።

                           --------------------

➦ የአፍሪካ ህብረት ( #AU ) ኮሚሽን ሊቀ መንበር ፤ ሙሳ ፋኪ በሰሜን ኢትዮጵያ ውጊያ ውስጥ ያሉ አካላት " ያለምንም ቅድመ ሁኔታ " የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ አሳስበው የሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎቶች ወደ ነበሩበት አንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት በደቡብ አፍሪካ ወደ ተጠራው " የሰላም ድርድር " እንዲመጡ ፋኪ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

                          --------------------

➦ የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፤ " በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ ነው። " ሲሉ ተናግረው ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

" አሁን በኢትዮጵያ ባለው ሁኔታ የማህበራዊ ትስስር እየተበጣጠ ነው ፤ የሲቪሎች ህይወት እየቀጠፈና ውድመት እያስከተለ ያለው ጦርነት ማብቃት አለበት ብለዋል።

" የኤርትራ ኃይሎች ከኢትዮጵያ መውጣት አለባቸው " ያለቱ ጉተሬዝ በትግራይ ክልል ያለው ግጭት አሁኑኑ ማብቃት አለበት ብለዋል።  አሁን በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ወታደራዊ መፍትሄ የለውም ሲሉ ተናግረዋል።

ጦርነቱ እንዲያበቃ ተመድ (UN) የአፍሪካ ህብረትን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑ አረጋግጠው " ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሁን ለሰላም መሰባሰብ አለበት ። " ብለዋል።

በተመሳሳይ የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከኤርትራ ሰራዊት ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል እያካሄዱት ያለውን  የጋራ ጥቃት እንዲያቆሙ ጠይቋል ፤  የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ሙሉ በሙሉ ለቀው እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

ህብረቱ ህወሓት በአማራ እና አፋር አጎራባች ክልሎች ያለውን ጦርነት እንዲያቆሙና ከወታደራዊ ዘመቻ እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

                        --------------------

➦ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ " በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከቁጥጥር ውጪ የወጣ ነገር የለም፤ ሁሉም ነገር በታቀደው መሰረት እየሄደ ነው " ብለዋል።

መንግስት የአፍሪካ ሕብረት ( #AU ) የሰላም ውይይቱ የሚካሄድበትን ቀን እስኪያሳውቅ በመጠባበቅ ላይ ይገኛልም ብለዋል።

" አንዳንዶች በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት ከቁጥጥር ውጪ ሆኗል በሚል እየተጠቀሙበት ያለው አገላለጽ ከእውነት የራቀ ነው " ሲሉ  ገልፀዋል።

" ግጭቱ ወደ አማራና አፋር ክልሎች ተስፋፍቶ ነበር አሁን ያ ነገር የለም፤ የመከላከል እርምጃው በታሰበው መልኩ እየሄደ ይገኛል " ያሉ ሲሆን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትና #መሰረታዊ_አገልግሎት እንደሚጀመር አሳውቀዋል።

                        --------------------

➦ ዛሬ ጥቅምት 8 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት ባወጣው መግለጫ የመከላከያ ሠራዊት በከተሞች ውስጥ ምንም ዓይነት ጦርነት ሳያካሂድ ፦
- ሽሬ፣ 
- አላማጣ
- ኮረም ከተሞችን እንደተቆጣጠረ ገልጿል።

በመግለጫው ላይ ፤ " የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተከተለው ጥብቅ ወታደራዊ ዲሲፕሊን፣ የሕወሐትን ፕሮፓጋንዳ ሲያስተጋቡ የነበሩ አካላትን ሟርት ያመከነ ነው። " ሲልም ገልጿል።

ከልዩ ልዩ የርዳታ ድርጅቶች ጋር በመሆን መከላከያ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ላይ ርዳታ እንዲደርስ በቂ ዝግጅት መደረጉን የገለፀው መንግስት እርዳታ የማድረሱ ስራ የሽሬ አውሮፕላን ማረፊያን መጠቀምን እንደሚጨምር ገልጿል።

በተጨማሪ በሰሜን ጎንደር ወደ ሽሬ የሚወስደውን እና ከኮምቦልቻ - ደሴ- ወልድያ- ቆቦ- አላማጣ ያለውን መንገድ ለመክፈት እየሠራ መሆኑም አሳውቆ ይሄንን ሥራ የሚያሣልጥ ኮሚቴ ከሚመለከታቸው አካላት ተወጣጥቶ ሥራ ጀምሯል ብሏል።

እነዚህ ሥራዎች ቴክኒካዊ የሆኑ ጥናቶችን እና ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች አገልግሎቶችን ለማስጀመር የሚያስችሉ መሠረታዊ ሥራዎችን ይጨምራል ሲልም አሳውቋል።

                             --------------------

➦ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ህወሓት ለ3ኛ ተከታታይ ጊዜ " ጦርነቱን ሆን ብሎ " በመቀስቀሱ ​​በሰሜን ኢትዮጵያ ላለው ወቅታዊ ሁኔታ ብቸኛ ተጠያቂ ነው ያለ ሲሆን ህወሓት ጊዜ እና ቦታ ከተሰጠው ይህን እንደገና ያደርጋል ብሏል።

በሌላ በኩል መንግስት ከ " ህወሓት " ነፃ ባወጣቸው እና በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ላይ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ ከድጋፍ ከሚያደርጉ አካላት ጋር አብሮ እንደሚሰራ እና የሰብዓዊ ድጋፍ ሰራተኞችን ደህንነት እንደሚያረጋግጥ አሳውቋል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት ፣ የአፍሪካ ህብረት ትዊተር ገፅ ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድረገፅ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የመንግስት ኮሚኒኬሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION ወልድያ ! የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ም/ቤት ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ ተጨማሪ ክልክለዎችን አስተላለፈ። የፀጥታ ምክር ቤቱ ከዚህ ቀደም የከተማውን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ  ክልከላዎችን ማስቀመጡ ይታወሳል። ሆኖም ነባራዊ ሁኔታ በማየት ተጨማሪ ክልከላዎች በማስፈለጉ ከነገ መስከረም 22 / 2015 ዓ.ም ጀምሮ  የሚተገበሩ ተጨማሪ ዉሳኔዎችን ማሳለፉን ገልጿል። …
በወልድያ ያልተነሱ ክልከላዎች ምንድናቸው ?

የወልዲያ ከተማን አሁናዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ከዚህ ቀደም ተላልፈው የነበሩ በርከት ያሉ ክልከላዎች ተነስተዋል።

የወልድያ ከተማ የፀጥታ ም/ቤት አስቀምጧቸው ከነበሩ ውሳኔዎች ከ3ቱ ውጭ ያሉትን ውሳኔዎችን ማንሳቱን አስታውቋል።

ምክር ቤቱ ከዛሬ ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከጦር መሳሪያ አያያዝ፣ ከሰራዊት ልብስ አጠቃቀም፣ የስአት እላፊ ገደብ ውጭ ሌሎቹን ውሳኔዎች ማንሳቱን አሳታውቋል።

ያልተነሱና ባሉበት የሚቀጥሉት ውሳኔዎች :-

1. ከፀጥታ መዋቅሩ ውጭ በከተማው በየትኛውም ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በፍጹም የተከለከለ ነው፡፡

2. ከተፈቀደላቸው የመንግስት የፀጥታ አባላት ውጭ የሰራዊቱን አልባሳትን መልበስ የተከለከለ ነው፡፡

3. ለእግረኛ የቀመጠው 4 ስዓት የስአት እለፊ ገደብ እና ለተሽከርካሪ የተቀመጠው 3 ስዓት ገደብ ባሉበት ይቀጥላሉ።

ከወልድያ በተጨማሪ ፤ ካለፈው ወር መጨረሻ አንስቶ በደሴ ከተማ የሰዓት ገደቦች ሙሉ በሙሉ ተነስተዋል።

በደሴ ከተማ ስምሪት ያላቸው ተሽከርካሪዎች ብቻ የሚመለከት ሆኖ ባጃጅ ፣ ታክሲዎች እና ሌሎችም ተሽከርካሪዎች በሰላም ወቅት እንደተለመደው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ተደርጓል።

@tikvahethiopia
ታላቁ ዓሊም አረፉ።

ታላቁ ዓሊም ሸይኹል መሻይኽ ሙፍቲ ሸይኽ አደም ቱላ ማረፋቸው ተሰምቷል።

ሸይኽ አደም ቱላ በህይወት ዘመናቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ታላላቅ አሊሞችን እና ደረሶችን ማፍራት የቻሉ ሲሆን በ1966 ጀምሮ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት (መጅሊስ) እንዲመሰረተ በተደረገው ጥረትና በመመስረት ትልቅ ድርሻ የነበራቸው አባት እንደነበሩ ተገልጿል።

ከታላቁ ዓሊም ሼይኽ አደም ቱላ እረፍት ጋር በተያያዘ ማምሻውን የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ  መንግስት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ፦ - ኢትዮጵያዊያን በግለሰብ ደረጃ ከ100 ሺህ ብር በላይ ለድርጅቶች ደግሞ ከ200 ሺህ ብር በላይ ቤት ውስጥ ማስቀመጥ የተከለከለ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸወል። - ገንዘብ በባንክ መቀመጥ አለበት ፤ የግብይት ስርዓትም በባንክ ማካሄድ ይቻላል። - መመሪያው ከሚፈቅደው የገንዘብ መጠን በላይ አስቀምጦ የተገኘን አካል #የጠቆመ ግለሰብ 15 በመቶ የወረታ ክፍያ…
በምን ልጠቁም ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕገ ወጥ የሆነ የገንዘብ ዝውውርን ለሚጠቁሙ ወሮታ የሚከፈልበትን መመሪያ በተመለከተ ዛሬ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

በቅርቡ ብሄራዊ ባንክ 4 ህገወጥ ጉዳዮች ላይ ህብረተሰቡ ጥቆማ እንዲያደርግ እና ጥቆማውን ለሚያደርጉ ዜጎች #ወሮታ እንደሚከፍል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1. ከተፈቀደ በላይ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ገንዘብ ማከማቸት፤

2. ሀሰተኛ የገንዘብ ህትመት መፈፀም፤

3. የወርቅ ክምችት፤

4. ገንዘብ ህገወጥ በሆነ መንገድ ያለፈቃድ ማስተላለፍ በሚፈፅሙ ግለሰቦች ላይ ዜጎች ጥቆማ እንዲሰጡ እና ዜጎች ለሚሰጡት ጥቆማ ወሮታ እንደሚከፈላቸው ገልጾ ነበር።

- በባንክ ከተፈቀደው በላይ የገንዘብ መጠን ይዘው የሚገኙ ግለሰቦችን ለጠቆሙ ከተያዘው ገንዘብ 15 በመቶ፣
- የውጭ ሀገር ገንዘብ ዝውውር ለሚጠቁሙ 15 በመቶ፣
- ሕገወጥ ሐዋላን ለሚጠቁሙ 25 ሺህ ብር ወሮታ ይከፈላቸዋል።

ለግለሰቦች በቀን ከ100 ሺህ ብር በላይ መያዝ፣ ለተቋማትም በቀን ከ200 ሺህ ብር በላይ መያዝ የተከለከለ ነው።

ይህን መመሪያ የተላለፈን ግለሰብ ወይም ተቋም ለጠቆመ #ምስጢራዊነቱን በተጠበቀ መልኩ ወሮታው ተፈጻሚ እንደሚሆን ተገልጿል።

ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ግለሰብ በከባድ የኢኮኖሚ ወንጀል እስከ 15 ዓመት ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ ነው የተመላከተው።

ጠቋሚዎች በስልክ ቁጥር 0118133960፣ በኢ.ሜል አድራሻ [email protected]፣ በፋክስ ቁጥር 0115514366 እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፖ.ሣ.ቁጥር 5550 ላይ ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU በአፍሪካ ህብረት (AU) መሪነት በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የሰላም ንግግር በሎጅስቲክስ ምክንያት መራዘሙን ሮይተርስ የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የዲፕሎማቲክ ምንጭ ቀጠሮ የተያዘለት የሰላም ንግግር መራዘሙ ከሎጂስቲክስ ዝግጅት ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልጸው እስካሁን አዲስ ቀን እንዳልተቆረጠ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት በአፍሪካ…
#PeaceTalks

ተራዝሞ የነበረው የሰላም ንግግር ከ4 ቀናት በኃላ በደቡብ አፍሪካ ለማድረግ ቀን እንደተቆረጠለት ተሰምቷል።

በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሊደረግ የነበረውና በሎጅስቲክስ ዝግጅት ምክንያት ተራዝሞ የነበረው የሰላም ንግግር ከዛሬ 4 ቀናት በኃላ (ሰኞ ጥቅምት 14/2015 ዓ/ም) በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ መሆኑ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚር የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የአፍሪካ ህብረት በደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግሩን  ለማድረግ ለጥቅምት 14/2015 ዓ/ም ቀን መቁረጡን ገልጸዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ፤ " በዚሁ የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆናችንን በድጋሚ አረጋግጠናል " ብለዋል። " ነገር ግን መንግስት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚወስደውን የመከላከል ርምጃ ለማጠልሸት የሃሰት ከስን ለመሰንዘርና የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ በሚጥሩ አካካት ላይ ያለውን ቅሬታ ይገልፃል።" ሲሉ አክለዋል።

አፍሪካ ህብረት በህብረቱ የሚመራና በደቡብ አፍሪካ ለሚደረግ የሰላም ንግግር ለኢትዮጵያ መንግስት እና ለህወሓት ግብዣ አቅርቦ እንደነበርና በሁለቱም በኩል ግብዣው ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል።

የሰላም ንግግሩ ፤ በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይና የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በቀድሞ የደ/አፍሪካ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ-ናግኩካ እንደሚመራም መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia