TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የሁለተኛ ቀን የፈተና መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል። ይኸው የፈተና መርሀ ግብር ዛሬ ከሰዓት በኃላም ይቀጥላል። እንደ ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና መርሀግብር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ነገ ጥቅምት 2 / 2015 የሚጠናቀቅ ሲሆን ተማሪዎች ከጥቅምት 3 እስከ ጥቅምት 4 ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ። በሌላ በኩል ፤ ትላንት…
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች #የመጨረሻ ቀን የፈተና መርሀ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ዛሬ ፈተናቸውን የሚያጠናቅቁት ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ወደየመጡበት አካባቢ የሚደረጉ ይሆናል።

የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች እንዲሰጥ ከመደረጉ በላይ አንዳንድ ተቋማት ኩረጃን ለመከላከል ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ የደህንነት ካሜራዎችን ሲጠቀሙ እንደነበር ለማውቅ ተችሏል።

የደህንነት ካሜራዎችን ተማሪዎች በግቢ ውስጥ ያላቸውን እንቅስቃሴ እና በፈተና ክፍል ያለው የፈተና ስርዓት ለመከታተል ነው ጥቅም ላይ እያዋሉ ያሉት።

ዘንድሮ ከታዩ በጎ በጎ ጅምሮች በተጨማሪ እንደ መጀመሪያ ጊዜም ስለሆነ #ክፍተቶች የነበሩ ሲሆን እነዚህን በቀጣይ የምናነሳቸው ይሆናል።

ትምህርት ሚኒስቴርም ፈተና እንዳለቀ አጠቃላይ የነበሩ አፈፃፀሞችን ላይ መግለጫ እንደሚሰጥ ተነግሮናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናቸውን እንዳይፈተኑ እና ጥለው እንዲወጡ የሚያበረታቱ የተለያዩ አክቲቪስት ነን የሚሉ አካላት ፣ የማህበራዊ ትስስር ገፆች መኖራቸውን ተመልክተናል።

የተማሪዎችን ህይወትን የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ ለማድረግ የሞከሩም ብዙ ናቸው ፤ ድርጊቱ በነገ የሀገር ተረካቢ ልጆች ላይ ትልቅ ተፅእኖ ስላለው ቢታታረም መልካም ነው።

ገና ፈተናቸውን ያልወሰዱና ወደ መፈተኛ ተቋማት የሚገቡ በርካታ ተማሪዎች በመኖራቸው ያሉ ክፍተቶች እንዲታረሙ ለማደረግ መረባረብ እንጂ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ተማሪዎችን መረበሽ ፍፁም ተገቢ አይደለም።

ፎቶ ፦ አርሲ ዩኒቨርሲቲ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና " የማህበራዊ ሳይንስ " የሁለተኛ ቀን የፈተና መርሀግብር ዛሬ ሲካሄድ ውሏል። በነገው ዕለት የመጨረሻው ቀን የፈተናው መርሃ ግብር ተካሂዶ ቀድሞ በወጣው መርሀ ግብር ተማሪዎች ከነገ በስቲያ ጀምሮ ወደ የመጡበት እንዲመለሱ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። ከዛሬው የፈተና ውሎ ጋር በተያያዘ በተለይም በደብረ ማርቆስ እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች  አንዳንድ ተማሪዎች…
" ተማሪዎቹ ከተሳሳተ ውሳኔያቸው እንዲመለሱና ወርቃማ ዕድላቸውን እንዲጠቀሙ የተቻለንን አድርገናል " - ዶክተር የህይስ አረጉ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር የህይስ አረጉ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አንፈተንም ብለው ማዕከሉን ለወቀው በወጡ ተማሪዎች ጉዳይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዶ/ር የህይስ ፤ " በጤና ካምፓስ " የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል የተወሰኑ ተማሪዎች ፈተና ከበደን ወይም ቁጥጥር በዛብን በሚል ሰበብ ፈተና አቋርጠዉ ወጥተዋል ብለዋል።

አብዛኞቹ ተማሪዎች ግን ፈተናቸዉን በሰላም በመዉሰድ ላይ ይገኛሉ ሲሉ ገልፀዋል።

" ፈተና ጥለዉ የወጡ ተማሪዎች በአከባቢው አስተዳደር አማካኝነት ወደ ቤተሰቦቻቸው ተሸኝተዋል። " ያሉት ምክትል ፕሬዜዳንቱ " ከዚህ ውጭ የሚወራውና የሚዟዟረው መረጃ ፍፁም ስህተት ነዉ። " ብለዋል።

" ተማሪዎቹ ከተሳሳተ ውሳኔያቸው እንዲመለሱና ወርቃማ ዕድላቸውን እንዲጠቀሙ የተቻለንን ሁሉ አድርገናል " ሲሉም ገልፀዋል።

ትላንት በደብረ ማርቆስ እንዲሁም በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች ከፈተጠረው ክስተት በተጨማሪ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተና አቋርጠው የወጡ ተማሪዎች መኖራቸውን ፈታኝ መምህራን የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሳውቀውናል።

ፈተናውን ሳይፈተኑ የመፈተኛ ማዕከላቸውን ለቀው ወጡ ከተባሉ ተማሪዎች በኩል ምን እንደተፈጠረ እና እንዳጋጠመ ፤ ለምንስ ይህን እንዳደረጉ ለማወቅ @officialtikvahethiopiaBOT ላይ መልዕክታቸውን ማግኘት አልቻልንም።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 " ቀጨኔ አካባቢ " አንድ ድርጅት የቡና ገለባ ከሻገተ ለውዝ ጋር በመቀላቀል የምግብ ዘይት ሲያመርት ተገኝቷል።

ድርጅቱ ሊገኝ የቻለው የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ባደረጉት መደበኛ ክትትል መሆኑን የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል።

በተቋሙ ላይ ቅኝት ሲደረግ፦

- ዘይት ማምረቻው የጤና ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የሌለው፤

- ለግብዓትነት የሚጠቀምባቸው ምርቶች ጥራታቸውና ደህንነታቸው ያልተጠበቀ፤

- የንጽህና አጠባበቅ መስፈርቶችን ያላሟላ ሆኖ ተገኝቷል።

የቡና ገለባን #ከተበላሸ_ለውዝ ጋር በመቀላቀልም የምግብ ዘይት ሲያመርት ነው የተገኘው።

ይህ ድርጅት የተጠቀመባቸው ግብዓቶች ተገቢ ካለመሆናቸው በተጨማሪ በቀላሉ የሚበላሹና አፍላ ቶክሲን በመፍጠር ለተለያዩ የካንሰር በሽታ አጋላጭ መሆናቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ፤ ድርጅቱ የተጠቀመባቸው ጥሬ እቃዎችና ባዕድ ግብዓቶች እንዲወገዱ እንደተደረገ እና በጉዳዩ ላይ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን ገልጿል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ የድርጅቱን ስም አልገለፀም።

@tikvahethiopia
" ፈተናው በሰላም ተጠናቋል " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 2/2015 ዓ.ም ድረስ ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቂያ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የከተማው ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

ቢሮው ፈተናው በአዲስ አበባ 9 የፈተና ጣቢያዎች መሰጠቱን አመልክቷል።

ፈተናውን 23,208 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለመውሰድ ተመዝግበው 22,533 የሚሆኑት መፈተናቸው ተገልጿል።

ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ፈተናውን ያልወሰዱና ተገቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተማሪዎች በቀጣይ እንደሚፈተኑ በትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ መቀመጡን ቢሮው አሳውቋል።

25,995 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እሁድ ጥቅምት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ፈተናውን ወደሚሰጥባቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ኦረንቴሽን ከተሰጣቸው በኃላ ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ ብሏል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተጠናቋል

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ  የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና መጠናቀቁን አሳውቋል።

አገልግሎቱ ፤ " የፈተና ኩረጃና ስርቆት ከፍተኛ የፈተና ደንብ ጥሰት ናቸው። ህግ ይከበራል። " ብሏል።

ለስራው መጠናቀቅ አወንታዊ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MoE

• 12,787 ተማሪዎች ፈተና አንፈተንም ብለው ጥለው ወጥተዋል።

• በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ ህይወቱ አልፏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መጠናቀቁን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ ለፈተና ከተቀመጡ 595 ሺህ ተፈታኞች ውስጥ 586 ሽህ 541 ተፈታኞች ፈተናውን ወስደዋል ብሏል።

" ፈተናው በተጀመረበት ወቅት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው አደጋ እና በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ስርዓቱ ባፈነገጠ ሁኔታ አንፈተንም በማለት 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው መውጥተዋል " ሲል አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በመግለጫው ፤ " ከሌሎቹ በተለየ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ሃይል በተቀላቀለበት መልኩ በደረሰ ግርግር የአንድ (1) ተማሪ ህይወት ሲያልፍ በፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት ደርሷል። " ማለቱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ምንም አይነት እድል አይሰጥም " - ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር ፈተና አቋርጠው ለወጡ ምንም አይነት እድል አይሰጥም ብሏል።

ሚኒስቴሩ ማምሻውን በሰጠው መግለጫው ፤ በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል።

ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ሚኒስቴሩ ምንም አይነት እድል እንደማይሰጥ አሳውቋል።

Credit : AMN

@tikvahethiopia
#Update

ለመጀመሪያ ጊዜ በፌዴራል ተቋማት / ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተሰጠ የሚገኘው የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የመጀመሪያው ዙር / የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ተጠናቋል።

ከጥቅምት 5/2015 ዓ/ም ጀምሮ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መግባት ይጀምራሉ።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ፤ የተማሪዎች ጉዳይ የሀገር ጉዳይ ስለሆነ ባለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችን ጉዳይ በንቃት እንደመከታተላችን ምን ልዩ ነገሮች ፤ ምን ምን ክፍተቶች ነበሩ ፤ እንዴትስ አለፈ የሚለውን ለመመልከት እንወዳለን።

(ከፈታኝ መምህራን ፣ ከተማሪ ወላጆች ፣ ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የተሰባሰበ)

- ተማሪዎችን ወደ ተቋም በማስገባት ሂደት አንዳንድ ቦታዎች ላይ የትራፊክ አደጋዎች ተከስተው ነበር ፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ የተሽከርካሪ እጥረትም ተስተውሏል።

- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአንድ ተማሪ ህይወት የቀጠፈ ድንገተኛ የድልድይ መደርመስ አደጋ ደርሶ በርካቶችን ያስደነገጠ ቢሆንም የአደጋው ሰለባ ያልሆኑት ተማሪዎች የመጀመሪያው ቀን ፈተናዎች አምልጧቸው ቀጣዮቹን ወስደዋል።

- በምግብ አቅርቦት በኩልም በመጀመሪያው ቀናቶች ክፍተቶች የታዩባቸው ተቋማት ነበሩ ለአብነት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ይጠቀሳል ፤ የተማሪ ወላጆች ይህ ክፍተት እንዲስተካከል ጠይቀው እንደነበር ይታወሳል።

- ፈተና ለመፈተን ረጅም ርቀትን ተጉዘው ወደ ተለያዩ ተቋማት የሄዱ አንዳንድ መምህራን በገቡበት ዕለት ከማደሪያ ቦታ ጋር በተያያዘ ተቸግረው / ተጉላልተው የነበሩባቸው ሁኔታዎችም ነበሩ።

- ከፈተና ቀን በፊት የሞባይል " ስልክ " ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

- በርከታ " ነፍሰጡር " ተፈታኞች ወደመፈተኛ ተቋማት ከገቡ በኃላ በሰላም ተገላግለዋል።

- በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ " ፈተና ሳይፈተኑ " ግቢውን ለቀው የወጡ ተማሪዎች ነበሩ ፤ በግቢው በነበረው ግጭት የአንድ (1) ተማሪ ህይወት አልፏል የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት ደርሷል ፤ በተመሳሳይ በደብረ ማርቆስ " የጤና ካንፓስ " ከነበሩ ተፈታኞች መካከል " ፈተና አንፈተንም " ብለው የወጡ ነበሩ ፤ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጣቢያዎችም እንዲሁ የወጡ ነበሩ።

- ምንም እንኳን ከየትኛው ተቋም እንደሆነ #በትክክል ለመለየት ባይቻልም በጥብቅ የተከለከለውን ሞባይል ስልክ / ሌላ መገናኛ ዘዴ ይዘው ገብተው ፈተናው ከጀመረ በኃላ / እንዲሁም ተጠናቆ ከወጡ በኃላ ከማደሪያ ክፍል ውስጥ በፎቶ በየቴሌግራም ግሩፖች ሲለቁ የነበሩ ተፈታኞች ነበሩ። ለዚህም ይመስለል በፈተና ሰዓት " ቴሌግራም መተግበሪያ " በሀገሪቱ ተገድቦ የነበረው።

እነዚህን የፈተና ወረቀት ሚለቀቅባቸውን የቴሌግራም ግሩፖች ደግሞ " ፈተናው ተሰርቋል " በሚል ለብዙሃን ሲያሰራጩ የነበሩ ብዙ ተከታይ ያላቸው ገፆች ነበሩ (ለአብነት አንድ የፈተና ወረቀት ፎቶ ስሊቀቅበት የነበረ ግሩፕ በአንድ ጊዜ የአባላቱ ቁጥር ከአስር ሺህ እንዲያልፍ አድርገዋል) ።

በማህበራዊ ሚዲያዎችና ከኛ የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን በስፋት " የፈተና ወረቀቶች ቀድሞ ወጥቶባቸዋል " እየተባለ ሲነገርባቸው የነበሩትን ግሩፖች በአግባቡ ረጅም ሰዓት ወስደን የተመለከትን ሲሆን ወረቀቶቹ ከፈተና ክፍል እና ፈተናው ከተጀመረ በኃላ የተሰራጩ መሆኑን ታዝበናል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ተማሪዎች ምንም የመገናኛ ዘዴ (ስልክ የመሳሰሉ) ሳይዙ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዲፈተኑ ከሚደረግባቸው ምክንያቶች አንዱ ድንገት እንኳን ፈተናውን በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቁ ካሉ ተማሪዎች እንዳያገኙት በሩን ለመዝጋት እንደነበር መግለፁ ይታወሳል።

ፈተናው ተሰርቆ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ወጥቷል ?

በማህበራዊ ሚዲያ ከትላንት ጀምሮ አንዳንድ አካላት ፈተናውን ከመሰጠቱ በፊት " ቀድሞ ተሰርቆ ወጥቶ " በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተሰራጭቶ እየተሰራ ነው የሚል በማስረጃ ያልተደገፉ ፅሁፎችን ሲያጋሩ ተመልክተናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የ2014 ዓ/ም የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ከፈተናው ቀድሞ / ተሰርቆ ወጥቶ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራ የሚያሳይ ማስረጃ እስካሁን ድረስ ማግኘት አልቻለም።

ከላይ እንደተገለፀው ከፈተና መስጫ ክፍልና ከፈተና በኃላ ከማደሪያ ክፍል ውስጥ የፈተና ወረቀት በፎቶ አንስተው ሲያሰራጩ የነበሩ ተፈታኞች መኖራቸውን ታዝቧል (ከየቱ ተቋም እንደሆኑ ለማወቅ ባይቻልም)።

ውድ ቤተሰቦቻችን የ2013 የ12ኛ ክፍል ፈተና ወቅት ፦
- የታሪክ ፣
- የኬሚስትሪ ፣
- የባዮሎጂ
- የስነ ዜጋና ስነምግባር ትምህርት ፈተናዎች ፈተናው ከሚሰጥበት ሰዓታት በፊት (ምሽት ላይ) በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መሰራጨታቸውን በዚህም ፈተናዎቹ " ቀድመው ተሰርቀው " መውጣታቸውን በበቂ ማስረጃ አረጋግጦ ማሳወቁ ይታወሳል።

በወቅቱ የትምህርት ሚኒስቴር እና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት " ምንም የተሰረቀ ፈተና የለም " የሚል ምላሽ መስጠታቸው አይዘነጋም።

በአሁኑ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተሰጠው የ2014 ፈተና ከፈተናው ከሰዓታት #በፊት የጥያቄ ወረቀቶች እስካሁን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲሰራጩ ለማየት አልቻልንም፤ ከቤተሰቦቻችንም መሰል ጥቆማ አለመጣም።

ዘንድሮ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር የተደረገበት ስለመሆኑ ከፈታኝ መምህራን ተገልጾልናል።

- ከ2014 የተጠናቀቀው " የማህበራዊ ሳይንስ " ፈተና ጋር በተያያዘ በአንዳንድ ተቋማት ተፈታኝ ተማሪዎች ክፍል ውስጥ በመጮኽ ፈታኞችን ለማዋከብ የሞከሩ እንደነበር ነገር ግን በፀጥታ ኃይሎች እንዲወጡ መደረጉን ከመምህራን ሰምተናል። በሌላ በኩልም ፤ " ካልሰራቹልን ፤ እንድንኮራረጅ ካላደረጋችሁን " በሚል በድፍረት የጠየቁም እንዳልጠፉ ከመምህራን ሰምተናል።

በቀጣይ ለሚሰጠው የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ፦

• ተማሪ በማጓጓዝ ሂደት አሽከርካሪዎች እንዲጠነቀቁ ማደርግ ይገባል።

• ተማሪዎች "ስልክ" እንዳያስገቡ ፍተሻው ተማሪ ወደ ግቢ ሲገባ ብቻ ሳይሆን ድንገተኛ ፍተሻ በየማደሪያ ክፍሎች ማደረግ፣ ለፈተና ወደ ክፍል ሲገቡም ፍተሻ ማድረግ ይገባል።

• በምግብ አቅርቦት ላይም የሚታዩ ክፍተቶች ካሉም በፍጥነት ማረም ይገባል።

• ስለሀገርና ትውልድ እንናስባለን የሚሉ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ተማሪዎችን የሚረብሹ ማስረጃ እና ያልተረጋገጡ ወሬዎችን ከማውራት መቆጠብ አለባቸው።

• ተፈታኝ ተማሪዎች #ተረጋግተው ፈተናቸውን መፈተን አለባቸው ፤ የሚወስዱት ፈተና ከአሁኑ ከተሰጠው ፈተና (ከማህበራዊ ሳይንስ) ጋር ተመሳሳይ አይነት ፈተና ባለመሆኑ የሚሰራጩትን ሀሰተኛ መረጃዎች በጥንቃቄ መመልከት እና ከዚህ መራቅ አለባቸው ፤ በማህበራዊ ሚዲያው ጫጫት ሳይረበሹ ፈተናውን እንዲወስዱ ወላጆች፣ ኃላፊነታ ያለባቸው ተሰሚ ሰዎች፣ ዋና ዋና መገናኛ ብዙሃን የበኩላቸውን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

መልዕክቶችን ለመላክ / ለማስተላለፍ ለምትፈልጉ ለተማሪ ወላጆች፣ ፈታኝ መምህራን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ክፍት ነው 👇
@officialTikvahethiopiaBOT

@tikvahethiopia
" 2 ተማሪዎች ሞተዋል እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው " - ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ

የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፤ ፈተና ያጠናቀቁ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን ወደ መጡበት አካባቢና ቤተሰቦቻቸው ለመሸኘት ዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል።

ነገር ግን " የማህበረሰቡን ሰላምና መረጋጋት የማይሹ " ያላቸው አካላት የተሳሳተ ወሬ እያሰራጩ ነው ብሏል።

እነዚሁ አከላት ፤ " ቴፒ ግቢ 2 ተማሪዎች በወባ በሽታ ታመው ሞተዋል " በማለት ማህበረሰቡን በተለይም የተፈታኝ ተማሪዎች ቤተሰቦችን ለማሸበር የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ገልጾ መላው ማህበረሰብ በተለይ የተማሪ ወላጅና ቤተሰቦች የተሰራጨው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን እንዲገነዘቡ እና እንዲረጋጉ መልዕክት አስተለልፏል።

ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ሰዓት ተማሪዎቹን ወደ መጡበት አካባቢ ለመሸኘት እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ምንም አይነት እድል አይሰጥም " - ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ሚኒስቴር ፈተና አቋርጠው ለወጡ ምንም አይነት እድል አይሰጥም ብሏል። ሚኒስቴሩ ማምሻውን በሰጠው መግለጫው ፤ በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል። ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ሚኒስቴሩ…
" መፈተን የፈለገ ይፈተናል ፤ መፈተን ያልፈለገ ትቶ ይሄዳል፤ ትቶ ለሚሄደው ተማሪ ግን ምንም ተጨማሪ ዕድል የሚሰጥበት መንገድ የለም " - ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ መውሰድ የነበረባቸውን ፈተና ሙሉ በሙሉ ወይም ውስን ፈተናዎችን ብቻ ወስደው ከዩኒቨርሲቲ ጥለው ወጥተዋል ያላቸው ፦

- ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ (መካነ ሰላም ካምፓስ) 1,700 ተማሪዎች

- ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ 1,226 ተማሪዎች

- ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ 2,711 ተማሪዎች

- ከደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ 7,150 በአጠቃላይ 12,787 ተማሪዎች ናቸው።

እንዚህ ተማሪዎች ከግቢ የወጡት " ፈተና መፈተን እንደማይፈልጉ " አሳውቀው በመሆኑ በቀጠይ ፈተና እንደማይወስዱ አሳውቋል።

ጥቅምት 8 ፈተና ሚጀምሩት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከዚህ ሊማሩ እንደሚገባ የገለፀው ሚኒስቴሩ ፤ " ፈተናውን ተፈትነን አናልፍም ብሎ በመፍራት / በሌላ መንገድ ፈተናውን ለመረበሽ ሲሞከር ዝም ብለው ሌሎችን ተከትሎ መሄድ በራሳቸው ህይወት ላይ አስከፊ የሆነ ነገር ይዞ እንደሚመጣ ማወቅ አለባቸው " ብሏል።

ተማሪዎች በራሳቸው ብቻ ተማምነው እንዲፈቱ ሌሎች አስገድደው አደጋ ያደርሱብኛል ብለው የሚሰጉ ካሉም የተማሪዎችን ደህንነት ማስጠበቅ የትምህርት ሚኒስቴር ስራ ስለሆነ " ደህንነታችሁን እናስጠብቃለን ለዚህም ቃል እንገባለን " ብሏል።

" መፈተን የፈለገ ይፈተናል ፤ መፈተን ያልፈለገ ትቶ ይሄዳል ትቶ ለሚሄደው ግን ምንም ተጨማሪ ዕድል የሚሰጥበት መንገድ የለም " ሲል አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE • 12,787 ተማሪዎች ፈተና አንፈተንም ብለው ጥለው ወጥተዋል። • በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ ህይወቱ አልፏል። ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መጠናቀቁን ገልጿል። ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ ለፈተና ከተቀመጡ 595 ሺህ ተፈታኞች ውስጥ 586 ሽህ 541 ተፈታኞች ፈተናውን ወስደዋል ብሏል። " ፈተናው በተጀመረበት…
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ከተሳተፈው ሰው ብዛት፣ ከተፈታኙ ብዛትና በዚህ መልኩ ፈተና ሲሰጥ የመጀመርያ ከመሆኑ አንጻር የሚጠበቅ ቢሆንም አጋጥመዋል ያላቸው ቁልፍ ችግሮች ፦

- በቂ ኦሬንቴሽን ባለማግኘት ወይም በማወቅም ጭምር የተከለከሉ ቁሶችን ይዘው የመጡና ይዘው የተገኙ ተፈታኞች መኖራቸው፤

- ነፍሰጡርና መጫት ተፈታኞች በሌላ ዙር እንደሚፈተኑ አስቀድሞ ቢገለፅም በዚህኛው ዙር ለፈተና መምጣታቸው፣

- በፈተና አዳራሽ #በጋራ_ካልሰራን ብለው ከፈተና አስፈጻሚዎች ጋር ግብ ግብ የፈጠሩ ተፈታኞች ማጋጠማቸው፤

- ከተሰጣቸው መመሪያና ከፈታኝ የማይጠበቅ ተግባር ላይ የተሳተፉ የፈተና አስፈፃሚዎች ማጋጠማቸው፤

- በትራንስፖርት እጥረት ምክንያት ዘግይተውና አምሽተው በዩኒቨርስቲዎች የደረሱ መኖራቸው፤

- ተማሪዎች ስልክ እንደሌላቸውና ፈተና ቢወጣ እንኳ እንደማያገኙ እየታወቀ ፈተና እንለጥፋለን የሚሉ " የቴሌግራም ገፆች " ማጋጠማቸውና ፈተና ካለቀ ወይም በመሰጠት ላይ እያለ አንድም ሁለትም ገፅ መለጠፋቸው፤ 

(የትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia