TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING ለሳፋሪኮም ሞባይል መኒ ተፈቀደ። የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ " ሞባይል መኒ " መፈቀዱን አስታውቀዋል። ይህን ያሳወቁት በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ ነው። ውድ ቤተሰቦቻችን ተጨማሪ መረጃዎችን እንልክላችኃለን። @tikvahethiopia
#MobileMoney
ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ምስጋና አቀረቡ።
የኬንያው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዊልያም ሩቶ የኢትዮጵያ መንግስት ለሳፋሪኮም የሞባይል ገንዘብ ዝውውር እንዲያደርግ በመፍቀዱ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል።
ፕሬዜዳንት ሩቶ " የኬንያ ህዝብ ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ይህን እንዳስፈጽም የቤት ስራ ሰጥቶኝ ነበር፤ የኢትዮጵያ መንግስት ይህን አገልግሎት በመፍቀዱ አመሰግናለሁ " ብለዋል።
ሳፋሪኮም በኬንያ በ " ኤም ፔሳ " የገንዘብ አገልግሎት ያገኘውን ስኬት በኢትዮጵያ ለመድገም እንደሚሰራም ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopia