TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቡራዩ⬇️

ከቡራዩ ከተማ ከተፈናቀሉት መካከል 1 ሺህ 700 ያህሉ ወደ መኖሪያ ቀያቸው
#መመለሳቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

የከተማዋ ኮምንኬሽን ቢሮ እንደገለጸው በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ ከተማ በአሁኑ ወቅት መረጋጋት በመፈጠረቱ ነው በአዲስ አበባ ጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው የነበሩት #ተፈናቃዮች መመለስ የጀመሩት።

በመጪው ሰኞ መስከረም 14 ቀን 2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ እለት በመሆኑ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮችን ወደ ሌላ ስፍራ የማዘዋወር ስራ መጀመሩን ቢሮው አክሎ አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅትም ተፈናቃዮች ተጠልለው ከሚገኙበት 9 ትምህርት ቤቶች ወደ ሌላ ቦታ የማሸጋሸግ ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል።

©የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወቃይት ጠገዴ⬆️

ከወልቃይት ጠገዴ ተፈናቅለው #ጎንደር ከተማ በጊዚያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙት #ተፈናቃዮች መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ ይስጠንና ወደቀያችን እንመለስ ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።  ቁጥራቸው ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ አብዛኛዎቹ ደግሞ በአፍላ የወጣትነት የዕድሜ ክልል የሚገኙ እነዚህ ተፈናቃዮች በጎንደር ከተማ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ በተዘጋጀላቸው ጊዚያዊ መጠለያ ውስጥ ነው ያሉት - በተጨናነቀ ሁኔታ።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰላም ሚኒስቴር‼️

ከ1 ሚሊየን በላይ #ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያ ቀያቸው መመለሳቸውን የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ካሚል የተቋማቸውን የ6 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ ተወካች ምክር ቤት ለውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ አቅርበዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትሯ በሪፖርታቸው ከህብረተሰቡ ጋር በተቀናጀ ተግባር 1 ሚሊየን 20 ሺህ ያህል ዜጎችን ወደ ቀያቸው መመለስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ቀሪ ተፈናቃዮችን በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ሙሉ በሙሉ የማቋቋም ስራ እንደሚያከናውንም ተናግረዋል፡፡

በጋምቤላ፣ ደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች በተመረጡ 12 ወረዳዎች ግጭቶች ከመከሰታቸወው በፊት የግጭት መንስኤዎችን የመለየትና ቀድሞ መከላከል ስራ መጀመሩንም ጠቁመዋል፡፡

በተለያዩ ግጭቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች እለታዊ እርዳታና ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችሉ ስራዎች ባለፉት 6 ወራት መሰራታቸውንም አንስተዋል፡፡

ለሰላም ግንባታ መሰረት መጣሉን የተናገሩት ሚኒስትሯ ግጭቶች ከመከሰታቸው በፊት የግጭት መንስኤዎችን ለመለየት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ከ900 በላይ በግጭት ወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ክትትል እየተደረገ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፥ ክልሎች በወንጀሉ በዋናነት በመሳተፍ ለተጠረጠሩ ግለሰቦች ሽፋን ከመስጠት ይልቅ አሳልፈው ለህግ እንዲሰጡም ጠይቀዋል።

ኤፍ ቢ ሲ እንደዘገበው የተዘረፉ ንብረቶችን ለማስመለስ እየተሰራ ሲሆን÷ በቃጠሎና ሌሎች ምክንያቶች የወደሙ ንብረቶችን አቅም በፈቀደ መጠን ለመገንባት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለማስቆም ምንጩን የማጥራት ስራ መጀመሩን ጠቅሰው፥ ህገ ወጥ የገንዘብና የሰዎች ዝውውርም ከሌሎች #የወንጀል ድርጊቶች ጋር ተመጋጋቢ ስለሆነ÷ ወደ ፊት በትኩረት ከሚሰራባቸው ነጥቦች መካከል መሆኑንም ጠቅሰዋል።

via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ክልል በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች የግጭት #ተፈናቃዮች መንግሥት አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ አላቀረበልንም፤ ለተላላፊ በሽታም ተጋልጠናል ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል፡፡ ከሁለቱ ዞኖች ወደ 46 ሺህ የሚጠጋ ሕዝብ ተፈናቅሏል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ እስካሁን ዕርዳታ የደረሳቸው 2 ሺህ 700 ብቻ ናቸው፡፡ ተፈናቃዮቹ በላይ አርማጭሆና ምዕራብ ደንቢያ ወረዳዎች ባሉ ቀበሌዎች ተጠልለዋል፡፡ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አደጋ መከላከል ምግብና ዋስትና ቢሮ 2 ሺህ 500 ኩንታል ስንዴና 3 ሺህ ኩንታል አልሚ ምግብ አሰራጭቻለሁ ብሏል፡፡ ከዞኑ 200፣ ከፌደራል ደሞ 600 ተጨማሪ ኩንታል እህል እየተጓጓዘ ነው፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH🔝

በጌዳኦ ዞን ለሚገኙ #ተፈናቃዮች በእናተ በTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በኩል በተሰበሰበው #ገንዘብ_ድጋፍ ለማድረግ በዛሬው ዕለት ወጣቶች ወደስፍራው አቅንተዋል።
.
.
.
አጠቃላይ የተሰበሰብው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ እንዲሁም የተፈፀሙ ግዢዎችን በደረሰኝ ለእናተ የማሳያችሁ ይሆናል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ:በትግራይ ክልል የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር #ሓጎስ_ጎድፋይ የተመራው እና ለጌድዖ #ተፈናቃዮች እገዛ ለማድረግ ያቀደው የጤና ባለሙያዎች ልዑካን ቡድን👆ዶክተር ሃጎስ በትዊተር ገፃቸው "ሕዝባዊነት #ብሔርም #ድንበርም የለውም" ብለዋል። #ኢትዮጵያ

@tsegabwolde @tikvahethiopia