TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መልዕክት

የ " መስቀል ደመራ በዓል " አከባበርን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተላለፈ መልዕክት ፦

- ሁከት ቀስሰቃሽ መልዕክቶችን በቲሸረሰቶች ላይም ሆነ በባነሮች ላይ በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ ይዞ መገኘት በፍፁም አይፈቀድም።

- በበዓሉ ላይ ህገ መንግስቱ የደነገገውን የኢትዮጵያን የፌዴራል ሰንደቅ ዓላማ #ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የፀደቀውን የቤተክርስቲያን ዓርማን ብቻ መጠቀም ይገባል። ከዚህ ውጪ የሆነ ምንም ዓይነት አርማም ሆነ ሰንደቅ አላማ መያዝ በጥብቅ የተከለከለ ነው። የምንጠቀመው ሰንደቅ ዓላማ ሆነ የቤተክርስቲያን አርማ በግልፅ የሚታዩ በሁለቱም ፊት ዓርማዎቹ በትክክል የተቀመጡ መሆን አለባቸው።

- በቲሸርቶች ፣ በባነሮች እንዲሁም በትርኢቶች ላይ ሁሉ ሌሎች ወገኖችን የሚያስከፉ፣ መብትን የሚጋፉ ሁከት ቀስቃሽ የሆኑ ጥቅሶችን መጠቀም ከሥነ ምግባር ውጪ ከመሆኑም በላይ ለሁከትና ግርግር መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

- ወደ መስቀል አደባባይ በሚደረግ ጉዞ #ተደጋጋሚ ፍተሻ ይደረጋል፤ የሚደረገው ፍተሻ ለደህንነታችን ተብሎ የሚደረግ ፍተሻ መሆኑን በመገንዘብ መላው ህዝበ ክርሰቲያን ራሱን ለፍተሻ ዝግጁ ማድረግና ፍጹም በሆነ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ለፍተሻ መተባበር እንደሚገባው በመረዳት የጸጥታ አካላትን መተባበር አለበት።

- በመስቀል አደባባይ እንዲሁም ደብረ ዕንቁ ቅድስት ልደታ ማርያም ጉዳይ የሚመለከተውን አካል በሕግ አግባብ መጠየቅ የሚገባና እና በጉዳዩ ዙሪያ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ ያከናውናሉ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎች በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ሊደረግ አይገባም።

- በቤተክርስቲያን ማዕከላዊ አስተዳደርና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ተዘጋጅቶ ከሚሰራጨው መጽሔት እና ብሮሸር ውጪ ምንም ዓይነት የህትመት ውጤት ስለማይሰራጭ ከእነዚህ ውጪ የሆኑ የህትመት ውጤቶችንና በራሪ ወረቀቶችን ይዞ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው። ይዞ የተገኘም በህግ ተጠያቂ ይሆናል።

- ከመስቀል አደባባይ ውጪ በአድባራትና ገዳማት በሚከበሩ የመስቀል ደመራ በዓላት ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር እና በመረዳዳት መሥራት የሚገባ ሲሆን ሁከት ቀስቃሽ ከሆኑ መልዕክቶች በመታቀብና ህጋዊ ያልሆኑ ሰንደቅ ዓላማዎችን ባለመጠቀም የበዓሉን ሰላማዊነትና የመስቀሉን ዓላማ መሰረት ያደረጉ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን የተላበሱ እንቅስቃሴዎች ሊደረጉ ይገባል።

- ማንኛውም አጠራጣሪ እና ለጸጥታ ስጋት የሚሆኑ ነገሮች ሲያጋጥም በቦታው ለተመደቡ የሥነሥርዓትና የጸጥታ አስከባሪ አባላት / ለፖሊስ አካላት መጠቆም ይገባል።

(የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን)

@tikvahethiopia