TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥንቃቄ📌ከአዲሱ የትምህርት ፎኖተ ካርታ ጋር ተያይዞ የ2011 ዓ.ም. #ተመራቂ የለም እተባለ የሚሰራጨው መረጃ የሀሰት መሆኑ ልታውቁት ይገባል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ📌ከአዲሱ የትምህርት ፎኖተ ካርታ ጋር ተያይዞ የ2011 ዓ.ም. #ተመራቂ የለም እተባለ የሚሰራጨው መረጃ የሀሰት መሆኑ ልታውቁት ይገባል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንዴት አመሽታችኃል? ላለፉት በርካታ ሳምንታት ብዙ ሳስብበት እና ብዙ ስጨነቅበት የነበረውን ጉዳይ ዛሬ ለናተው አቀርባለሁ።

በቅድሚያ አንድነት ሀይል ነው!!
.
.
TIKVAH-AID፦
እነዚህን እቅዶች ተመልከቷቸው እና አስተያየት ስጡባቸው። እቅዶቹን ሳወጣ ሁሉን አካታች እና አሳታፊ ለማድረግ ሞክርያለሁ።

በየወሩ ለመስራት የታቀደ እቅድ-TIKVAH-ETH

🔹በየወሩ በከፍተኛ የጤና ችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን ለማሳከም ከ100,000 ብር - 150,000 ብር ማሰባሰብ።

🔹ትምህርታቸው በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት መከታተል ሳይችሉ የቀሩ እና ያቋረጡ ወገኖችን ማገዝ፦

▪️በየዩኒቨርሲቲዎቹ ውስጥ በችግር ውስጥ ሆነው ለሚማሩ ተማሪዎች ቢያንስ የአንድ አመት ሀንዳውት ኮፒ የሚያደርጉበትን ወጪ መሸፈን።

▪️አልባሳት እና ጫማ የሚያስፈልጋቸው #ተመራቂ ተማሪዎችን ወጪ መሸፈን።

ልዩ...🔹በችግር ውስጥ ሆነው ትምህርታቸው የሚከታተሉ ሴት እህቶቻችንን በሁሉም ረገድ እገዛ ማድረግ፦

▪️የንህፅና መጠበቂዎችን ማሟላት
▪️የአልባሳት ግዢ መፈፀም
▪️ከትምህርት ጋር የተገናኙ ማናቸውም ነገሮችን ማሟላት

እቅዶቹን እንዴት እናሳካቸው??
TIKVAH-ETH
TIKVAH-EDU
TIKVAH-AID
TIKVAH-UNIV

በነዚህ ቻናሎች ከ200,000 ሺ በላይ ተከታዮች በመላው ኢትዮጵያ እና በተለያዩ ሀገራት አሉ። በዚህ ስራ ውስጥ ቢያስ 50,000 አባላት በቅንነት ብንሳተፍ የብዙ ሰዎችን ህይወት መቀይር ይቻላል።

በየዕለቱ 10,000 የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ቢሳተፍ፦ 1 ብር ከአካውንታችን ቀንሰን ለዚህ አላማ ብናውል:

1×10,000=10,000 ብር በቀን
10,000×30=300,000 ብር በወር

🔹150,000 ብር ለህክምና ወጪ
🔹150,000 ብር ለተለያዩ ድጋፎች

የገንዘብ ማሰባሰቢያው መንገድ፦
.ሞባይል ባንኪንግ
.በአካል ባንክ በመሄድ ማስገባት

🔹በቀን አንድ ብር ማስገባት የማንችል የ7 ቀን 7 ብር አንዴ ብናስገባ እንችላለን።

▪️በየቀኑ 1 ብር ድጋፍ ማድረጋችን ሰዎችን ከማገዝ በተጨማሪ በህይወታችን ውስጥ ትልቅ ትምህርት እየሰጠም ያልፋል!!

ማሳሰቢያ፦ ተቀማጭ የሚባል ገንዘብ የለም። በወር ውስጥ የሚዘጋጀው አካውንት ባዶ ይሆናል። በወር የተሰበሰብው ገንዘብ በ30ኛው ቀን ወጥቶ ለታለመለት አላማ ይውላል።

ግልፅነትን በተመለከተ፦ በየዕለቱ የባንክ ቤት መረጃዎች ይፋ ይደረጋሉ። ይህንንም በየባንኮቹ የሚሰሩ የTIKVAH-ETH አባላት ሃላፊነታቸውን ይወጣሉ።

ፈተና የሆነብኝ የtikvah-aid የባንክ ሂሳብ መክፈት ነው። ሂሳቡ መጠሪያው በtikvah-aid እንዲሆን ነው የተፈለገው። በዚህ ላይ ምን ማድረግ እንዳለብን መመካከር ይኖርብናል። የባንክ ሰራተኞችም አግዙን!!

🔹ማሳሰቢያ 2፦ ቋሚ እገዛ በቀጣይ አመታት እስኪደረግ ላአሁኑ የተለያዩ የተቸገሩ ሰዎችን ነው የምናግዘው።

አስተያየት እና ምክር በዚህ አድርሱኝ፦ @tsegabwolde
መቀለ ዩኒቨርሲቲ🔝

"ትላንት የመቀለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ #ተመራቂ ተማሪዎች ለጎዳና ተዳዳሪዎች የተለያዩ ልብሶችን ከተማሪዎች በማሰባሰብ ሲሰጡ ውለዋል፡፡ ባለፈው ሳምንትም በበጎ አድራጎት ስራ ላይ መዋላቸው ይታወሳል፡፡ መልካምነት፣ ፍቅር እና ሰላም ለኢትዮጵያ!"

ለሌላውም ወጣት ትልቅ ትምህርት እየሰጣችሁ ስለምትግኙ በቻናሉ ስም ትልቅ ምስጋና እናቀርባለን!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነቀምት🔝

የወለጋ ዩኒቨርስቲ Civil Engineering #ተመራቂ ተማሪዎች ዛሬ GC Announcement ቀንን አክብረዋል። ወጣቶቹ ቀኑን ያከበሩት "ሠውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!" በሚል ከ7ኛ-10ኛ ለሚማሩ ተማሪዎች አጋዥ መፀሀፍትን በስጦታ በማበርከትና ነቀምት ከተማን #በማፅዳት ነው። ሁሉም በአቅሙ #የሚችለውን ቢያደርግ ሁላችንም #የተሻለ ቦታ እንደርሳለን ሲሉ ተመራቂዎቹ መልዕክት አስተላልፋዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትላንት በትራፊክ አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን ተዘግቦ ነበር፦

• ከሟቾቹ ውስጥ ሦስቱ ጓደኛማቾች ይገኙበታል
• 3ቱም የ3ኛ ዓመት የአርኪዮሎጂ ተማሪዎች ናቸው
• ያቤሎ በሀዘን ተመታለች!
• እንደወጣን አንመለስም! …

በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል።

አደጋው የተከሰተው ከኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ ወደ ደቡብ ክልል ኮንሶ ከተማ ኮንትሮባንድ ጭኖ በፍጥነት ሲጓዝ የነበረ ተሽርካሪ ከከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።

በደረሰው ከባድ የትራፊክ አደጋ ከ15 ሰዎች በላይ ህይወት አልፏል። ከቦራና ወደ #ወላይታ_ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለ2ኛ ሴምስተር ምዝገባ ሲጓዙ የነበሩት የ3ኛ ዓመት የ#አርኪዮሎጂ #archeology ተማሪዎች የሆኑት ተማሪ #መቅደስ_ተሰፋዬ፣ ተማሪ #ትዝታ_ይድነቃቸው እና ተማሪ #ከና_ሚፊታ በመኪና አደጋ ሕይዋታቸው ተነጥቋል፡፡

ከሟቾቹ ውስጥ ከላይ በፎቶው የምትመለከቷቸው ሦስት ጓደኛሞች የአደጋው ሰለባ ሆነዋል፡፡ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የዘንድሮ #ተመራቂ ተማሪዎች ነበሩ::

• (በመንገድ ላይ እየቀረን ነው)

ያገሬ ልጆች እንደወጡ አይመለሱም፤ አንመለስም!

ነፍስ ይማር!

Via Getu Temsegen
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠርጣዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ...

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በአንድ ተማሪ ሞት የተጠረጠሩ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

ዩኒቨርሲቲው ባወጣው መግለጫ ዓርብ ግንቦት 16/2011 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ ምንጩ ያልታወቀ ጥቃት በተማሪዎች ላይ ደርሷል ብሏል።

ጥቃቱ ከተለመደው የተማሪ #ፀብና #ግርግር ለየት ያለ ባህሪ ያለው ሲሆን፥ ጩኸትና ግርግር የማይታይበት ተማሪዎችን #በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት የሚያደርስ ነበርም ነው ያለው።

ጥቃት አድራሾችም ፊታቸውን በመሸፈናቸው በቀላሉ ለመለየት አስቸጋሪ ነበር ያለው ዩኒቨርሲቲው፥ ሆኖም ግን አርብ ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ ከግቢ ወጥተው ወደ ጫካ ሲገቡ በማህበረሰቡ ጥቆማ የተወሰኑትን የፀጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ሥር አውሏቸው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ስለ ችግሩ እና ስለ ቀጣይ የተማሪዎች ሰላም ተወያይተዋል። ድርጊቱን ያወገዙት ተወያዮቹ ችግር ፈጣሪዎቹን በማጋለጥ ለፀጥታ አካላት እንደሚሰጡም ቃል ገብተዋል። እስካሁን በድርጊቱ የተጠረጠሩ ተማሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ነው በውይይቱ ላይ የተገለፀው።

የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትም የክልሉ መንግሥት እና ሕዝብ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በአንድ #ተመራቂ ተማሪ ላይ በደረሰዉ የሕይወት መጥፋት ከልብ ማዘኑን በመግለፅ ድርጊቱን አጥብቀው #እንደሚያወግዙት ገልጿል።

የክልሉ መንግሥት ከሕዝቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ጥቃት አድራሾችን ተከታትሎ ለሕግ እንደሚያቀርብ ማስታወቁንም ነው አብመድ የዘገበው።

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጣው የሀዘን መግለጫም በደብረማርቆስ ዩንቨርሲቲ ተማሪ በነበረው ወጣት ሰዓረ አብርሃ ህልፈተ ህይወት የተሰማዉ #ጥልቅ_ሃዘን ገልጿል።

ጉዳዩን በአፅንኦት እየተከታተለው እንደሚገኝ የገለፀው የክልሉ መንግስት፥ ወንጀለኞች ወደ ህግ እንዲቀርቡ እና አስፈላጊዉ ፍርድ እንዲያገኙ ከሚመለከተዉ አካል ሆኖ እንደሚሰራ በመግለፅ ለሟች ቤተሰብ፣ ወዳጅና ዘመድ መፅናናትን ተመኝቷል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbaba

“ ኖህ ሪልስቴስት እየሰራው ያለው ህንፃ ላይ የወደቀ ብረት ነው የገደለው ” - ኮማንደር ማርቆስ

ኢዩኤል ታዬወርቅ የተባለ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ቤተሰብን ለመጠየቅ በመጣበት ከህንፃ ላይ በወደቀ ብረት በድንገት ሕይወቱ ማለፉ በማኀበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ ተስተውሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞን ለአደጋው ምላሽ እንዲሰጡ የጠየቀ ሲሆን፣ “ እኛ አገልግሎት አልሰጠንም ” ብለዋል።

ሆኖም፣ ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ምላሽ ሰጥተዋል።

ኮማንደር በሰጡት ምላሽ፣ “ ኖህ ሪልስቴስት እየሰራው ያለው ህንፃ ላይ የወደቀ ብረት ነው የገደለው። 4 ሰዓት ላይ ነው የሞተው በሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ” ብለዋል።

“ ሟቹ ኢዩኤል የሚባል ልጅ ነው። እድሜው 23 ነው። የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረ እንደሆነ ነው የተነገረኝ” ያሉት ኮማንደር ማርቆስ፣ አደጋው የደረሰው “የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ በበኩሉ ሟቹ የኪነህንፃ  (Architecture) #ተመራቂ ተማሪ እነደነበር ባሰራጨው የሀዘን መግለጫ አስታውቆ፣ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።

“ ተማሪ ኢዩኤል ታዬወርቅ የፋሲካ በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር በአዲስ አበባ ለማክበር የሄደ ሲሆን፣ በማግስቱ ከታናሽ ወንድሙ ጋር እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ኬንያ ኢምባሲ አካባቢ እየተሰራ ከሚገኝ ከፍተኛ ፎቅ በወደቀ ብረት በመጎዳቱ  ሚያዚያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በለጋ እድሜው ህይወቱ አልፏል ” ብሏል ዩኒቨርሲቲው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia