TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ አውሮፕላን ኪስማዮ ውስጥ እንዳያርፍ ተከለከለ!

ወታደሮችን አሳፍሮ ደቡብ ሶማሊያ ኪስማዮ ውስጥ ሊያርፍ ነበር የተባለ የኢትዮጵያ አውሮፕላን በኬንያ ኃይሎች በሚደገፉት የጁባላንድ ክልላዊ ወታደሮች መከልከሉን የዓይን ምስክሮች ገለጹ።

ወደ ኪስማዮ ያቀናው አውሮፕላን 'ከ90 በላይ ኮማንዶዎችን አሳፍሮ ነበር' የተባለ ሲሆን ተገቢውን መረጃ ቀድሞ አልሰጠም በሚል ምክንያት ነው እንዳያርፍ የተከለከለው ተብሏል።

ከምሥራቃዊ ኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ ተነስቶ ወደ ሶማሊያ እንደበረረ የሚነገርለት ይህ አውሮፕላን ኪስማዮ እንዳያርፍ በመከልከሉ ወደ ደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ በማቅናት ባይዶዋ ውስጥ እንዳረፈም ተነግሯል።

በኪስማዮ አየር ማረፊያ ሰራተኛ የሆነ ግለሰብ አውሮፕላኑ ከኢትዮጵያ መነሳቱንና በኋላም ወደ ባይዶዋ መሄዱን ለሮይተርስ አረጋግጧል። ነገር ግን አውሮፕላኑ የሲቪል ይሁን ወታደራዊ የታወቀ ነገር የለም።

#ቢቢሲአማርኛ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-20
"ክልላዊ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት የማቋቋም ጥያቄ የቤተ ክርስቲያኗ የዶግማና የቀኖና ትውፊት ለውጥ ሳይኖር አስተዳደራዊ ችግሮችን ለመፍታት መዋቅር የማበጀት ጥያቄ ነው" የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት አደራጅ ኮሚቴ

#ቢቢሲአማርኛ #BBCAMHARIC

የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት በክልል ደረጃ እንዲዋቀር የቀረበው ጥያቄ ምላሽ ቅዱስ ሲኖዶሱ በ30 ቀናት ውስጥ እንዲያሳውቃቸው ይህ ተግባራዊ ካልሆነ ግን አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ መኮንን አስታውቀዋል።

በዛሬው ዕለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኮሚቴው ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ ክልላዊ ፅህፈት ቤቱን ጥያቄ የሚቀበለው ከሆነ የሰው ኃይል አመዳደቡም ሆነ አፈፃፀሙ ይህ አደራጅ ኮሚቴና ጠቅላይ ቤተ ክህነት በጋራ የሚወስኑት እንደሚሆን ተገልጿል።

በተጠየቀው መሰረት አስቸኳይ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ የምዕመኑን ጥያቄ ለመመለስ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ኮሚቴው አስጠንቅቋል። እርምጃው ምን እንደሆነ በዚህ ወቅት ግልፅ ባያደርጉም ከዚህ ቀደም እንደተናገሩት በራሳቸው ክልላዊ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት እናቋቁማለን ማለታቸው የሚታወስ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-01-3

@tsegabwolde @tikvahethiopia