TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር መግለጫቸው ይበልጥ ትኩረቱን ያደረገው በሕገወጥ የሐዋላ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በሚመለከት ነው።

በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- 391 የሚደርሱ ሕገወጥ የሐዋላ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የባንክ ሂሳባቸው ተዘግቷል ፤ የግለሠቦቹን ስም ዝርዝር ለፍትሕ ሚኒስቴር በመላክ ክስ የመመስረት ሂደት ይጀመራል።

- በህገ ወጥ መልኩ #በጥቁር_ገበያ ላይ በተሠማሩ አካላት ላይ የተጠናከረ እርምጃ ይወሰዳል።

- በባንክ ቤቶች ውስጥ ያሉ የባንክ #ኃላፊዎችና #ሰራተኞችም በህገወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ አሉ በነዚህ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃና ሕጋዊ እርምጃ ይወሰዳል።

- ሕገወጥ ድርጊት ለሚጠቁሙ ዜጎች የወሮታ አከፋፈል ስርዓት ተዘጋጅቷል።

ይህ ማለት ፦

• ከተፈቀደው በላይ በቤት ውስጥ የብር ክምችት የሚያደርጉ፣

• የሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን የሚሠሩና የሚያሠራጩ አካላት፣

• በህገወጥ መልኩ የሐዋላ አገልግሎት የሚሠጡ ወይም በጥቁር ገበያ ላይ የተሰማሩ አካላትን ለሚጠቁሙ ዜጎች #ደህንነታቸው እና #ሚስጥራዊነታቸውን በጠበቀ መልኩ #የሚሸልምና #ወረታውን የሚከፈል ይሆናል።

- የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር የፈቀደውን የፍራኮ ቫሉታ ፍቃድ እንደ እድል በመጠቀም በህገወጥ መንገድ ዶላር በመጠቀም ሸቀጦችን የማስገባት ተግባር የተስተዋለ በመሆኑ በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች የባን ማስረጃ ለብሔራዊ ባንክ እንዲያቀርቡ ይደረጋል።

Credit : EPA

@tikvahethiopia