TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለገጣፎ ለገዳዲ‼️

የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል ያላቸውን መኖሪያቤቶች ማፍረስ ጀምሯል። በያዝነው ሳምንት ብቻ 3,685 ቤቶች እንደሚፈርሱ የከተማው ከንቲባ ወይዘሮ #ሀቢባ_ሲራጅ ለOMN ተናግረዋል። በቀጣያ 12ሺ ቤቶችን ለማፍረስ እቅድ መያዙንም ከንቲባዋ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ እንደሚሉት ቤቶቹን ለማፍረስ የተገደዱት የከተማው #መሪ_ዕቅድን_በመጣስ ለአረንጓዴ ቦታ (green area) በተከለለ ስፍራ በመሰራታቸው ነው። መኖሪያ ቤታቸው እንዲፈርስ የተወሰነባቸው ዜጎች በበኩላቸው በከተማው ለአመታት መኖራቸውንና በህጋዊ መንገድ ግብር ሲከፍሉ መቆየታቸውን ለዋልታ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

የለገጣፎ ከንቲባ ወ/ሮ #ሀቢባ_ሲራጅ ዛሬ #ዋንጫ የተሸለሙት የከተሞች የአትሌቲክስ ክለብ በማቋቋም ጥረት ከኦሮሚያ 3ኛ ደረጃን አግኝተው ነው። ሰሞኑን በለጋጣፎ በወሰደችዉ እርምጃ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሽልማት ተበረከተላት በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሽከረከረ ያለው ወሬ ፌክ ኒውስ ነው።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia