TIKVAH-ETHIOPIA
የጋምቤላ ክልል የኢሰመኮን ሪፖርት እንደማይቀበለው እና እንደሚያወግዝ በገለፀበት መግለጫ ምን አለ ? - ሚዛናዊነት የጎደለው በመሆኑ ምርመራውን አልቀበለውም፤ በጥብቅም አወግዛለሁ። - ሪፖርቱ የአንድ ክልል የፀጥታ ተቋምን ከተራ የአሸባሪ ቡድን ተላላኪ ጋር በአንድነት ያየ፤ በክልልና በአገር ላይ ይደርስ የነበረ ከፍተኛ ጥቃት በመቀልበስ ሂደት የህይወት መስዋዕትነት የከፈለውን የፀጥታ ተቋሙን በጅምላ የፈረጀ፤…
* ከኢሰመኮ የተለከ መግለጫ !
" በጋምቤላ ከተማ በብሔራዊ ሰብአዊ መብቶች ተቋም እና ሠራተኞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በክልሉ የስብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ምልከታ የሚጥል በመሆኑ የፌዴራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት በአፋጣኝ ሊያስቆሙ ይገባል " - ኢሰመኮ
ከኢሰመኮ መግለጫ የተወሰደ ...
" ... የሪፖርቱን (https://t.iss.one/tikvahethiopia/73948) ይፋ መደረግ ተከትሎ በማኅበራዊ ትስስር ድረ ገጾች እና መገናኛ ብዙኃን የተሳሳተ፤ አነሳሽ እና ዛቻ ያዘሉ መረጃዎች ሲሰራጩ እንዲሁም በኢሰመኮ ባልደረቦች ላይ ያነጣጠሩ የጥላቻ መልእክቶች ሲዘዋወሩ ቆይተዋል።
ኮሚሽኑ ጉዳዩን ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር መፍታት እንደሚቻል በማመን ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቦ ቆይቷል።
ሆኖም መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ/ም በቡድን ሆነው የመጡ ሰዎች ወደ ኢሰመኮ ጋምቤላ ጽሕፈት ቤት በመሄድ የተለያዩ የጥፋት ድርጊቶችን የፈጸሙ ሲሆን፣ በኢሰመኮ ባልደረቦች ላይ #ዛቻ እና #ማስፈራሪያ አድርሰዋል።
እንዲሁም በከተማዋ የተለያዩ የስብአዊ መብቶች ሥራዎችን በሚያከናውኑ ሌሎች ድርጅቶች ላይ ተመሳሳይ ጥፋት አድርሰው ድርጅቶቹ ከከተማው ለቅቀው እንዲወጡ አስፈራርተዋል። "
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia