TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የተማሪዎች ምረቃ ቀጥላል ...

#GambelaUniversity

ዛሬ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በመጀሪያ እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 1 ሺህ 229 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

በመጀመሪያ ዲግሪ 958 ተማሪዎችን የሚመረቁ ሲሆን 389 ሴቶችና 596 ወንዶች ናቸው።

በሁለተኛ ዲግሪ ደግሞ 45 ተማሪዎች የሚመረቁ ሲሆን ከነዚህ መካከል አምስቱ ሴቶች ናቸው።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

#ArsiUniversity

አርሲ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃግብሮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 959 ተማሪዎቹን አስመርቋል።

ከተመራቂዎች መካከል 732ቱ ሴቶች ናቸው።

ተማሪዎቹ በጤና፣ በቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ፣ በትምህርት እና ስነባህሪ፣ በህግ፣ በማህበራዊ ሳይንስና ሂዩማኒቲስና በግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጆች የሰለጠኑ ናቸው።

#MetuUniversityBeddeellee

የመቱ ዩኒቨርሲቲ የበደሌ ግብርናና ደን ሳይንስ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት 543 ተማሪዎቹን አስመርቋል።

PHOTO : Maye (Gambella Tikvah Family) ፣ Ibra Abdu (Arsi Tikvah Family) ፣ ENA ፣ OBN
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia