TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶክተር ዊሊያም ሩቶ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዜዳንቱ አዲስ አበባ ሲደርሱ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተቀብለዋቸዋል። ሩቶ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያደርጉ የተገለፀ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሀገር አቀፍ የቴሌኮም ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል። ዶ/ር…
#Kenya #Ethiopia

ፕሬዜዳንት ዶክተር ዊሊያም ሩቶ የኢትዮጵያ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ኬንያ አመሻሹን ተመልሰዋል።

ጉብኝታቸው ምን ይመስል ነበር ? የኬንያ ፕ/ት ፅ/ቤት ምን አለ ?

- ፕሬዝዳንት ሩቶ ጥዋት አዲስ አበባ ሲገቡ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው ቦሌ ኤርፖርት ተገኝተው የተቀበሏቸው።

- ከዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

- ከቀናት በፊት የተመረቀውን የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየምን ከዶ/ር ዐቢይ ጋር ሆነው ጎብኝተዋል።

- ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ጋር ሆነው በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

እንደ ኬንያ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት (ስቴት ሀውስ) መረጃ ፦

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ረጅም ጊዜ የዘለቀ ግኝኑነት እና ቅርበት በመጠቀም የድንበር ተሻጋሪ ንግድን ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት የገለፀች ሲሆን ፕሬዜዳንት ሩቶም ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

" የኬንያ - ኢትዮጵያ አጋርነት ለጋራ ተጠቃሚነታችን እና ቀጠናዊ መረጋጋት የማዕዘን ድንጋይ ነው " ሲሉ ሩቶ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፕሬዜዳንቱ ኢትዮጵያ #የላሙ_ወደብን ለደቡብ ኢትዮጵያ ክፍል እንደ መነሻ ወደብ እንድትጠቀም ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ የኬንያ ፕ/ት ፅ/ቤት / የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia