TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጅግጅጋ⬆️የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ሙስጠፋ_መሀመድ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ጎብኝተዋል።

©ጋሻው ሲሳይ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሶማሌ ክልል⬆️

የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፋ_መሀመድ ከክልሉ ፖሊስ አባላት ጋር በክልሉ ወቅታዊ የሰላም ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአፋር እና በሱማሌ ክልሎች #አዋሳኝ አካባቢዎች ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት እንደሚሰሩ የሁለቱ ክልል ከፍተኛ ርዕሰ መሰተዳደሮች ገለፁ፡፡

የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሙስጠፋ_መሀመድ እና የአፋር ክልል ርዕሰ መሰተዳደር አቶ #አወል_አርባ ዛሬ በአዲስ አበባ በሁለቱ ክልሎች የፀጥታ ችግር መፍትሄ ዙሪያ ላይ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በሁለቱ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች አንድም ሰው እንዳይሞት እና ግጭት እንዳይከሰት የማድረግ ሰራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትር ዲኤታው አቶ #ዘይኑ_ጀማል በበኩላቸው ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎች በአስቸኳይ የሀገር ሽማግሌዎች ቡድን እንዲቋቋምና ችግሩ በዘላቂነት ሊፈታ እደሚገባው ተናግረዋል፡፡ በአጠቃላይ ጉዳይ ላይም በህዝብ ለህዝብ #ውይይት ሊፈታ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ክልሎቹ #ከማንነት እና #ከወሰን ጋር ያሉ ችግሮችን ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia