TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NobelPeacePrize

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኖርዌይ ኦስሎ ከኖቤል ኮሚቴ አባላት ጋር ተገናኝተዋል። #Norway #Oslo

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የሰላም የኖቤል ሽልማታቸውን የሚቀበሉበት ሥነ ሥርዓት ነገ ማክሰኞ፤ ኅዳር 30 / 2012 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ምሽት በኖርዌይ የኖቤል ተቋም የክብር እንግዳ መዝገብ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክብር እንግዳ መዝገቡ ላይ በአማርኛ አስተያየታቸውን ያሰፈሩ የመጀመሪያው ሎሬት መሆናቸውን ከኖርዌይ የኖቤል ተቋም የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን ለጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ ሽልማት ከመስጠታቸው በፊት ባደረጉት ንግግር ጠቅላይ ሚንሥትሩ ለሰላም ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ ሰላምና ዲሞክራሲን ለማስፈን በርካታ ርምጃዎችን መውሰዳቸው እንዲሁም በካቢኔያቸው አምሳ በመቶ ሴቶችን መሾማቸዉ ተመስግኗል። በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰላም ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ሣኅለ-ወርቅ ዘውዴ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ማአዛ አሸናፊ ሴቶች መኾናቸውን ሊቀመንበሯ አመስግነዋል።

ሽልማቱም የተሰጠው፦ ሰላም እና ብልጽግና በኢትዮጵያ ለማስፈን ዓልመው መነሳታቸው ሊቀመንበሯ ገልጠዉ የኖቤል ኮሚቴዉ ዕውቅና ሰጥቶታል። በምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት ሰላም እንዲሰፍን ጠቅላይ ሚንስትሩ ላበረከቱት አስተዋጽዖም በኮሚቴው ተመስግነዋል።

ኤርትራ እና ጅቡቲ ሰላም እንዲፈጥሩ ጥረት መደረጉ፤ በደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ሰላማዊ መፍትኄዎችን እንደ አማራጭ መወሰዳቸው ተወድሷል። «ኢትዮጵያ የሰው ልጆች መገኛ ናት» ያሉት የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን፤ «የመጀመሪያው ሆሞ ሴፒያን የፈለሰው ከእርስዎ [ጠ/ሚ ዐቢይ]ሀገር ነው፣ በዚህም እኛ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን» ብለዋል። ኢትዮጵያ በአዉሮጳዉያን ቅኝ አለመገዛትዋ፤ የአፍሪቃ ኅብረት መቀመጫ መኾኗ ከመድረኩ ሲገለጥም ሞቅ ያለ ጭብጨባ ከታዳሚያን ተሰምቷል።

(DW)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize #AbiyAhemedAli

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኦስሎ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ አቀባበል ሊደረግላቸው ነው። የዘንድሮው የሰላም ኖቤል አሸናፊ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ነገ ወደ አገራቸው ይመለሳሉ።

የአዲስ አበባ ከንቲባ ከደቂቃዎች በፊት በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ አቀባበል ይደረግላቸዋል።

ኢንጅነር ታከለ እንዳሉትም የአዲስ አበባ ህዝብ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ተገኝቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባል እንዲያደርግላቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

(ETHIO FM 107.8)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

የዓለም የኖቤል የሰላም ሎሬት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ማለዳ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ 2019 የኖቤል የሰላም ተሸላሚ በመሆን ሽልማታቸውን ከትናንት በስቲያ በኖርዌይ ኦስሎ በተካሄደ ደማቅ ስነ ስርዓት መቀበላቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ አዲስ አበባ ሲደርሱም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ለክብራቸውም 21 ጊዜ መድፍ ተተኩሷል።

(ኤፍቢሲ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#NobelPeacePrize

‹‹የራስ ሀገር ዜጋ ትልቅ ለሆነ የክብር ሽልማት ሲበቃ ደስ የማይለው ሰው ቢኖር እጅግ በጣም ጥቂት ነው። እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ደስ ብሎኛል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የነበረው ክብርና ዝና የሚያመጣውን ኃላፊነት መሸከም ከባድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጫዊ ሰላም ያደረጉትን ሀገር ውስጥ ያለውን ሰላም ከፍ በማድረግ፣ የህዝቦች ወድማማችነት እንዲጠናከር፣ ሰው በነፃነት ወጥቶ እንዲገባ፣ የህግ የበላይነት እንዲከበር ለማድረግ መስራት ይጠበቅባቸዋል። ከጎረቤት ሀገራትና ከሌላው አለምም ጋር መልካም ግንኙነት ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም አሁን በሀገር ውስጥ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አስተማማኝ የሆነ ዘላቂ ሰላም ያስፈልጋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማቱ ያሸከማቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ፈጣሪ ይርዳቸው።" - አቶ በቀለ ገርባ (የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ /ኦፌኮ/ ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#NobelPeacePrize

ከትናንት በስቲያ በኖርዌይ ኦስሎ በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማታቸውን ለተቀበሉት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በአሁኑ ሰዓት በብሔራዊ ቤተመንግስት አቀባበል እና የእራት ግብዣ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ በኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በተዘጋጀው በዚህ አቀባበል እና የእራት ግብዣ ላይ የፌደራል እና የክልል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

100ኛው የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማት አንደኛው ሜዳሊያና ዲፕሎማ በብሔራዊ ሙዚየም እንዲቀመጥ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ወስኗል። ሜዳሊያውና ዲፕሎማው በብሔራዊ ሙዚየም የሚቀመጠው እሁድ ታህሳስ 5 ከቀኑ 8፡30 ነው ተብሏል።

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ያገኙት የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አንደኛው ሜዳሊያና ዲፕሎማ በብሔራዊ ሙዚየም የማስቀመጥ ስነ ስርዓት እየተከናወነ ነው።

(📸ኤፍቢሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia