TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብሏል።

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተናን ለመስጠት ዝግጅት #መጠናቀቁንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ይህንን የገለፀው የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ባለፉት 6 ዓመታት ከፈተና ስርቆትና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ጋር ተያይዞ ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ችግር ገጥሞት የነበረ መሆኑን ገልጾ ዘንድሮ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ተፈታኞች ከቀጣይ ሰኞ ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲፈተኑ እንደሚደረግ ገልጿል።

ይሁን እንጂ ዘንድሮ ከ900,000 በላይ ተማሪዎች ለፈተና የሚቀመጡ በመሆኑ ይህንን ቁጥር በአንድ ጊዜ ማስተናገድ ባለመቻሉ በሁለት ዙር ፈተናው እንደሚሰጥ አስረድቷል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከመስከረም 26-28 ወደሚፈተኑባቸው ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡ ሲሆን ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 02 ፈተና ወስደው ከጥቅምት 03 ጀምሮ ወደመጡበት እንደሚመለሱ ተጠቅሷል።

በ2ኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከጥቅምት 5 አስከ ጥቅምት 6 ወደ ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡ ሲሆን ከጥቅምት 8 እስከ ጥቅምት 11 ፈተና የሚወስዱ ይሆናል።

ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን እና ሌሎችም ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ ቁሶችን መያዝ እንደማይችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላምና ፀጥታ ጋር ተያይዞ መፈተን የማይችሉና ከሀገር የወጡ የኮሚኒቲ ተማሪዎች በአጠቃላይ 56,000 ተማሪዎች ሲሆኑ በቀጣይ #ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደሚዘጋጅላቸው ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብሏል። የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተናን ለመስጠት ዝግጅት #መጠናቀቁንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ይህንን የገለፀው የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው። ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ባለፉት 6 ዓመታት ከፈተና ስርቆትና…
ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ፦

(ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ - የትምህርት ሚኒስትር)

- በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላም እና ፀጥታ ጋር ተያይዞ መፈተን የማይችሉ እና ከሀገር የወጡ የኮሚኒቲ ተማሪዎች በአጠቃላይ 56,000 ተማሪዎች ሲሆኑ በቀጣይ #ሁለተኛ ዙር ፈተና ይዘጋጅላቸዋል።

- አሁን ለፈተና ለማይቀመጡ 56 ሺህ ተማሪዎች በአንድ ወር ውስጥ ለፈተናው እንዲቀመጡ ይደረጋል።

- ከመስከረም 30 ጀምሮ የሚሰጠው ብሄራዊ ፈተና ዝግጅት እና ህትመት በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።

- ተማሪዎችን ወደ ተመደቡባቸው አካባቢዎች የሚያደርሷቸው የክልል የፀጥታ አካላት ሲሆኑ በዩኒቨርሲቲዎች የጥበቃና ፍተሻ ስራን የሚሰሩት #የፌዴራል_ፖሊስ አባላት ናቸው።

(WMCC/ኢብኮ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አምባሳደር ማይክ ሐመር ምን አሉ ? የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር በኢትዮጵያ ከነበራቸው የ10 ቀናት ቆይታ በኃላ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም የተለያዩ ሃሳቦችን አንስተዋል። ኤርትራን በተመለከተ ፦ " የኤርትራ ሠራዊት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ለጦርነት መሰለፉ ያሳስበናል፤ እንቃወማለንም። የትኛውም የውጭ ተዋናይ የኢትዮጵያን የግዛት ሉዓላዊነት ማክበር ጦርነቱ…
#USA

አምባሳደር ማይክ ሐመር ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ወደ ኬንያ ፣ ደቡብ አፍሪካ እና #ኢትዮጵያ ጉዞ ያደርጋሉ።

የአሜሪካ አፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ከጥቅምት 3 እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2022 ወደ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ እንዘሚጓዙ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዛሬ አሳውቋል።

ሐመር ወደ ቀጠናው የሚመለሱት በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆምና በአፍሪካ ህብረት የሚመራ የሰላም ድርድር እንዲጀመር ለመደገፍ ነው ተብሏል።

በናይሮቢ ቆይታቸው ከኬንያ መንግስት ባለስልጣናት፣ ዓለም አቀፍ አጋሮች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ሌሎች ሰላምን ለመፍጠር እና ሰብአዊ እርዳታን ለተቸገሩ ወገኖች ለማድረስ በቀጠናዊ ጥረቶች ላይ ከሚሳተፉት ጋር አካላት ጋር ተገናኝተው ይመክራሉ።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት መረጃ ባለፈው መስከረም 27 ቀን 2022 በዋሽንግተን የአሜሪካ-ደቡብ አፍሪካ የአፍሪካ እና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች የስራ ቡድን በሰሜን ኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ ላይ ውይይት መደረጉን የሚጠቁም ሲሆን ይህን ውይይት ተከትሎ ልዩ መልዕክተኛው ሐመር ወደ ፕሪቶሪያ በማቅናት ከደቡብ አፍሪካ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ይገናኛሉ። በዚህም ወቅት በአፍሪካ ኅብረት የሚመራውን የሽምግልና ጥረት ለመደገፍ ስለሚደረጉ ጥረቶች ይመክራሉ።

አምባሳደር ማይክ ሐመር በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም ከአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው ይመክራሉ።

በተጨማሪም ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ የሰብዓዊ ድጋፍ ከሚሰጡ እና የድርቅ ምላሽ ከሚሰጡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ባለስልጣናት እና ከሌሎችም አጋሮች ጋር ይገናኛሉ።

ልዩ መልዕክተኛው ሐመር ፤ ግጭቱን ለመፍታት እና ብሄራዊ እርቅን ለማምጣት በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ ተጠያቂነትን የማስፈን አስፈላጊነት ላይ አፅንኦት ይሰጣሉ ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ አምባሳደር ማይክ ሐመር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ የሁሉንም ወገኖች ጥቅም የሚያስጠብቅ እና የበለጠ ሰላምና የበለፀገ ቀጣና እንዲኖር በሚደረግ አስተዋጽኦ ላይም ይሳተፋሉ ሲል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ ቤት አሳውቋል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር ከሳምንታት በፊት ኢትዮጵያ መጥተው ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት እንዲሁም ከሌሎችም አካላት ጋር ውይይት አድርገው  እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና በ10 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚገኙ 31 ማዕከላት ይሰጣል፡፡

ፈተናው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ እየሠራ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በክልሉ ሁሉም የመፈተኛ ተቋማት እና ማዕከላት በቂ የጸጥታ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ምክትል ኮሚሽነር እንየው ዘውዴ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ወረዳን ማዕከል አድርጎ ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተቀመጠው ጊዜ ለማድረስ በቂ የትራንስፖርት አገልግሎት ዝግጅት ማድረጉን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ውቤ አጥናፉ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች የወረዳ ትራንስፖርት ቢሮ በሚያወጣው መርሃ ግብር መሰረት በጊዜ እየተገኙ እንዲስተናገዱ ጠይቀዋል፡፡

ሀገራዊ ግዴታቸውን በአግባቡና በሀላፊነት የማይወጡ የትራንስፖርት ማህበራትና ባለሀብቶች በትራንስፖርት መመሪያ እና በሕግ ይጠየቃሉ ብለዋል፡፡

ተማሪዎች በሚጓጓዙባቸው ቀናት መደበኛ ትራንስፖርት ስለማይኖር ሕዝቡ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እንዲተባበር ጥሪ አድርገዋል፡፡

ምንጭ፦ አሚኮ

More : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#AI2022 #ኢትዮጵያ🇪🇹 ሀገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪየውን የፓን አፍሪካን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ኮንፈረንስ ልታካሂድ ነው። ኮንፈረንሱ ከጥቅምት 4 እስከ 5 (2022) ድረስ ነው የሚካሄደው። ይኸው የመጀመሪያ የሆነው ኮንፈረንስ የሚካሄደው በአዲሱ የሥነ ጥበብ እና ሳይንስ ሙዚየም መሆኑ ታውቋል። ኮንፈረንሱን ለመታደም ለመመዝገብ : panafriconai.org Via Billene Seyoum…
#ETHIOPIA

ዛሬ ' የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም ' በጠ /ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተመርቆ ተከፍቷል። ከሙዚየሙ ምርቃት ባለፈም ጠቅላይ ሚስትሩ የቴክኖሎጂ ዐውደ ርእይ አስጀምረዋል።

በተጨማሪም ለ2 ቀናት የሚቆየው የመጀመሪያው የፓን አፍሪካን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስ ዛሬ ተከፍቷል። ይኸው ኮንፈረንስ የሚካሄደው ዛሬ በተመረቀው የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም ነው።

ℹ️ አጭር መረጃ ስለ ኢትዮጵያ የሳይንስ ሙዚየም ፦

- በ6.78 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ሙዚየሙ ሁለት ግዙፍ ህንጻዎች አሉት።

- ትልቁ ህንጻ ከ15 ሺህ ሜትር ካሬ በሚበልጥ መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን አጠቃላይ ስፋቱ 132 ሜትር ያህል ነው።

- በሙዚየሙ ውስጥ ቋሚ እና ጊዜያዊ አውደ ርዕይ ማሳያዎች አሉት።

- ሙዚየሙ ሳይንስ ጥበባዊ በሆነ መንገድ የሚገለጽበት ጥበብም ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚታይበት ነው።

- ከተፈጥሮ ስርዓት ጋር ተስማሚ ሆኖ የተገነባው ሙዚየሙ ከጸሐይ ብርሀን የኤሌክትሪክ ሀይል የሚያገኝ ሲሆን የሙዚየሙ ውጫዊ ክፍል የቀለበት እና የጉልላት ቅርጽ እንዲኖረው ተደርጎ  የተገነባ ነው፡፡

ፎቶ ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት እና Zaho Zhiyuan (በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር)

@TIKVAHETHIOPIA
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA አምባሳደር ማይክ ሐመር ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ወደ ኬንያ ፣ ደቡብ አፍሪካ እና #ኢትዮጵያ ጉዞ ያደርጋሉ። የአሜሪካ አፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ከጥቅምት 3 እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2022 ወደ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ እንዘሚጓዙ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዛሬ አሳውቋል። ሐመር ወደ ቀጠናው የሚመለሱት በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆምና…
#USA #KENYA

ትላንት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በስልክ ከጎረቤታችን ኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ጋር በተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮቻቸውና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን " ሲትዝን ቲቪ ኬንያ " ዘግቧል።

እንደ ዘገባው ከሆነ ፤ ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ሲሆን የተወያዩባቸው #ዝርዝር_ጉዳዮች በይፋ አልተገለፀም።

አሜሪካ ከሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ጋር በተያያዘ በአፋጣኝ ግጭት እንዲቆምና በአፍሪካ ህብረት የሚመራ የሰላም ድርድር እንዲጀመር ለመደገፍ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛዋን አምባሳደር ማይክ ሀመርን ወደ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ እና ኢትዮጵያ (ከጥቅምት 3 - ጥቅምት 18 /2022 ድረስ) ልካለች።

https://www.citizen.digital/news/president-ruto-blinken-discuss-fertilizer-crisis-ethiopia-and-russia-ukraine-conflict-n306753

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የትምህርት ሚኒስቴር የብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ ፦

(ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ - የትምህርት ሚኒስትር)

- የፈተና ንክኪው በእጅጉ ተቀንሷል።

- ከዚህ በፊት በፈተና አሰጣጥ ወቅት የነበረውን " የኔ አካባቢ ሰው ፣ የኔ ዘመድ " የሚለውን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ማንኛውም የአንድ አካባቢ ተወላጅ እዛው አካባቢ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም። ማንኛውም የአንድ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እራሱ የሚያስተምርበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አይፈትንም።

- ተማሪዎች አንዴ ዩኒቨርሲቲ (ካምፓስ) ከገቡ በኃላ ከሌለው የውጪ ማህበረሰብ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አይኖራቸውም። ምንም ስልክ ወይም ሌላ የግንኙነት ነገር ይዘው አይገቡም።

- ተፈታኝ ተማሪዎች ለ4 ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ እናበላቸዋለን ፣ እናጠጣቸዋል፣  እንከባከባቸዋለን ነገር ግን በፍፁም ከሌላው ዓለም ጋር አይገናኙንም።

- ተማሪዎች ከሚነሱበት ቦታ የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው እንዳይሄዱ የክልል የፀጥታ ኃላፊዎች የፍተሻ ስራ ይሰራሉ፤ የክልል የፀጥታ አከላት ስራ ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲ በር ላይ እስኪደርሱ ብቻ ነው ከዛ በኃላ ያለውን የፍተሻ እና ጥበቃ ስራ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ይሆናሉ።

- ስልክ ይዞ አንድ ተማሪ ቢገኝ ስልክ ይቀማል ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ፈተናውን እንዳይወስድ ይደረጋል።

- ተማሪዎች በምንም ሁኔታ ፈተና ከሚወስዱበት ግቢያቸው ውጭ መውጣት አይችሉም፤ ከማንም ጋር መገናኘት አይችሉም።

- ከፍተኛ ዝግጅት እያደረግን ስለቆየን ችግር ይኖራል ብለን አናምንም።

- በእስር ላይ ላሉ፣ በውጭ ላሉ የኮሚኒቲ ት/ቤቶች ፣ በፀጥታ ምክንያት ፈተናውን ለመውሰድ ለማይችሉ ሌላ ሁለተኛ ፈተና ተዘጋጅቶላቸዋል። በአንድ ወር ውስጥ ይሰጣቸዋል።

የተፈጥሮ እና ሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች በተለያየ ጊዜ መፈተናቸውን ተከትሎ ተመሳሳይ የሆኑ ትምህርቶች እንዴት ይሰጣሉ ?

በትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ላይ እንደተገለፀው የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት እና ኩረጃን ለመከላከል በ2ቱ ዙር ተፈታኞች መካከል ምንም አይነት ግኝኑነት አይኖርም።

የመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች ፈተናቸውን ጨርሰው ከወጡ ከቀናት በኃላ ነው ሁለተኛው ዙር ተፈታኞች የሚፈተኑት።

ሁለቱም የሚወስዷቸው (የናቹራል እና ሶሻል) አንድ አይነት ትምህርቶች ላይ ጥንቃቄ ተደርጎ የተለያዩ ፈተናዎች ናቸው የተዘጋጁት።

ተማሪዎች ስልክ ይዘው ባለመሄዳቸው ከወላጆቻቸው ጋር እንዴት ይገናኛሉ ?

ትምህርት ሚኒስቴር ኩረጃን እና ስርቆት ለመከላከል ሲባል ተማሪዎች ወደ ሚፈተኑበት ተቋም ስልክ ይዘው መግባት እንደማይችሉ አሳውቋል።

ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ፈታኞችም የፈተና ክፍሎች አቅራቢያ እና ፈተናው የሚሰጥበት አካባቢ ስልክ ይዘው መገኘት አይችሉም።

በየዩኒቨርሲቲዎቹ አንድ አንድ ተወካይ የሚኖር ሲሆን በተወካዩ አማካኝነት ወላጆች ልጆቻቸውን ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ይችላሉ።

የህትመት ዝግጅቱ ምን ይመስላል ? የፈተናው ኮዶች ስንት ናቸው ?

በአጠቃላይ የህትመት ዝግጅቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ጥንቃቄ የተደረገበት ሲሆን የፈተናው ኮዶች በፊት ከነበረው " 4 ኮድ " ወደ " 12 ኮድ " ከፍ ተደርጓል።

ለወላጆች የተላለፈ መልዕክት ፦

ወላጆች ተማሪዎች ይዘው መሄድ የሌለባቸው ፣ እና ስለሚጠበቅባቸው ግዴታቸው አስገንዝበው መላክ አለባቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የትምህርት ሚኒስቴር የብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ ፦ (ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ - የትምህርት ሚኒስትር) - የፈተና ንክኪው በእጅጉ ተቀንሷል። - ከዚህ በፊት በፈተና አሰጣጥ ወቅት የነበረውን " የኔ አካባቢ ሰው ፣ የኔ ዘመድ " የሚለውን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ማንኛውም የአንድ አካባቢ ተወላጅ እዛው አካባቢ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም። ማንኛውም የአንድ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እራሱ የሚያስተምርበት ዩኒቨርሲቲ…
የፈታኝ መምህራን ጉዳይ !

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚፈትኑ መምህራንን ምደባ አካሂዷል።

መምህራኑ ወደ ተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወዳሉ የመፈተኛ ማዕከላት የተመደቡ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ሚቀርቡ ማንኛውም አይነት ጥያቄዎችን እንደማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች እያሳወቁ ይገኛሉ።

በሚኒስተሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 260/2004 አንቀፅ 9(2) በተሰጠው ሥልጣንና እንዲሁም በሀገር አቀፍ የፈተና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1/2012 መሰረት ፈተና ለመፈተን ወደ ሌላ መፈተኛ ማዕከል የተመደበ መምህር በተዘጋጀው የፈተና አሰጣጥ እና አፋጻጸም ማንዋል 01/2014 መሰረት የፌደራል ት/ሚ/ር እና ፈተናዎች አገልግሎት ኤጄንሲ ወደ ተመደበበት ቦታ የመገኘት ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ይገልጻል፡፡

በመመሪያው መሰረት የዩኒቨርሲቲ መምህራን ወደ ተመደቡበት አካባቢ ሄደው የተጣለባቸው #ሀገራዊ_ኃላፊነት የመወጣት ግዴታ ያለባቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከጉዞ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ማንኛውንም ጥያቄ እንደማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች ከወዲሁ እያሳወቁ ይገኛሉ።

ትላንት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ፤ " ከዚህ በፊት የነበረውን የኔ አካባቢ ሰው ፣ የኔ ዘመድ የሚለውን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ማንኛውም የአንድ አካባቢ ተወላጅ እዛው አካባቢ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም። ማንኛውም የአንድ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እራሱ የሚያስተምርበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አይፈትንም " ሲሉ አሳውቀዋል።

(ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከፈታኝ መምህራን ምደባ ጋር በተያያዘ ማንኛውም አይነት ጥያቄ እንደማያስተናግድ ያሳወቀበት ነው)

@tikvahethiopia