TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፈይሳ ሌሊሳ ተሸለመ🔝

ከሁለት አመታት በፊት በሪዮ ኦሎምፒክ እጆቹን ከፍ አድርጎ በማጣመር የኢትዮጵያ መንግሥት በወቅቱ #በተቃዋሚዎች ላይ ይወስድ የነበረውን የኃይል እርምጃ #የተቃወመው ፈይሳ ሌሊሳ በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ሽልማት ተበረከተለት። ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ለፈይሳ ሽልማቱ የተበረከተለት በሪዮ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር #ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ በማስገኘቱ ነው።

Photo: #PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸

በአበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤና ልማት ድርጅት የተከበረውን TIKVAH-ETH ሁለተኛ አመት የምስረታ በዓልን #በፎቶ ተመልከቱ!

📸ዶክተር ኤልያስ ገብሩ
📸የWKU ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ
📸የሰብአዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ
📸የ"ተስፋ የሰነቀ ጉዞ" ፀሃፊ ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ ካሳ
📸የWKU የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶክተር ሲሳይ ሸዋማረ

#ሁለተኛ_አመት🎂#TIKVAH_ETH

#አበበች_ጎበና_የህፃናት_እንክብካቤና_ልማት_ድርጅት #ሀምሌ21

🏷በዕለቱ የተላለፉ መልዕክቶችን በቀጣይ ቀናት በዩትዩብ እና በቴሌግራም ቻናላችን በኩል ወደእናተ ይደርሳል!! በድጋሚ እንኴን አደረሰን!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#TIKVAH_ETH

📹የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፂዮን ተክሉ
📹የWKU ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ደጀኔ አየለ
📹የሰብአዊ መብት ተሟጋች ኦባንግ ሜቶ
📹የ"ተስፋ የሰነቀ ጉዞ" ፀሃፊ ጋዜጠኛ ጥሩወርቅ ካሳ
📹የWKU የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶክተር ሲሳይ ሸዋማረ

#ሁለተኛ_አመት🎂#TIKVAH_ETH

#አበበች_ጎበና_የህፃናት_እንክብካቤና_ልማት_ድርጅት #ሀምሌ21

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA 🇪🇹 #Tokyo2020 ዛሬ ሌሊት ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረጉ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ የአለም አትሌቲክስ ባወጣው የተወዳዳሪዎች ዝርዝር መሰረት ከዚህ በታች የተገለፁ የሀገራችን አትሌቶች ውድድሮቻቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል። በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ፦ - ሀብታም አለሙ - ነፃነት ደስታ - ወርቅውሃ ጌታቸው በ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ ፦ - ጌትነት ዋለ - ለሜቻ ግርማ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA🇪🇹

አትሌት ለሜቻ ግርማ 3,000 መሰናክል በመጀመሪያው ምድብ የማጣሪያ ውድድሩን አድርጎ 8:09.83 #አንደኛ ሆኖ አልፏል።

በሁለተኛው ምድብ ውድድሩን ያካሄደው የሀገራችን ልጅ አትሌት ጌትነት ዋለ 8:12.28 በሆነ ሰዓት በመግባት #ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል፤ ወደቀጣይ ዙር አልፏል።

በመጨረሻው ሶስተኛ ምድብ ውድድሩን ያካሄደው አትሌት ታደሰ ታከለ 8:24.69 በሆነ ሰዓት 8ኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቁ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

@tikvahethsport @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA 🇪🇹 #Tokyo2020 ዛሬ ሌሊት ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረጉ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ የአለም አትሌቲክስ ባወጣው የተወዳዳሪዎች ዝርዝር መሰረት ከዚህ በታች የተገለፁ የሀገራችን አትሌቶች ውድድሮቻቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል። በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ፦ - ሀብታም አለሙ - ነፃነት ደስታ - ወርቅውሃ ጌታቸው በ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ ፦ - ጌትነት ዋለ - ለሜቻ ግርማ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA🇪🇹

800 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ :

አትሌት ሀብታም አለሙ ወደ ቀጣዪ ዙር አልፋለች።

የ800 ሜትር ሴቶች የ ማጣርያ ውድድሯን ያካሄደችው አትሌት ሀብታም አለሙ 2:01.11 በሆነ ሰዓት በመግባት #ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን አጠናቃለች።

ሀብታም የግማሽ ፍፃሜ ውድድሯን ከነገ በስቲያ ቅዳሜ የምታካሂድ ይሆናል።

በሌላኛው ምድብ የ800 ሜትር የማጣርያ ውድድሯን ያካሄደችው አትሌት ነፃነት ደስታ 2:01.98 በሆነ ሰዓት #አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን አጠናቃለች ።

አትሌት ነፃነት ደስታ ከሌሎች የምድብ ማጣሪያ ውድድሮች የተሻለ ሰዓት ካላት የማለፍ እድል የነበራት ቢሆንም ሳይሳካ ቀርቷል።

አትሌት ወርቅውሃ በመጨረሻው ምድብ የማጣሪያ ውድድር ላይ አልተሳተፈችም ፤ ለምን ? ስለሚለው ለጊዜው መረጃ ማግኘት አልተቻለም።

@tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ኢትዮጵያ🇪🇹 ሶስተኛ እና አራተኛ ላይ የሚገኙት ኬንያ እና ኢትዮጵያ ናቸው። 🇪🇹 አባብል የሻነ ፉክክሩ እጅግ በጣም ከባድ ነው። ድል ለሀገራችን🇪🇹❤️! @tikvahethiopia
#Update

ከፍተኛ ተጋድሎ ስታደርግ የነበረችው 🇪🇹 አባብል የሻነ ውድድሩን አቋርጣለች።

#አንደኛ እና #ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያሉት ኬንያ እና ኢትዮጵያ ናቸው። ተያይዘው ነው እየሄዱ ያሉት።

ከኃላ ቀርተው የነበሩት የእስራኤል እና የኤርትራ አትሌቶች ወደፊት ገስግሰው 3ኛ እና 4ኛ ላይ ይገኛሉ።

More : @tikvahethsport

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብሏል።

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተናን ለመስጠት ዝግጅት #መጠናቀቁንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ይህንን የገለፀው የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ባለፉት 6 ዓመታት ከፈተና ስርቆትና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ጋር ተያይዞ ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ችግር ገጥሞት የነበረ መሆኑን ገልጾ ዘንድሮ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ተፈታኞች ከቀጣይ ሰኞ ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲፈተኑ እንደሚደረግ ገልጿል።

ይሁን እንጂ ዘንድሮ ከ900,000 በላይ ተማሪዎች ለፈተና የሚቀመጡ በመሆኑ ይህንን ቁጥር በአንድ ጊዜ ማስተናገድ ባለመቻሉ በሁለት ዙር ፈተናው እንደሚሰጥ አስረድቷል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከመስከረም 26-28 ወደሚፈተኑባቸው ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡ ሲሆን ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 02 ፈተና ወስደው ከጥቅምት 03 ጀምሮ ወደመጡበት እንደሚመለሱ ተጠቅሷል።

በ2ኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከጥቅምት 5 አስከ ጥቅምት 6 ወደ ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡ ሲሆን ከጥቅምት 8 እስከ ጥቅምት 11 ፈተና የሚወስዱ ይሆናል።

ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን እና ሌሎችም ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ ቁሶችን መያዝ እንደማይችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላምና ፀጥታ ጋር ተያይዞ መፈተን የማይችሉና ከሀገር የወጡ የኮሚኒቲ ተማሪዎች በአጠቃላይ 56,000 ተማሪዎች ሲሆኑ በቀጣይ #ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደሚዘጋጅላቸው ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብሏል። የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተናን ለመስጠት ዝግጅት #መጠናቀቁንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ይህንን የገለፀው የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው። ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ባለፉት 6 ዓመታት ከፈተና ስርቆትና…
ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ፦

(ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ - የትምህርት ሚኒስትር)

- በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላም እና ፀጥታ ጋር ተያይዞ መፈተን የማይችሉ እና ከሀገር የወጡ የኮሚኒቲ ተማሪዎች በአጠቃላይ 56,000 ተማሪዎች ሲሆኑ በቀጣይ #ሁለተኛ ዙር ፈተና ይዘጋጅላቸዋል።

- አሁን ለፈተና ለማይቀመጡ 56 ሺህ ተማሪዎች በአንድ ወር ውስጥ ለፈተናው እንዲቀመጡ ይደረጋል።

- ከመስከረም 30 ጀምሮ የሚሰጠው ብሄራዊ ፈተና ዝግጅት እና ህትመት በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።

- ተማሪዎችን ወደ ተመደቡባቸው አካባቢዎች የሚያደርሷቸው የክልል የፀጥታ አካላት ሲሆኑ በዩኒቨርሲቲዎች የጥበቃና ፍተሻ ስራን የሚሰሩት #የፌዴራል_ፖሊስ አባላት ናቸው።

(WMCC/ኢብኮ)

@tikvahethiopia