TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FakeNewsAlert

"የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የስራ መልቀቂያ አላስገቡም!"-የመከላከያ ሚንስቴር የህዝብ ግንኙነት ክፍል

አቶ ለማ መገርሳ የስራ መልቀቂያ አስገብተዋል ተብሎ እየተናፈሰ ያለው ወሬ ሐሰት መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። የመከላከያ ሚንስቴር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ እንዳስታወቀው ሚንስትሩ አቶ ለማ መገርሳ መልቀቂያ አላስገቡም ብሏል።

አቶ ለማ በአሜሪካ ስራቸውን በማከናወን ላይ ናቸው የስራ መልቀቂያ አስገቡ ተብሎ እየተናፈሰ ያለው መረጃ ከአውነት የራቀ መሆኑን አስታውቋል። የኮሚንኬሽን ክፍሉ ለሬድዮ ጣቢያው እንደገለፀው በተቋም ደረጃ እንደዚህ አይነት መረጃ የለም ውሸት ነው ሲል የተናገረ ሲሆን ከዛ ውጪ የሚናፈሰው ወሬ የፖለቲከኞች እንጂ በተቋም ደረጃ ስለዚህ ጉዳይ የተነሳ ነገር የለም ብሏል፡፡

(ETHIO FM 107.8)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#FakeNewsAlert

(Elias Meseret)

ይህ "ዛሬ ጠዋት ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጠ/ሚር አብይ ልዩ ሰው ነው አሉ፣ እሱን በቃላት ለመግለፅ ይከብዳል ብለው ለጋዜጠኞች ተናገሩ" እየተባለ በብዛት ሼር እየተደረገ ያለ ነገር የሀሰት ነው። ብዙ ተከታይ ያላቸው ግለሰቦች፣ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲህም የሚድያ ሰዎች የሀሰት መረጃ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ላለማሰራጨት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አደም መሐመድ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ እየተባለ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የሚሰራጨው መረጃ የበሬ ወለደ አይነት ሃሰተኛ መረጃ ነው ሲል የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።
.
ኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ያሰራጨው መልዕክት፦

".... ይህ መረጃ የበሬ ወለደ አይነት የሃሰት መሆኑን እየገለጽን ላልደረሰው #ሼር በማድረግ እንድታደርሱልን በትህትና እንጠይቃለን!" -

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

(Tigray People's Liberation Front)

- ህወሓት ከሌሎች ድርጅቶች ስለሚኖረው ግንኙነት በተመለከተ አንዳንድ የፌስቡክ ፔጆች እያናፈሱት ያሉት መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑ ልናሳስብ እንወዳለን።

- ሁለተኛ አቶ ጌታቸው ረዳ ከዚሁ ጉዳይ በተያያዘ ከድምፂ ወያነ ቴሌብዥን አደረጉት የተባለው ቃለ መጠይቅም ውሸት መሆኑን እንገልፃለን። በመጨረሻ ይህን ተግባር፣ በየጊዜው የውሸት ፕሮፖጋንዳ በመቅረፅ ህዝብን ለማደናገርና ከራሱ ዋና አጀንዳ እንዲወጣ በማሰብ የተፈበረከ የውሸት አጀንዳ መሆኑ መታወቅ ይኖሩበታል።

(Tigray People's Liberation Front)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

"የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡመድ ኡጁሉ ሞቱ" በሚል ከትላንት ለሊት ጀምሮ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰተኛ ነው። ርዕሰ መስተዳደሩ በህይወት አሉ።

ለውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች መልዕክት፦

- አንድ ዜና ስትሰሙ ከማጋራታችሁ በፊት ደጋግማችሁ አረጋግጡ። ከተለያዩ ሚዲያዎችም በደንብ አረጋግጡ። በፌስቡክ እንኳን ምታነቡትም ደግማችሁ ደጋግማቹሁ አጣሩ። ጥርጣሬ የሚፈጥርባችሁን ዜና ለሌላ ሰው አታጋሩ።

- ዜናውን ማነው የሚያሰራጨው የሚለውን ገምግሙ። ምንጭ ጠይቁ! ከታማኝ ከሚባሉ ገፆችም እንኳን ቢሆን መረጃ ስታገኙ ከሌሎች ቦታዎችን ማጣራት አትዘንጉ።

- አንድ ሚዲያ ያሰራጨውን ዜና ሌሎች ሚዲየዎችስ ምን አይነት መረጃ ሰጡበት ብላችሁ ማረጋገጥ እንዳትዘነጉ።

ከሀሰተኛ መረጃ ተጠንቀቁ፤ እንጠንቀቅ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

ፕ/ሩን በሚመለከት የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው!

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት 'ህወሓት ወንጀል ፈጥሮላቸው የፍርድ ቤት ክስ እና ማዘዣ ወጣባቸው' በሚል በፌስቡክ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጀ ሀሰተኛ ነው። መረጀው የፈጠራ ወሬ እንደሆንም ሰምተናል። ፕሮፌሰር ክንደያም መረጃውን 'ውሸት' ሲሉ ገልፀውታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

'ጉራጌ ቲዩብ, Gurage Tube' በሚባል 5,000 አካባቢ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገፅ ኃይሌ ሪዞርት አርባምንጭ ላይ በኮሮና በሽታ የተያዘ ሰው አለ ተብሎ የተለቀቀው እና ከስራ አስኪያጁ አገኘሁት ያለው መረጃ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን ኃይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ማኔጅመንት አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

በሶማሌ ክልል መፈንቅለ መንግስት ተሞከሮ ከሸፈ መባሉ #ሐሰት መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።

የክልሉ የኮሙንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ ሂቦ መሃመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ እንዳሉት በክልሉ መፈንቅለ መንግስት ተደረገ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ እየተናፈሰ ያለው መረጃ ሃሰት ነው ብለዋል።

ወሬውን የሰማነው ከማህበራዊ ድረገጽ ነው እንጂ የክልሉ አጠቃላይ አመራር በኮሮና ቫይረስ መከላከል ስራ ላይ እየተንቀሳቀሰ ያለው ሲሉ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር እስጢፋኖስ አፈወርቂ የፃፉት በማስመሰል በፎቶሾፕ የተቀነባበረ 'የኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እንዳረፉ' ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያው እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #ሀሰተኛ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተላከ "የትግራይ ክልል ምርጫ መራዘሙን ስለማሳወቅ"' የሚል በፎቶ ሾፕ የተቀነባበረ ሀሰተኛ ደብዳቤ እየተዘዋወረ ይገኛል።

ይህን ደብዳቤ ዋቢ እያደረጉ እጅግ በርካታ ተከታይ ያላቸው ሚዲያዎች ሳይቀሩ ሳያጣሩ እና ለማጣራትም ሳይሞክሩ እያሰራጩት ነው።

ዛሬ ምሽት የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን 6ኛው ክልላዊ ምርጫ ጳጉሜ 4/2012 ዓ/ም እንደሚደረግ ማስታወቁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot