TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሰኔ ወር የዋጋ ግሽበት ...

የ2013 የሰኔ ወር የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ24.5 ከመቶ ጭማሬ አሳይቷል፡፡

የምግብ ዋጋ ግሽበት የሰኔ ወር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ28.7 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በዳቦና እህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በያዝነው ወርም የቀጠለ ሲሆን ፥ በተለይ የበቆሎና የገብስ ዋጋ በፍጥነት #ጨምሯል፡፡ በተጨማሪ ፦
- ሥጋ፣
- የምግብ ዘይት፣
- ቅቤ፣
- ቅመማ ቅመም፣
- በርበሬና ቡና የዋጋ ጭማሪ በዚህም ወር በመቀጠላቸው ለዋጋ ግሽበት ምጣኔ በፍጥነት መጨመር አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

ያለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ዋጋ ከአሁኑ ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር በንጽጽር ዝቅተኛ ስለነበር የዋጋ ግሽበቱ በያዝነው ወርም ከፍ ብሎ ታይቷል፡፡

በሌላ በኩል " ምግብ ነክ " ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት የሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ19 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ከምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋና ምክንያቶች ውስጥ በተለይም
- በአልኮል፣
- ልብስና ጫማ፣
- የቤት እንክብካቤና ኢነርጂ (ማገዶና ከሰል)፣
- የቤት መስሪያ እቃዎች (የቤት ኪራይ፣ ሲሚንቶና የቤት ኪዳን ቆርቆሮ) ፣
- ህክምና እና ጌጣጌጥ (ወርቅ) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ነው፡፡

አጠቃላይ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር 7 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጄንሲ አመልክቷል፡፡

#ኢፕድ

@tikvahethiopia